የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም እቅድ እና የተማሪ ቅበላ አፈጻጸምን ገመገመ።
(ነሀሴ 30/2016ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎችን ጨምሮ የወረዳ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ቀናሳ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በየጊዜው አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ጠቁመው ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአፋን ኦሮሞ ትምህርትን ተደራሽነት ለማሳደግ ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በመጥቀስ የተማሪ ቅበላ አፈጻጸሙ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ እንዲል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በ2016ዓ.ም የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ግን የተማሪዎች ውጤት በሚጠበቀው ደረጃ ባለመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎም በቀረቡ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎች በስራ ክፍሉ ምላሽ ተሰቷል።