#### ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ####
(በፈረስ ስማቸው አባ ነፍሶ)
በአገምጃ ሶዶ(ወሊሶ) በሚባል ቦታ በነሀሴ ወር ፲፰፻፶፬ ዓ.ም ተወለዱ። የዓድዋው ጦርነት ሥመ ጥር ጀግናው ባልቻ አባ ነፍሶ ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያ በድጋሚ ስትወር ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋራ ፀብ ስለነበራቸው ባልቻ ከጣልያን ጎን ይሰለፋሉ ብለው ጣልያኖች አሰቡ። ደጃዝማች ባልቻ በንጉሱ ላይ ቅሪታ ቢኖራቸውም በአገር ጉዳይ ላይ ሌላ ድርድር መግባት አልፈለጉም ስለሆነም ጦራቸውን ማሰባሰብ ጀመሩ እናም ከነ ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ፣ አበበ አረጋይ፣ በላይ ዘለቀና አቡነ ጴጥሮስ ጋራ ስለ ጦርነቱ የሚስጥር ደብዳቤ መለዋወጥ ጀመሩ። ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ አምስት ሺ ጦራቸውን ይዘው በ፸፱ ዓመታቸው ከትውልድ መንደራቸው ከአገምጃ ሶዶ ተነስተው አዲስ አበባ ደረሱ ከዛም ረጲ ተራራ ላይ ሆነው መድፋቸውን ጠምደው የሌሎችን አርበኞች መልዕክት ይጠባበቁ ጀመር።ሺ የባልቻ ሰላይ የነበሩት በባንዳ ተይዘው ሲገደሉ ጣሊያን በአውሮፕላን ሆኖ የደጃዝማች ባልቻ ጦርን እየተከተለ በጣም ብዙ ሰው ፈጀባቸው። በህይወት ዘመናቸው ጣልያንን ሁለት ጊዜ የተዋጉት ብዙ ወታደር የነበራቸው ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ብቻቸውን ቀሩ። ባልቻ ሁለት ወንድሞች ነበሯቸው ፊታውራሪ ገብረ መድህን እና ፊታውራሪ ሳህለሚካሄል ሁለቱም በጦርነት ተማርከውና ተገለዋል። በዚህም ጊዜ ደጃች ባልቻ እንዲህ አሉ ጦር መጣ ይላሉ እኔ ምን ቸገረኝ እናቴም ልጅ የላት ለእኔም ወንድም የለኝ። ደጃዝማች ባልቻ በልጅነታቸው ከጦርነት ላይ ተማርከው በአፄ ምኒልክ ቤት ያደጉ ታማኝ የጦር መኮንን የነበሩ...ከዓድዋ ጦርነት ፊት በጅሮንድ ተብለው የንብረት ኃላፊ ነበሩ። ኋላ በዓድዋ ጦርነት ላይ ፊታውራሪ ገበየሁ በጦርነት ላይ በጀግንነት ሲያልፉ መድፈኛነቱን ተክተው በመቀሌ እና በዓድዋ ጦርነት በጀግንነት ተዋግተዋል። ሰውነታቸውም ቀጭን ሆኖ ሳል መድፉን ሲያገላብጡ እንዲህ ተብሎላቸዋል....
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
እንደ ደጋ ገብስ እንዲያ ኮስሶ
ያስቆረጥማል ጠላቱን ኮሶ
የዳኘው ጀግና ባልቻ አባ ነፍሶ።
በጦርነቱም ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ጆሯቸው በመቆረጡ ባለቅኔው እንዲህ አሞገሳቸው
ማን እንዳተ አርጎታል የእርሳሱን ጉትቻ
የዳኘው አሽከር አባ ነፍሶ ባልቻ።
የጠላት ጦር ደጃዝማች ባልቻ ወደሚኖርበት እስከ ጉራጌ ድረስ በመዝለቅ በእሳቸው ላይ ዘመተባቸው ህዝቡም ከዳቸው ወታደሮቹም ለህይወታቸው ሲሉ ሸሿቸው ደጃዝማች ባልቻ እና ሁለቱ አሽከሮቻቸው ከእሳቸው ጋራ ሦስት ሰው ብቻ ቀረ ብዛት ያለው የጣልያን ጦር ከበባቸው ወዴትም መሄድ አልቻሉም ። በመጨረሻም እጅህን ስጥ መሳሪያህን ጣል ብሎ ጣልያኑ ሲያዛቸው ደጃዝማች ባልቻ እኔ እጄን የምሰጥ ሰው አይደለሁም ትጥቄን አልፈታም ብለው ነጩን ጣልያን ገድለው በራሳቸው ጥይት የራሳቸውን ህይወት አጠፉ። እጃቸውን እንኳን ለጠላት ሳይሰጡ በራሳቸው ሽጉጥ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም ተሰው።
@wegoch