❤የፍቅር ጥግ!❤
አባትነት በልጅነቴ አይገባኝም ነበር።
በጠዋት የሚወጣ ኮስተር ያለ ሰውዬ ማታ ይመጣል።
አጥና ይላል , ሳጠፋ ይመክራል, ግዛልኝ ያልኩትን አይነት ጫማ እና ልብስ አይገዛም።
እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም።
እንዳይቆጣኝ እርቄ አልሄድም ቤት ውስጥ ቁጭ ካለ እንደልቤ አልነጫነጭም። ካጠፋሁ , ላጠፋ ስል የሱን ስም እየጠሩ ያስፈራሩኛል።
አደኩኝ።
ሳድግ አባቴን አየሁት። ጨዋ ነው , ታታሪ ነው , ለፍቶ አዳሪ ነው። ሀላፊነቱን ይወጣል እንደሱ ደሀ እንዳልሆን ነበር የሚታገለው። ባለጌ እንዳልሆን ነው የሚመክረኝ። ከሱ የተሻለ እንድሆን ነው የታተረው። ፋብሪካ ሰርቶ እየዋለ ነው ደከመኝ ብሎ የማያውቀው። መዝናናት እያማረው ፍላጎቱን ቸል ብሎ ነው የቻለውን ሁሉ ለሚስቱ , ለልጆቹ , ለጎጆው የሚያሟላው።
ስሜቱን ስለሚቆጣጠር ነው የሚሰማውን ሁሉ የማይናገረው። ሲያመው አመመመኝ የማይለው እንዳንጨነቅ ነበር። ሲያመኝ የሆነውን, የምፈልገውን ለማሟላት የሄደበት መንገድ የፍቅሩን መገለጫዎች ሳያቸው መውደዴ ከማዘን ጋር ተጣበቀብኝ።
በቅንነት share & react እያደረጋችሁ
@tksa_tks