#ግብር
🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች
🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።
" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።
አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?
" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።
አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።
'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።
ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።
በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው።
ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።
ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ።
እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።
አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።
ከዚህ ቀደሙ ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ።
በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም።
አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።
እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ።ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።
የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን” ብለዋል።
አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?
" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።
የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።
ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።
ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው።
ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።
እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው " ብለዋል።
(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia