" የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆራረጥ ትምህርታችን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነዉ "- በከምባታ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ ከምባታ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ዉስጥ ባሉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች " የበጀት እጥረት " እየተባለ በሚነገራቸዉ ምክንያት የመምህራን ወርሃዊ ደመወዝ መቆራረጥና መዘግየት በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቅሬታ ካሰሙ ተማሪዎች መካከል በዳንቦያ ወረዳ የፉንጦ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ፣ በቃዲዳ ጋሜላ ወረዳ ጆሬ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ እንዲሁም በሀዳሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ አመሌቃ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ተማሪዎች ይገኙበታል።
ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሰሙ ተማሪዎች ምን አሉ ?
- በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ምክንያት መምህራን በተደጋጋሚ ከት/ት ቤት ስለሚቀሩ በየወሩ ከ5-14 ቀናት የማንማርበት አጋጣሚ እየተዘወተረ መጥቷል።
- አንዳንዶቻችን ወደ ትምህርት ቤት ከ30 ደቂቃ በላይ በእግር ተጉዘን ከደረስን በኋላ " በደሞዝ ምክንያት መምህራን አልገቡም " እንባላለን።
- አሁን አሁን በደመወዝ ወቅት መረጃ እየተቀባበልን ለመምህራን ደሞዝ አለመከፈሉን ካረጋገጥን ከትምህርት ቤት እንቀራለን።
- ይህ ተግባር እየተዘወተረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ዉሏቸዉን ወደ ፑልና ጆቶኒ ጫወታዎች አዙረዋል።
- ትምህርታቸውን አቋርጠዉ የሚያገቡ ሴት ተማሪዎችም አሉ።
- አከባቢያችን በብዛት ወጣቶች ወደ ዉጪ ሀገራት ከሚሰደዱባቸዉ አንዱና ዋነኛው ነዉ። ባለፈዉ ዓመት በትምህርቱ ላይ ተስፋ ቆርጦ አቋርጦ የተሰደደ ተማሪ አለ።
- ቅሬታችንን ለየትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ዩኒት ሊደሮች እኛም ወላጆቻችንም በተደጋጋሚ አቅርበናል ግን " የደመወዝ ጉዳይ ከትምህርት ቤት አቅም በላይ ነዉ፤ መምህራን ሳይበሉና ሳይጠጡ አስተምሩ ብለን ማስገደድ አንችልም " የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መከካል ዘንድሮ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ተፈታኞች እንደሆኑ የነገሩን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች " የዘመናት ልፋታችንና የወደፊት ህልማችን አደጋ ላይ እየወደቀ ነዉ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሔ " ይስጡልን ብለዋል።
" ለሀገር አቀፉ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመዘጋጀት ተጨማሪ የቲቶሪያል ትምህርት ሊሰጠን ቀርቶ መደበኛ የትምህርት መረሃግብሮች በአግባቡ አይሸፈኑም አሁን በዚህ ወቅት እንኳን አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ገና አንድና ሁለት ዩኒቶችን (ምዕራፎችን) ብቻ ነዉ በተንጠባጠበ ሁኔታ የተማርነዉ " ሲሉ ገልጸዋል።
መምህራን ምን አሉ ?
" ብዙ ጊዜ ጮኼን ሰሚ አላገኘንም " የሚሉት በከንባታ ዞን የዳንቦያ፣ ሀዳሮ ጡንጦና ቃዲዳ ጋሜላ ወረዳዎች የሚያስተምሩ መምህራን " የደመወዝ በወቅቱ አለመከፈል፣ መቆራረጥና አልፎ አልፎም በፐርሰንት የመክፈል ችግሮች ባላፉት ሁለት ዓመታት እየተባባሱ መጥተዋል ፤ በርካታ መምህራን በዚህ ምክንያት ስራ ገበታቸዉ ላይ በአግባቡ አይገኙም " ሲሉ ገልፀዋል።
የከንባታ ዞን መምህራን ማህበር ተወካይ አቶ አለሙ አቡዬ ምን አሉ ?
° የደመወዝ መዘግየትና እያቆራረጡ መክፈል በከንባታ ዞን ባሉ ሁሉም መዋቅሮች እየተለመደ መጥቷል።
° ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረጉ ተግባራት ጉዳዩ ከሚያስፈልገዉ ትኩረትና ከሚያሳድረዉ ተፅእኖ አንፃር በጣም ዝቅተኛ ነዉ።
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳዊት ለገሠ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፤ ችግሩ ባለፉት ጊዜያት ዞኑ ያለበትን የብድር ዕዳ ተከትሎ በተከሰተ የበጀት እጥረት በሁሉም የመንግስት መዋቅሮች የሚስተዋል ነው።
" የዞኑ መንግስት ካቢኔ መምህራንን ጨምሮ ለፀጥታ፣ ፍትህ እና የጤና ባለሙያዎች ደመወዝ ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲከፈል ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት እየተተገበረ ነዉ " ብለዋል።
" አንዳንድ ወረዳዎች የኋላውን እየሸፈኑና በብድር የተጠቀሟቸዉን በጀቶች እያተካኩ በሚሄዱበት ወቅት የደሞዝ መዘግየቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። የመማር ማስተማሩ ተግባር እንዳይቆራረጥ በተቻለ መጠን ሁሉ የዞኑና የክልሉም መንግስት ትኩረት ነዉ " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia