ያከሸፈቻቸው ያከሸፏት አገር!
(አሌክስ አብርሃም)
የ8ኛ ክፍል ተማሪወች እንደነበርን ነው። አንድ ቀን የሆነ አስተማሪ ቀረ። በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሰራ (አብዛሀኞቻችን ወሬና መንጫጫት) አንድ ምስጋናው? የሚባል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ። ስዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ስዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ የግንባራቸው መስመር፣ ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች። ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም። እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከነንጉሳዊ ልብሳቸው። ወደጎን ዞር ብለው። ሁላችንም ተገረምን ተደነቅን። የስእሎቹ መጠን የእውነት ሰው ያክሉ ነበር።
ቀጣዮ ክላስ ጅኦግራፊ ነበር። ኮስታራው አስተማሪያችን ገባና ስዕሎቹን አየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ። በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር። ራሱ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ቀጠቀጠው። እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚሸናበት አይደለም ደደብ" ብሎ ደነፋ። ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ሀይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው። አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።
ብዙ ዓመታት አለፉ። አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ አየሁ ምስጋናው ነበር። ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም። ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ የሳለው ስእል በአስተማሪዎቹና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ። ስዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን ብላለች ርዕሰ መምህርቷ። አገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች። ይህ ሒሳብ የገባቸው ብፁአን ናቸው። ለትውልድ ፍቅር ያወርሳሉና።
@wegoch
@wegoch
@paappii