የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን ህልውና ማስቀጠል ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን ህልውና ማስቀጠል እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይሲቲ ፓርክ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይሲቲ ፓርክ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን ሲያኖሩ እንደተናገሩት ፥ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ቀኑን ሙሉ ችግኞችን እንተክላለን፡፡
በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ በአዲስ አበባ በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየተሳተፈ መሆኑም ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር ለወደፊት የሀገር ብልጽግና መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው ፤ የአየር መዛባትን የሚከላከል ነው ፤ ምግብና መድሃኒትም ነው ብለዋል፡፡
በዚህም አረንጓዴ አሻራን ማኖር ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ትልቅ ትሩፋት ነው ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
የችግኝ ተከላው የሚካሄድበት አይሲቲ ፓርክ በከተማዋ ከተመረጡት መካከል አንዱ ሲሆን ፥ ለአካባቢው እና ለስነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
''የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ'' በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መርሐ-ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣የሀይማኖት አባቶች ፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በምንይችል አዘዘው እና በመሰረት አወቀ