ቡና የምታፈላበት ስቲም ፈንድቶ ሁለት ዓይኗን ያሳጣት ወጣት ህይወቴን ታደጉኝ በሚል እየተማጸነች ነዉ።
ትእግስት ላቀ ታደለ ትባላለች። ተወልዳ ያደገችዉ በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ደብረ ዘይት ኩችት ቀበሌ ነዉ።
ትእግስት በ2014 የትምህርት ዘመን በሜዲካል ላብራቶሪ በዲፕሎማ ተመርቃለች። ትእግስት ቤተሰቦቿን የመርዳትና ራሷን የመቻል ህልሟ ከፍተኛ ስለነበረ ከ2015 ዓም ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 በተለምዶ አብማ አካባቢ ቡና በማፍላትና በመሸጥ ህይወትን አሃዱ ብላ ጀመረች።
ትእግስት ህይወቴ ይቀይራል ያለችዉ የቡና ማፍላት ስራ ለዓይነስዉርነት ዳረጋት።
ነገሩ እንዲህ ነዉ። ትእግስት እንደተለመደዉ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም እንደወትሮዉ ሁሉ ቡናዋን በማፍላት ደምበኞቿን ለማስተናገድ ደፋ ቀና እያለች ነዉ። ደምበኞችም ቡና ለመጠጣት ወንበራቸዉን ላይ ቁጭ ብለዉ ይጠባበቃሉ። ቡናዉን አፍልታ ለመቅዳት ጎንበስ እንዳለች ቡና ያፈላችበት ስቲም ፈንድቶ በአይኖቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ።
ቡና ለመጠጣት የተቀመጡ ወጣቶች ተሸክመዉ ወደ ሆስፒታል ተሯሯጡ። ከግራና ቀኝ አይኖቿ መካከል ማለትም ከአፍንጫዋ ከፍ ብሎ የማያቋርጥ ደም ይፈሳል።
የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ሙያተኞችና የአመራሮች ምስጋና ይግባቸዉና አስታማሚ የሌላትንና በጎ ፈቃደኞች ያደረሷትን ወጣት የነጻ ህክምና እንድታገኝ በማድረግ ደሙ እንዲቆም፤ ጉዳት የደረሰበት አይኗ እንዲታከም ቢያደርጉም ሁለቱም አይኖቿን ብርሃን መመለስ አልተቻለም።
የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ከግራና ቀኝ አይኖቿ መካከል ማለትም ከአፍንጫዋ ከፍ ብሎ ያለዉ አጥንት በመሰበሩ ለጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሪፈር ብሏታል።
ትእግስት ራሷን በራሷ የምታስተዳድር በመሆኗ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ስለሌላት ደጋግ ኢትዮጵያዊያንን እርዳታ ጠይቃለች።
ትእግስት ''የዓይኔን ብርሃን መመለስ እንኳን ባይቻል የሳሳሁላት ህይወቴ ታደጉኝ'' ስትል እየተማጸነች ነዉ።
✅ ትእግስትን ማግኘት ለምትፈልጉ በ0947890066 ማግኘት የምትችሉ ሲሆን
✅ ገንዘብ ማገዝ ለምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትእግስት ላቀ ታደለ በሚል በተከፈተዉ የሂሳብ ቁጥር 1000657479188 እንድትረዷት በፈጣሪ ስም ትጠይቃለች።
ማገዝ እንኳን ባይችሉ ሸር በማድረግ ለሌሎች በማጋራት የድርሻዎን ይወጡ!
ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ።
Via Gashaye Getahun - East Gojjam Communication