#Day_2
ሀጢአተኛ እና በደለኛ ሆነህ እንኳን እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ ፍቅሩ ገለጦልሀል:: የእርሱ ፍቅር አንተ እርሱን እንደወደድከው ሳይሆን እርሱ እንዴት አንተን እንደወደደህ ነው:: የእርሱ ፍቅር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ፣ የማይቀያየር፣ ዘላለማዊ ነው:: ዛሬ እርሱን ሳታውቅ ያለህበት ሁኔታ ላይ እንኳን ብትሆን፣ እርሱን ያልተከተልክ እንኳ ብትሆን እርሱ አንተን አውቆህ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ የሆነ ፍቅሩን ገልጦልሀል:: ላይጠላህ ወዶህል! አንተን ለመውደድ ሀጢአትህ እና በደልህ ያላገደውን እንዲሁ የወደደህን አባት ልትከተል ትወዳለህ?
1 ዮሐንስ 4:10፤ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram |
Facebook |
Telegram |
TikTok |
Youtube |
Threads