Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ከታሪክ አምባ
(ክፍል አራት)
~
ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:—
"በሐጅ ወቅት መካ ውስጥ ነበርኩ። አንድ ከኹራሳን የሆነ ሰው ‘እናንተ ሑጃጆች ሆይ! እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ! ነዋሪዎች! መጤዎች! አንድ ሺህ ዲናር የያዘ ከረጢት ጠፍቶብኛል። የመለሰልኝ ሰው አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ከእሳትም ነፃ ያድርገው። በምርመራው ቀንም ምንዳና ሽልማት ይኖረዋል’ ሲል ሰማሁት።
በዚህን ጊዜ ከመካ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ትልቅ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳኒዩ ሆይ! ሃገራችን ሁኔታዋ የከፋ ነው። የሐጅ ቀናት ጥቂት ናቸው። ክብረ በአላቱም ውስን ናቸው። የስራ በሮች ተዘግተዋል። ምናልባትም ይሄ ገንዘብ ከድሃ አማኝ፣ ከትልቅ አዛውንት እጅ ወድቆ ወሮታውን እንድትሰጠው ቃል እንድትገባለት ሊከጅል ይችላልና ገንዘቡን ቢመልስ ትንሽ ሐላል ገንዘብ ትቸረዋለህ ወይ?’ አለ።
ኹራሳኒዩ:— ስንት ነው ወሮታው? ስንት ይፈልጋል?
አዛውንቱ:— አንድ አስረኛ ይፈልጋል። መቶ ዲናር። የአንድ ሺው 10%።
ኹራሳኒዩ:— አልተስማማም። ‘አላደርገውም። ይልቅ የዚህን ሰውዬ ጉዳይ ወደ አላህ አስጠጋለሁ። በምናገኘውም (የቂያማ) ቀን ወደሱው እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን፣ ያማረ የሆነ መመኪያ’ አለ።"
ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ድሃ ሰው የተባለው ይሄ ሽማግሌ መሰለኝ። ምናልባትም የዲናሮቹን ከረጢት አግኝቶት ከሱ ትንሽ ፈልጎ ነው። ተከተልኩት። ወደቤቱ ተመለሰ። እንደጠረጠርኩት ነበር።
‘ሉባባ ሆይ!’ ብሎ ሚስቱን ሲጣራ ሰማሁት።
‘አቤት የጊያሥ አባት!’ አለች።
‘የገንዘቡን ባለቤት እያፈላለገ ሲጣራ አገኘሁትኮ። ላገኘለት ሰው ምንም ሊሰጥ አይፈልግም። ከሱ ላይ መቶ ዲናር ስጠን ብየው ነበር። እምቢ ብሎ ጉዳዩን ወደ አላህ አስጠጋ። ምን ባደርግ ይሻላል ሉባባ? የግድ መመለስ አለብኝ። እኔ ጌታዬን እፈራለሁ። ወንጀሌ እንዳይደራረብ እሰጋለሁ’ አለ።
በዚህን ጊዜ ሚስቱ እንዲህ አለች:— ‘ሰውየ! እኛኮ ካንተ ጋር ከአምሳ አመት ጀምሮ በድህነት እየማቀቅን ነው። አራት ሴት ልጆች፣ ሁለት እህቶች፣ እኔ፣ እናቴ አለን። አንተ ዘጠነኛችን ነህ። ፍየል የለን፣ የግጦሽ ቦታ የለን። ገንዘቡን ሁሉንም ውሰድ። ተርበናል አጥግበን። ያለንበትን ታውቃለህ አልብሰን። ምናልባትም አላህ — ዐዘ ወጀለ— ከዚያ በኋላ ያብቃቃህ ይሆናል። ያኔ ቤተሰብህን ካበላህ በኋላ ገንዘቡን ትሰጠዋለህ። ወይ ደግሞ በትንሳኤ ቀን እዳህን አላህ ይከፍልልሃል’ አለች።
ሰውየው:— ሉባባ ሆይ! እድሜዬ 86 አመት ከደረሰ በኋላ ሐራም ልበላ ነው? ድህነቴን ይህን ያክል ከታገስኩ በኋላ አካሌን በእሳት ላቃጥል? ለቀብሬ ከቀረብኩ በኋላ የኃያሉን ቁጣ በራሴ ላይ ላስወስን? በፍፁም አላደርገውም ወላ፞ህ!’ አለ።"
ኢብኑ ጀሪር እዚህ ላይ እንዲህ ይላሉ:— "የዚህ ሰውዬና የሚስቱ ነገር እያስደነቀኝ ተመለስኩኝ። በነጋታው ያ የዲናሮቹ ባለቤት ልክ እንደ ትላንቱ ሲጣራ ሰማሁት። ያ አዛውንት ተነሳና
‘አንተ ኹራሳኒዩ! ትላንት ያልኩትን ብዬህ መክሬህ ነበር። ሃገራችን ወላ፞ሂ አዝመራውና እላቢው የቀለለ ነው። ገንዘቡን ያገኘው ሰው ሸሪዐን እንዳይፃረር ትንሽ ገንዘብ ብትሰጠው፤ ላገኘው ሰው መቶ ዲናሮችን ስጠው ብልህ እምቢ ብለሃል። ገንዘብህ አላህን — ዐዘ ወጀለ— ከሚፈራ ሰው እጅ ላይ ቢወድቅ በመቶው ፋንታ አስር ዲናሮችን ብቻ ብትሰጠው ምናለበት? እነሱንም ይሰትራቸዋል፣ ይሸፍናቸዋል፣ ቀለብም ይሆናቸዋል’ አለ።
ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ገንዘቤን ከጌታዬ ዘንድ እተሳሰበዋለሁ። በትንሳኤ ቀንም ወደሱ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው’ አለ።"
"በቀጣዩም ቀን የዲናሮቹ ባለቤት እንደቀደሙት ቀናት ጥሪውን አስተጋባ። አሁንም ያ ሽማግሌ ተነሳና እንዲህ አለ:—
‘አንተ ኹራሳኒዩ! የመጀመሪያ ቀን ላይ ገንዘቡን ላገኘው ሰው መቶ ዲናር ስጠው ብዬህ እምቢ ብለሃል። ከዚያ አስር አልኩህ እምቢ አልክ። እሺ አንድ ዲናር ብትሰጠውና በግማሿ የሚፈልጋትን ነገር ቢሸምት፣ በግማሿ ደግሞ የሚያልባት ፍየል ቢገዛና ሰዎችን እያጠጣ ገቢ ቢያገኝ፣ ልጆቹን እያጠጣም ምንዳውን ቢያስብ ምናለበት?’
ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ለአላህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በቂያማ ቀንም ከጌታዬ ዘንድ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው።’
ሽማግሌው:— ሰውየውን ልብሱን ጎተተውና ‘ና ተከተለኝ። ዲናሮችህን ውሰድና ሌሊቱን እንድተኛ ተወኝ። ይህንን ገንዘብ ካገኘሁበት እለት ጀምሮ ሰላም አላገኘሁም’ አለ።
ኢብኑ ጀሪር ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ባለ ዲናሩ ሰውየ ከሽማግሌው ጋር ሄደ። ተከተልኳቸው። ሽማግሌው ከቤቱ ገባ። መሬት ቆፍሮ ዲናሮቹን አወጣና ‘ገንዘብህን ውሰድ። አላህን ይቅር እንዲለኝና ከትሩፋቱ እንዲለግሰኝ እለምነዋለሁ’ አለ።”
ኹራሳኒዩ:— ተቀበለና መውጣት አሰበ። በሩ ጋር ሲደርስ እንዲህ አለ:— ‘አንተ አዛውንት ሆይ! እኔ አባቴ ሶስት ሺህ ዲናር ትቶ ሞቷል፣ አላህ ይዘንለትና። እና ‘ሲሶውን አንተ ይበልጥ ይገባዋል ለምትለው ስጥ’ ብሎኝ ነበር። በዚህ ከረጢት ውስጥ ያስቀመጥኩት ለሚገባው ለመስጠት ነው። በአላህ ይሁንብኝ! ከኹራሳን ከወጣሁ ጀምሮ እዚህ እስከምደርስ ድረስ ካንተ የበለጠ የሚገባው ሰው አላየሁም። ስለዚህ ውሰደው አላህ ይባርክልህና። አማናህን ስለተወጣህ፣ በድህነትህ ላይ ስለታገስክ አላህ በመልካም ይመንዳህ’ አለና ገንዘቡን ትቶ ሄደ። ሽማግሌው ተነስቶ አላህን እየተማፀነ ማልቀስ ያዘ። እንዲህም አለ:— ‘የዚህን ገንዘብ ባለቤት (ሟቹን) በቀብሩ ውስጥ አላህ ይዘንለት። በልጁም ይባርክለት።’
ምንጭ:— [ጀምሀረቱል አጅዛኢል ሐዲሢያ፞ህ: 251]
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:—
{ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا (٢) وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا}
"ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰፅበታል። አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።" [አጦ፞ላቅ: 2–3]
=
https://t.me/IbnuMunewor