#Tigray
ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል።
በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ያጋጠመ ሞት የለም።
ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ?
በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት አስተዳዳሪዎች አሉ። አንዱ የቆየ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾመ ነው።
ሁለቱም ማህተም ይዘው በየፊናቸው " እኔ ነኝ ህጋዊ የቀበሌው አስተዳደር " በማለት ህዝቡን ለሁለት መክፈላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ " ህዝቡ አማርሮ እንድንታደገው ጠይቆናል አዛዦቻችንም ይህንን እንድንፈፅም ልከውናል" ያሉ 9 የሰራዊት አባላት ወደ ቀበሌው ደርሰው ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ማህተም እንዲያስረክቡ ይጠይቃሉ።
" ታስረክባላችሁ አናስረክም " በሚል እልህ በነዋሪዎች እና የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ይነሳል። ነዋሪውም ደንጋይ መወርወር ይጀምራል። የትግራይ ኃይል አባላትም ጥይት ይተኩሳሉ።
በዚህ መካከል በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው እጁ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ሲገባ ሌሎች 20 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በትግራይ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት የደረሰባቸው አሉ።
የወረዳው አስተዳደር ለክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 13 ታጣቂዋች ወደ ወረዳው አስተዳደር በመምጣት የጊዚያዊ አስተዳደር ማህተም እና የፅህፈት ቤት ቁልፍ እንዲያስረክቡዋቸው መጠየቃቸውን እና ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።
ከህወሓት ወደ ሁለት መሰንጠቅ በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸው ሁለት አሰተዳዳሪዎች መስማት የተለመደ ነው።
በአንዳንድ ዞኖች ያሉ ወረዳዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የደብሪፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ለሁለት ተከፋፍለው ይተዳደራሉ።
የትግራይ መሪዎች በተለይም የህወሓት አመራሮች ከዚህ መሰል ህዝብ የሚከፋፍል አደገኛ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች ፤ የትግራይ ኃይል አባላት አንዱን ቡድን ደግፈው ሌላው ቡድን ማውገዝ ተጨማሪ ቀውስ እና ጥፋት ስለሚያስከትል የገለልተኝነት ሚናቸው እንዱወጡ አበክረው እያሳሰቡ ናቸው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia