አዶናይ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


በዚህ ቻናል በኩል የታረደውን የእግዚአብሔር በግ እያከብረን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በውስጥ ሰውነታችንን በሀይል እንበረታለን።
መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው 🥰
@AdonaiComments_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


ከዚች ትርጉም ከሌላት እና ራሷን ካዋረደች አለምና ስርዓት ለዘላለም ለቀን የምንሄድበት ጊዜው በጣም የቀረበ ይመስለኛል ምናልባት ሰሞኑን ሊሆን ይችላል 🤗 ብቻ ጌታ በቅርቡ ይመጣል፤ ዘወትር ልባቹ ለዚህ ፅኑ ተስፋ ንቁ ይሁን።

ኢየሱስ ይመጣል

@thedayofpentecost


በመንፈሳዊ ህይወታቹ እንድጠነክሩ ስለሚረዷቹ እነኚን ሁለት ቻናሎች ሁላቹም እንድትቀላቀሏቸው ጋብዛቿለሁ 🥰

@Teme_Cloud

@PRAYANYTIME


ጥያቄ ?

ከቅርብ ጊዜያት በኃላ በፀሎት ሰዓት ላይ የባዶነት ስሜት እየተሰማኝ ነው ፣ እንደ ቀድሞ መጽሐፍ ቅዱሴን ባነብም ነገር ግን ይሄ ስሜት አልጠፋም ?

መልስ

ይህ የወንድሜ ጥያቄ የእናንተም ጥያቄ ሊሆን ስለሚችል በሚገባቹ መልኩ ለማስረዳት ሞክራለው እናንተ ብቻ ማንበቡ ላይ በርቱልኝ 🥰 አብዛኞቻቹ በፁሎት ሰዓት ወይም ከፀሎት በኃላ ውስጣቹ የባዶነት ስማት የሚሰማቹ ሰዎች ከነኚ ሁለት አይነት አማኞች መካከል ልትሆኑ ትችላላችሁ...

የመጀመሪያዎቹ... በመንፈሳዊ ህይወታቸው ገና ያላደጉ፣ በግላቸውም ብዙም የመፀለይ ልምድ የሌላቸው ሰዎች ሲሆኑ እነኚ ሰዎች ለብቻቸው መፀለይ ሲጀምሩ መጀመሪያ አካባቢ ላይ በፀሎት ሰዓታቸው ላይ ምንም አይነት የተለየ መነቃቃት ላይሰማቸው ይችላል ይህ የሚሆነ በደንብ የውስጥ ሰውነታቸው መጠንከር ስላልጀመረ ነው በተጨማሪም ደግሞ የምታሰላስሉት የእግዚአብሔር ቃል እውቀት በውስጣቹ ከሌለ የፀሎት ጊዜያቹ ድካም የበዛበት ብሎም እንቅልፍ እና ድብርት የተጫጫነው ሊሆን ይችላል... በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳላቹ የሚሰማቹ ልጆች ካላቹ በሚቀጥለው ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት በቀላሉ መውጣት እንደምትችሉ እነግራቿለው🥰

ወደ ሁለተኛዎች ስመጣ... በፀሎት ውስጥ ወይም ከፀሎት በኋላ የባዶነት አይነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ በተቃራኒ በመንፈስ አለም የጠየከሩ፣ ውስጣቸውም በመንፈስ ርሃብ የሚቃጠልባቸው ልጆች ሊሆኑ ይችላል እኔም ብዙ ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ አልፌ ስለማውቅ ሁኔታ ይገባኛል፤ እንደ ጤና ባለሞያ ነገርዬው በምልክት ባስቀምጠው በቀላሉ ትረዱኛላቹ ☺️...ለምሳሌ የ 15 ቀን ፆም ፀሎት ይዛቹ በደንብ እየፀለያቹ እያለ የሆነ ሰዓት ላይ ውስጣቹ ባዶ ይሆናል ተነስታቹ መጽሐፍ ቅዱሳቹ ታነባላቹ አሁንም ግን ከዚያ ሁኔታ ውስጥ መውጣት ይከብዳቿል ፤ በቀን 2 እና 3 ሰዓታት ከጌታ ጋር ጊዜ አሳልፋቹ ስትወጡ እንዳሰባቹ የመንፈስ እርካታ ላይሰማቹ ይችላል... ይህ የሚሆነው አንደኛ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሌለበትን የሆነ Mistake በህይወታቹ ከሰራቹ እግዚአብሔር በዚህ አይነት መልኩ ወደ ፍቃዱ እንድትመለሱ ሊያደርጋቹ ይችላል ሁለተኛው እና አብዛኛው ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የምትገቡበት ምክንያት ከልክ ያለፈ መንፈሳዊ ርሃብ ውስጥ በምቶኑበት ጊዜ ነው አለ አይደል በቃ እስከ ጥግ ድረስ ውስጣቹ የእግዚአብሔር ክብር ሲፈልግ የሚሰማቹ መንፈሳዊ ርሃብ አይነት ልክ ያዕቆብ አለቅህም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ትግልን እንደገጠመው ማለት ነው 🔥እናንተም የምትፈልጉት እስካላገኛቹ ድረስ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ መርካት አትፈልጉም በዚህም ምክንያት ከፀሎት በኋላ እንኳን ምንም እንዳልተቀበላቹ ሊሰማቹ ይችላል ነገር ግን ይህ ትግል የሆነ ከፍታ ላይ ሲያደርሳቹ ትናንት ያልረካቹበት ፀሎት ቀስ በቀስ የእናንተ መዋያ ይሆናል ።

እወዳቿለሁ 🥰

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


የሚጮህ ደም 🗣️

የሰው ደም በባህሪው ለእግዚአብሔር የሚሰማው ድምፅ አለው ብዬ አምናለሁ ትዝ ካላቹ ቃየል አቤልን ከገደለው በኋላ የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር እንደጮኽ መጽሐፍ በግልፅ ይነግረናል ልክ እንደ አቤልም እስከ ዛሬ ድረስ የሰዎች ደም ለፍርድ ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ ለምን አትፈርድም ፣ አታይም ወይ የሚሉ የደም ጩኽቶች በእግዚአብሔር ዘንድ እስከ አሁን ድረስ ይሰማሉ፤ ከዛሬ ሁለት ሺ አመታት በፊት መስቀል ላይ የታረደው የእግዚአብሔር በግ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ የሌሎች ሰዎች ደም ለፍርድ ሲጮኽ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ አሁን አብ የሚሰማው መስቀል ላይ የታረደውን የገዛ ልጁን ደም ነው ይሄ ክቡር ደም ደግሞ ይቅርታ እና ምህረት እንጂ ፍርድን ወደኛ ለማምጣት አይጮህም ለዛም ነው መጽሐፍ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋልብሎ ያለን ፤ እኛም በዚህ ምክንያት ነው በሙሉ ልብ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ያለ ጠበቃችን ነው ለማለት ድፍረትን ያገኘነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


እነኚ የመዝሙር ስንኖች አንብቧቸው

ባየው ባየው አይለወጥም ፍቅሩ ፣
ባየው ባየው አልቀዘቀዘም መውደዱ ፤
ባየው ባየው አይቀየርም እንክብካቤው
እንደ ትናንቱ እንደ ልጅነቴ ሲወደኝ ያው ነው


ስንደክም አቅም ሳጣ ፣ እጆቼ እጆቹን መያዝ ሲከብዳቸው የእርሱ ፍቅር ግን ያው ነው በኛ ድካም የማይቀዘቅዝ ፍቅር በኛ ጥፋት የማይለወጥ ርህራሄ እያሳየ የሚያኖር ድንቅ አባት፤

ጌታ ሆይ በኛ ላይ ስላልተቀየረው ፍቅርህ እናመሰግንሃለን 🥰


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በጣም ድንቅ መልዕክት 💪

ከወንድማቹ ኤርሚያስ 🥰


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


ድሉን ከማ ጋር ?

በመንፈስ አለም በጌታ ፍቃዱ የዘገየ ሰው ብቻውን ሮጦ ካሸነፈው ሰው በላይ ፈጣን ነው፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ድል ሁል ጊዜም የሚገኘው ከሰዎች ጋር በመሮጥ ሳይሆን እርሱን በመጠበቅ ውስጥ ነው። የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ለማሸነፍ ማርፈድ ካለባቹ አመታቶችንም ቢሆን እንኳን አርፍዱ ፤ የምታውቋቸው ሰዎች ከእናንተ ርቀው ቢሄዱም እናንተ ግን ከእርሱ ጋር ሆናቹ መቆምን ምረጡ፤ እርሱ ሳይኖርበት ብዙ ጦሮችን ከምታሸንፉ ይልቅ ጌታ ኖሮላቹ ደጋግማቹ ብትሸነፉ ይሻላቿል፤ ደግሞሞ ለኛ ድል ትክክለኛ ትርጉም የሚኖረው እግዚአብሔር ከፊት ሆኖ የሚመራው ከሆነ ብቻ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አባ እወድሃለሁ 😭

በቅርቡ በ TikTok በኩል በእንደነዚህ አይነት ጥልቅ መልዕክቾች እመጣለሁ 🥰


ከመነካት የመነጨ የፍቅር ቋንቋ 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


በሰማሁት ቁጥር የምነካበት ድንቅ መዝሙር

መዝሙሩ ከወጣ ከ 8 አመት በላይ ቢሆነውም ዛሬም ድረስ ግን ነፍስን የሚነካ ሀይል አለበት🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

2k 0 34 2 27

በየቀኑ እኔን ከጌታ ለመለየት የምትሰሩ መናፍስቶች ግን ምን ነክቷቹ ነው ቆይ ለምን ተስፍ አትቆርጡም ደግሞ አይደክማቹም እንዴ 😁 እኔን ለመጣል ምን ያልፈነቀላቹት ድንጋይ አለ እኔ እንደው አሁንም በጌታዬ እቅፍ ውስጥ ነኝ 😇.. እንደኔ በግ መሆን እና እንደናንተ ተኩላነት ቢሆን ኖሮ ገና ዱሮ ነበር የሚያልቅልኝ ነገር ግን በእኔ እና በእናንተ መካከል አንድ እኔን የሚጠብቅ መልካም እረኛ አለ💪 እና ብዙ አትድከሙ ኢየሱስ የሚባል ጀግና እረኛ አለኝ 🥰


ኑሮ ያልከውን መኖር 😭

ሰሞኑን የዘማሪ ሐዋሪያው ዮሃንስን አንድ መዝሙር እየሰማሁ ከእኔ አልፎ ለናንተም የማካፍለውን ትልቅ መልዕክት በውስጡ አገኘው... መልዕክቱ ከመናገሬ በፊት ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ አሁን ላይ መኖራቹ ትርጉም ያለው ይመስላቿል ? ትርጉምስ አለው ካላቹን ህይወታቹ ትርጉም የኖረው ለእናንተ ነው ወይስ ለእግዚአብሔር ? ? ገና ሳትፈጠሩ በማህፀንም ሳይሰራቹ እግዚአብሔር እንድትኖሩለት ያሰበውን ያንን መኖር እየኖራቹ ከሆነ አዎ መኖራቹ በርግጥ አሁን ላይ ትርጉም አለው፤ ያሰበላቹን ሳይሆን ያሰባቹትን ፣ ፍቃዱን ሳይሆን ፍቃዳቹን ከኖራቹ ደግሞ ምንም ያህል እናንተ እየኖራቹ እንደሆነ ብታስቡም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ገና መኖር አልጀመራቹም፤ ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ስኬቶችና ድሎች ትክክለኛ ትርጉም የሚኖራቸው ከእግዚአብሔር እንፃር ልክ ከሆኑ ብቻ ነው ካለዚያ ግን ድል ላይ ብዙ ድሎች ቢከመሩም እንኳን ሁል ጊዜ ተሸናፊዎች ነን።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


እንደ ምክር ያህል 😇

መቼም ቢሆን በህይወታቹ ውስጥ ዙሪያቹ ያሉትን ሰዎች ላለማስቀየም ብላቹ የእግዚአብሔር ሃሳብ የሌለበትን ውሳኔ በራሳቹ ላይ አትወስኑ ... አሁን ላይ ከጌታ ቤት ስትርቁ፣ ፀሎት ስታቆሙ እና በህይወታቹ ውስጥ የተሳሳተ ውሳኔ ስትወስኑ ልክ ናቹ ብለው ያጀቧቹ ሰዎች ነገ ላይ ስትጎዱ እና ስትደክሙ እናንተን ለማገዝ ማናቸውም አብረዋቹ አይቆሙም...church ስትሄዱ የሚደብራቸው ሰዎች ካሉ እነርሱ ለማስደሰት ብላቹ Church ከምትቀሩ ለዘላለም እነርሱ እየደበራቹ ቢቀጥሉ ይሻላቸዋል፣ በመንፈሳዊ ህይወታቹም ስትበረቱና ፀሎት ስታበዙ ሙድ ለመያዝ የሚሞክሩ ጓደኞችም ካሏቹ እነርሱን ለመምሰል ብዙ አትጣጣሩ ተዋቸው ... አንድ ወርቅ የያዘ ሰው ከዘጠና ዘጠኝ ድንጋይ ከያዙ ሰዎች ጋር አብሮ ብሆንና ድንጋይ የያዙት ሰዎች ሙድ ቢይዙበት ይህ ሰው የግድ እነርሱን ለማስደሰት ብሎ የያዘውን ወርቅ መጣል ሳይሆን ያለበት እነርሱን ትቶ ወርቅ ከያዙ ሰዎች ጋር ነው መቀጠል ያለበት ካልሆነ ግን እነኚ ሰዎች በጊዜ ሂደት እነርሱ የያዙት ወርቅ እርሱ የያዘው ደግሞ ድንጋይ እንደሆነ አሳምነውት ትክክለኛ ወርቅ ያስጥሉታል፤ Be Wise 😇 አሁን ያላቹበት ህይወት በጣም ውድ ነው፤ ሰዎች በዚህ ህይወት ላይሀሳብ እንዲሰጡበት አትፍቀዱላቸው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


አሁን ይሄን ጽሑፍ በምታነቡበት በዚህ ሰዓት ብዙ ሰዎች በራቸውን ዘግተው የእግዚአብሔር ፊት እየፈለጉ እንደሆኑ ስንቶቻቿ አስተውላቿል... በዚህ ሰዓት ተንበርክከው አባ ክብርህ አሳየኝ ፣ ለራስ አድርገህ ለየኝ እያሉ አባታቸው እግር ስር እያለቀሱ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ እናንተ ከነኚ ዘወትር የእግዚአብሔርን ፊት ከሚፈልጉ ሀያላን መካከል ትሁኑ ፣ አትሁኑ አላውቅም ነገር ግን በዚህ ሰዓት ከነኚ ሰዎች በላይ የት መዋል እንዳለባቸው በትክክል ያወቁ ሰዎች አይገኙም... ብዙዎች በየ መጠጥ ቤቱና በየእርኩሰት ስፍራ ላይ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት በጌታ እግሮች ስር ተንበርክኮ እንደመገኘት ያለ ትልቅ እድል የለም😭 የተወደዳቹ ጌታ በየቀኑ ኑሩበት ብሎ በእድሜያቹ ላይ ቀኖች ከተጨመረላቹ ላይቀር እነኛ ቀኖች እግሮቹ ስር ተንበርክካቹ የምታሳልፏቸው ቀኖቹ ይሁኑላቹ🔥

3.4k 0 16 10 116

🎙️ አንተን ፍለጋ

ፍለጋ...ፍለጋ...ፍለጋ
ቀኞቼ ይለቁ አንተኑ ፍለጋ 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


አንተስ ምን ትላለህ ?

ብቻዋን ያመነዘረች ይመስል እሷን ብቻ ይዘው ባንዴ ፀጥ የሚያደርጋትን ድንጋይ እየመረጡ በየአደባባዩ ትወገ ትወገ ብለው ሞቷን ደገሱላት...... ኢየሱስም አይቶ የድርሻውን ድንጋይ እንዲጥል ፈልገው ወደ እርሱ አመጧትና አንተስ ምን ትላለህ ? ብለው ጠየቁት፤ እርሱም ድንጋይ መወርወር ሲገባው ጥቂት ቃላት ወደ ከሳሾቿ ወርውሮ በድብቅ የሰሩትን ኃጢአት በግልፅ ገለጠባቸው ከዛም ድንጋይ ተሸክመው የመጡትን ሰዎች የሰሩትን ኃጢአት አሸክሟቸው ሸኛቸው ኃጢአቷን ይዛ የመጣችውን ሴት ግን የእርሱን ፅድቅ አካፍሏት በሰላም ሂጂ አላት.... የተወደዳቹ ሰዎች ስለናንተ ህይወት እድሉ ቢያገኙ ብዙ የሚያወሩት ይኖራቸዋል... ትወገር ፣ ትሙትትጥፍ ፣ አይለፍላት ፣ አይሳካላት ፣ ብቻ ብዙ ነገር ይላሉ ነገር ግን በእናንተ ህይወት ማንም ምንም ቢናገር መፍረድ እስካልቻለ ድረስ ምንም ማድረግ አይችልም፤ ለዚህ ነው ምን ይላሉ ሳይሆን ምን ይላል ብለን መጠበቅ የሚኖርብን።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


እስከ ዛሬ በህይወታቹ ውስጥ ስለበዛው ታላቅ ምህረት እግዚአብሔርን አመስግኑ🙏

“በተከበበች ከተማ ውስጥ፣ የሚያስደንቅ ምሕረቱን ያሳየኝ፣ እግዚአብሔር ይባረክ።”
መዝሙር 31፥21

3.1k 0 21 4 109

ምን እየሆንን ነው ?

ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ የክርስትናችን መልክ ባንድም በሌላም መንገድ ስርዓት የሚባል ነገር እያጣ መጥቷል፤ ትናንት ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ብዙ ልክ ያልነበሩ ነገሮች አሁን ላይ ግን ተደጋግመው ስለሚደረጉ ብቻ ትክክል መሆን ጀምረዋል፤ በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ስንፀየፋቸው የነበሩ ኃጢአቶች አሁን አሁን በቤተ-ክርስቲያን ደረጃ እንኳን እውቅና እየተሰጣቸው ነው ፤ የእግዚአብሔር ፅድቅ በዘመን አመጣሹ Democracy አሳፋሪ እየሆነ ፣ የኛ ቅጥ ያጣ ነውር ደግሞ በአደባባይ ይጨበጨብለታል 😡 የውላቹ የተወደዳቹ እኛ አገልግሎታችን ለ Media ፍጆታ፣ ጌታን እንድናሳይበት የተሰጠንን መድረክ ደግሞ ለራስ ክብርና ለታይታ እንድናደርገው አይደለም የተጠራነው፤ መቼም ቢሆን ደግሞ የኛ ስህተት በታዋቂ ሰዎች ስለተደገፈ እና ህዝብ ስላጨበጨበለት ብቻ ትክክል አይሆንም፤ሁላችንም ሀሳብ ልክ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ከተስማማ ብቻ ነው ካለዚያ ልክ ናቸው ያልናቸው እውነታዎቻችን ሁሉ ስህተት ይሆናል፤ ክርስትናችንም ቢሆን የእውነት የሚሆነው ዘመን ከሚያመጣው ስልጣኔና በየዘመኑ ከሚነሳው የሰዎች ትምህርት በላይ በእግዚአብሔር እውነት ላይ ከተመሰረተ ብቻ ነው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ክብር ያስመለሱ መሰዊያን ያደሱ🙏
ሁሉም የረሱትን በእድሜአቸው ያነሱ🙌🏼
እግዚአብሔርን ሽተው ታሪክ ያስለወጡ፤
በየዘመናቸው ለእውነት የተሰጡ


ነበሩ አምላካቸውን ፈገግ ያስደረጉ፤
ከእጁ ይልቅ ፊቱን ከምር የፈለጉ፣
ነበሩ አምላካቸውን ፈገግ ያስደረጉ
ከእጁ ይልቅ ክብሩን ከምር የፈለጉ


እግዚአብሔር በየዘመኑ የእውነት የሚኖሩለት ትውልዶች አሉት


ስንቸገርበት ለነበረው ኃጢአትና በጣም ስንፈራው ለነበረው ሞት ሁነኛ የሆነ መድሃኒት ከወደ ቤተልሄም አግኝተናል🤗 ደስ ይበላችሁ 🥰

መልካም በዓል ለሁላቹም


አንድ ሰሞን 💪🔥..... 😞🙇

መፀለይ ታዞትራላቹ ፣ ውስጣቹም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይቀጣጠላል የሚደንቁ ህልሞችንና ራዕዮችንም ማየት ትጀምራላቹ ፣🔥 ነገር ግን ይሄ ከአንድ ሰሞን አያልፍም ደግሞ ወደዛ ወደማቶዱት ህይወት ትመለሳላቹ... መድከም ትጀምራላቹ🙍 ያንን ትጋታቹን ትጥሉታላቹ፣ ኃጢአት Normal ይሆንባቿል ብቻ ብዙ ነገር... አሁን በዚህ አይነት ድካም ውስጥ እያለፈ ያለ ሰው ካለ የምለው ነገር በደንብ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ ፤ " ግን ለምንድነው ምደክመው ? " የብዙዎቻቹ ጥያቄ ነው እስቲ ላንዳፍታ ይሄ ጥያቄ በውስጣቹ የሚፈጠርባቹ ልጆች ጥቂት ጊዜ ወስዳቹ ዙሪያቹን ተመልከቱ...የአባቴ ልጆች እናንተ አላስተዋላቹም እንጂ እኮ የእናንተ አድካሚዎች በዙሪያቹ ነው ያሉት ለምሳሌ ጓደኞቻቹ ፣ የ social media አጠቃቀማቹ እና ሌላም... የተወደዳቹ እንደ ወንድም የምትሰሙኝ ከሆነ አንድ ምክር ልምከራቹ፤ እንድትደክሙ ከሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ራሳቹን አርቁ በቃ ወስኑ አውቃለው ከለመዳቹት ነገር መለየቱ ያማል ነገር ግን እያመማቹም ቢሆን
ሳታውቁት ዛሬ ላይ ሀይላቹን እያደከሙባቹ ካሉ ነገሮች
ፈጥናቹ ራሳቹን አድኑ።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

3.9k 0 27 11 94
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.