#MoE
" በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ይወስዳሉ " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
ባለፈው ዓመት ወደ ተግባር የገባው የኦንላይን ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮም እንደሚቀጥል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት 150 ሺ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይ ) እንዲወስዱ ቅድመ ዝግጅ እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።
ይህንን ያሉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ከዚህ ባለፈ በመድረኩ " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥራት ያለው ትምህርት በማግኘት ረገድ እኩል እድል እንዲኖረው ፤ በድሃና ሃብታም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ሥራ መስራት አለብን " ብለዋል።
" ይችን ሀገር መለወጥ የሚቻለው የትምህርት ሥርዓቱን መቀየር ሲቻል " ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተሻለ የመማር ማስተማር እንዲኖር ማድረግ ላይ መሥራት እንደሚገባና ' በትምህርት ለትውልድ ' የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል የተጀመረው ንቅናቄ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ የመምህራንን አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከተመረቁ ዜጎች ውስጥ ልዩ የማስተማር ሙያ (pedagogy) ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሙያው እንዲገቡ እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል።
#MoE
@tikvahethiopia