ባለቤቴ በለሊት ተነስታ ነጠላዋን አጣፍታ ወደ ቤተስኪያን ጉዞ ልትጀምር ነው ። እንደ ልማዷ "እንቅልፍ የሰማዩን መንግስት የሚያሶርስህ እንዳይመስልህ በል ተነስ!!" የሚለው ንትርኳን ላለመስማት ኮሮና ቫይረስ በቅርቡ የያዘው ገመምተኛ መስዬ ከህይወት መለስ ከሞት ቀነስ ያለ ውሸታም እንቅልፍ ውስጥ ሰጠምኩኝ ።
ነጠላዋን ደግሞ እያጣፋች "የኔ ጌታ አንተ ምን ይሳንሀል ?! አሁን ሳይወድ በግዱ ይሰበሰባታል " ትላለች ። ሶስት ረዘም የሚሉ የጧፍ ዘለላዎችን ደግሞ አፈፍ አድርጋ በጎኗ ሸጎጠች ። ፈገግም እንደማለት ብላለች (የባለቤቴ ሳቅ ሁሉ ችግሮቼን የሚያስረሳኝ ምትሀተኛ ፈገግታ ነው ። እንደውም ከምንም ነገር በላይ በሳቋ ማርካኝ እንዳገባኋት ይሰማኛል ። የእሷን ሳቅ ምድር ላይ የሚወክልልኝ አንዲት ምሳሌ ላጣቅስ ባልችልም የቅዳሜዋ ፀሀይ ግን በትንሹ ልትፎካከራት እንደምትሞክር አውቃለሁ ። እሷም ብትሆን እንደ ስለሺ ስህን ተከታይ ብትሆናት እንጂ የኔን ቀነኒሳ ሳቂ እንደማታስንቃት አውቃለሁ ።
ሳቋ ነፍሴ ነው !!
"ዛሬ ምን ተገኘ ?" ብዙም ነገረ ስራዋ ግልፅ አልሆነልኝም ። ዝም ብዬ በሀሳብ እየተብሰለሰልኩ እንቅልፌን አጣጣምኩኝ ።
ማልዶ ስነሳ "በአስር ሰከንድ ሶስቴ ዱፍ የምትለው ትዕቢተኛ ጀበና ከሰል ማንደጃ ላይ ተጥዳለች ። ፋንዲሻው ጉዝጓዙ ሳሎናችንን አድምቆታል ።
ምንም ሳላስበው ያልተጀመረው ፆሙ ተፈፅሞ ፋሲካ ደረሰ እንዴ ? ብዬ ትንሽ ተብሰለሰልኩ ።
የባላቤቴ እህት ደግሞ አንድ ብርኩማ ላይ በስተጥግ በኩል ተቀምጣ
"እድሜ ለለውጡ መንግስት በይ !! አሁን አንድ ቢራ 30 ብር መግባቷን ሲሰማ ኩም ይላታል "
ኦ ፈጣሪ ! የሰማሁት ድምፅ በህልሜ እንዲሆን ተመኘሁ ። ይሁንና የሰማሁት ድምፅ ፈፅሞ ውሸት አይደለም ።
"እንዴ ይሄን ነገር አምረው እውነት አደረጉት እንዴ ?"
ጓዳ መለስ ብዬ ነስር እንዳስቸገረው ሰው በሁለቱ መዳፎቼ ሁለቱን የሳፋ ጠርዝ ይዤ የምሬን ቆዘምሁ ።
ከደቂቃዎች በኋላ ከየት መጣ ያልተባለ የፍሪጅ ውሀ በአናቴ በኩል ሲንቆረቆር ተሰማኝ ።
"አይዞህ ምናባቱ! ራስህንማ ልትታመም አይገባም ። ቢቀር ቢቀር መጠጣት ቢቀርብህ ነው " ቀና ስል ባለቤቴ በነዛ ሀጫ በረዶ ጥርሶቿ ፈገግታን ተላብሳ እንደ አደይ አበባ ፈክታ ቆማለች ። ለመጀመርያ ጊዜ የሚስቴ ሳቅ ደበረኝ
@wegoch
@wegoch
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ