Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
በረመዳን ወር ፆም ላይ እያለ ግንኙነት የፈፀመን ሰው የሚመለከቱ ህግጋት
~ ~~~~ ~
1. በረመዳን ወር ፆም ላይ እያለ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመ ሰው በቁርኣን፣ በሱናና በኢጅማዕ ፆሙ ይበላሻል፡፡
2. በተጨማሪ ለፈፀመው ከባድ ጥፋት ማካካሻ (ከ -ፋ -ራ) የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ሴቷ በጥፋቱ ላይ ተገዳ ከገባች ቀዷም፣ ማካካሻም የለባትም፡፡ [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/404] በምርጫዋ ከገባች ማካካሻ ይመለከታታል ወይስ አይመለከታትም በሚለው ብርቱ ውዝግብ ውስጥ መግባት ስላስፈራኝ አልፌዋለሁ፡፡
4. በእለቱ ፆመኛ ሳይሆን ቀርቶ ግንኙነት ቢፈፅም ማካካሻ አይመለከተውም፡፡
5. አንድ ሰው ረስቶ በመብላቱ ወይም በመጠጣቱ ምክንያት ፆሙ የተበላሸ መሰለውና ከዚያ በኋላ ግንኙነት ቢፈፅም ማካካሻ የለበትም፡፡ ረስቶ መብላትና መጠጣት ፆም እንደማያፈርስ እያወቀ ከዚያ በኋላ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ማካካሻ አለበት፡፡
6. በፆም ግንኙነት መፈፀም ሐራም መሆኑን የማያውቅ ሰው ጥፋቱን ቢፈፅም በጥፋቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ማካካሻም የለበትም፡፡ “ክልክልነቱን አውቃለሁ፡፡ ቅጣቱን ነው የማላውቀው” ቢል ከተጠያቂነት አይተርፍም፡፡ ማካካሻም ይመለከተዋል፡፡ [አልመጅሙዕ፡ 6/381]
7. ፆመኛ መሆኑን ረስቶት (ምናልባት ካጋጠመ) የፈፀመ ሰው ቀዷም ማካካሻም የለበትም፡፡
8. ፈጅር ገና ያልወጣ መስሎት ግንኙነት የፈፀመና ኋላ ላይ ፈጅር ወጥቶ እንደነበር ያረጋገጠ ሰው ቀዷም ማካካሻም የለበትም፡፡
9. ግንኙነት እየፈፀመ እያለ ፈጅር የወጣበት ሰው ቀጥታ ማቆም አለበት፡፡ ካቆመ ቀዷም ማካካሻም የለበትም፡፡ ከቀጠለ ግን ማካካሻ ይመለከተዋል፡፡
10. አንድ ሰው ግንኙነት በመፈፀሙ ምክንያት ማካካሻ ግዴታ ከሆነበት በኋላ በእለቱ ህመም ወይም መንገድ ቢያጋጥመው ማካካሻው አይቀርለትም፡፡
11. በመብላት ወይም በመጠጣት ፆሙን ካፈረሰ በኋላ ግንኙነት የፈፀመ ሰው አቡ ሐኒፋ፣ ማሊክ፣ አሕመድ፣ ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑል ቀይም፣ ኢብኑል ዑሠይሚን፣ ... ማካካሻ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በዚህ አይነት ሰው ላይ ማካካሻ ግዴታ ባይሆን ግንኙነት ለመፈፀም ያለመ ሁሉ ሆን ብሎ አስቀድሞ ፆሙን በመብላትና በመጠጣት የማፍረስ ብልጠት ሊጠቀም ይችላል የሚል ነው፡፡
12. ግንኙነቱን የፈፀመው ከረመዳን ወር ውጭ ከሆነ ፆሙ ትርፍ ፆምም ይሁን የረመዳን ቀዷም ይሁን ሌላግዴታ ፆምም ቢሆን ማካካሻ የለበትም፡፡ ማካካሻ የሚመለከተው ግንኙነቱ በረመዳን ወር ከተፈፀመ ብቻ ነው፡፡
13. በረመዳንም ሙሳፊር ወይም መንገደኛ ከሆነ ግንኙነት ቢፈፅምም ቀዷ እንጂ ማካካሻ አይመለከተውም፡፡ ምክንያቱም መንገደኛ ፍላጎቱ ከሆነ የማፍጠር መብት አለውና፡፡
14. በአንድ ቀን ደጋግሞ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ያለበት ማካካሻ በኢጅማዕ አንድ ብቻ ነው፡፡ ግንኙነቱ በተለያየ ቀን የተፈፀመ ከሆነ በቀኖቹ ብዛት ልክ ማካካሻ አለበት፡፡
15. እስካሁን ያሳለፍነው ቀጥታ ግንኙነት ከተፈፀመ ነው፡፡ እንጂ ግንኙነቱን በሌላ አካሎቿ ለምሳሌ ጭኗ ላይ ቢያደርገው ቀዷ እንጂ ማካካሻ የለበትም የሚለው አቋም የብዙሃን ዑለማእ ምርጫ ነው፡፡ ግንኙነቱ የተፈፀመው በፊንጢጣ ከሆነ ድርጊቱ በራሱ ወንጀል ከመሆኑም ባለፈ ማካካሻ አለበት፡፡
16. ግንኙነቱ በረመዳን ቀን እስከሆነ ድረስ የፈፀመው ከተፈቀደለት ሴት ጋርም ይሁን በሐራምም ይሁን የማካካሻው ብይን እንዳለ ነው፡፡ እያወራን ያለነው ስለ ወንጀሉ እንዳልሆነ ይታወስ፡፡
ማካካሻውን በተመለከተ
-
[U]. በረመዳን ቀን ግንኙነት በመፈፀም ፆሙን ያፈረሰ ሰው ጥፋቱን ለማካካስ የተቀመጡት ነጥቦች ሶስት ናቸው፡፡ እነሱም
1- ባሪያ ነፃ መውጣት፣
2- ሁለት ወር በተከታታይ መፆም እና
3- ስልሳ ምስኪኖችን ማብላት፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
እነዚህ ትእዛዞች በቅደም ተከተል /በተራ/ እንጂ በምርጫ አይደለም የሚፈፀሙት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ባሪያ እንደሌለ ይታወቃል። ስለዚህ 2ኛና 3ኛ ምርጫዎች ይቀራሉ ማለት ነው። 2ኛውን የሚችል ሰው ወደ 3ኛው መዝለል አይችልም፡፡
[ለ]. ስለዚህ የሚችል ከሆነ ሁለት ወር በተከታታይ መፆም አለበት ማለት ነው፡፡ የጨረቃውን ወር አንድ ሲል ተከትሎ ከሆነ የሚፆመው ሁለቱም ወራት 29፣ 29 በድምሩ 58 ቀን ሆነው ቢያልቁም ሁለት ወር ሙሉ እንደፆመ ነው የሚቆጠረው፡፡ የጀመረው ከወሩ መጀመሪያ ካልሆነ ግን ስልሳውን ቀን መድፈን አለበት፡፡ ፆሙን ሆን ብሎ በመሀል ያቋረጠ ሰው እንደገና አንድ ብሎ መጀመር ግዴታው ነው፡፡ በመሀል የተቋረጠው በህመም፣ የወር አበባና መሰል ከአቅም በላይ በሆነ ሰበብ ከሆነ ከቆመበት ይቀጥላል፡፡ መጠንቀቅ የሚችሉት አይነት ምክንያት ከሆነ ግን በዚህ ማቋረጥ አይቻልም፡፡ ያለበለዚያ እንደገና አንድ ማለት ግድ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በመሀል ላይ ከማካካሻው ውጭ የሆነ ሌላ አይነት ፆም እንኳን ማስገባት አይቻልም፡፡ [አልሙግኒይ፡ 7/367]
[ሐ]. ሁለት ወር በተከታታይ መፆም ያልቻለ ሰው የሚኖረው ምርጫ 60 ምስኪኖችን ማብላት ነው፡፡ እዚህ ላይ ማከታተል ግዴታ አይደለም፡፡ ባይሆን አንድን ምስኪን በመደጋገም ሳይሆን የተለያዩ ምስኪኖችን ሊሆን ይገባል የሚያበላው፡፡ የማስረጃው ቀጥተኛ መልእክት ይህን ስለሆነ የሚጠቁመው እራስን ከውዝግብ ማራቁ የተሻለ ነው፡፡ የሚያበላው ቤተሰቡን ከሚመግበው ምግብ መካከለኛ ከሚባለው ያነሰ መሆን የለበትም፡፡
[መ]. ሶስቱንም የማካካሻ አይነቶች መፈፀም ያልቻለ ሰው እስከሚችል ድረስ ይጠብቃል እንጂ ከማካካሻ ነፃ አይሆንም፡፡ [አልኢስቲዝካር፡ 10/105]
ወላሁ አዕለም፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 06/2010)
https://t.me/IbnuMunewor