Addis Ababa Education Bureau


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች በትላንትናው እለት ተመርቆ የተከፈተውን ኤግዚቪሽን ጎበኙ።


(ህዳር 13/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲን የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የተዘጋጀውን ኤግዚቪሽን ጎብኝተዋል።


በጉብኝቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት አመታት የተከናወኑ አንኳር ስራዎች በቪአር ፣ በቪዲዮ ፣ በፍቶና በምዴሎች ቀርበው ገለፃ የተሰጠባቸው ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/


ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስማርት በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎት እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረጉ መሠረተልማት ዝርጋታዎች እንዲሁም ስማርት የነዋሪዎች እና የዜጐች ተኮር ከባቢዎች መገንባታቸው፤ ተያይዘው የተፈጠሩ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፤ እና ብቁ እና አመቺ ልማት ቴክኖሎጂን የተደገፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደታቶች በመተግበራቸው ከተማይቱ ይህንን ሽልማት እንድታገኝ አድርጓታል ተብሏል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሸላሚ መደረጉ ለሀገራችን የገጽታ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል : : በአፍሪካ አህጉር ለሚገኙ መሰል ዋና ከተሞች ተምሳሌት የሚሆን ተብሏል።


ይህ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ  በዋናነት በኬንያ መንግስት፣ በናይሮቢ ካውንቲ እና ናይሮቢ በሚገኘው በተመድ የሰዎች ሰፋራ (UN-Habitat) እና ሌሎች አጋር አካላት   በትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።


በዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ልዑካን ቡድን  እየተሳተፉበት የሚገኙ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሚነስትሮች፣ ከንቲባዎች፣ የተለያዩ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

በናይሮቢ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲን በመወከል ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ በሽልማት ስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል ።

የቀጣዩን y 2025 ጉባኤም አዲስ አበባ የምታስተናግድ መመረጧም ተገልጿል


የአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች አዋርድ ተሸላሚ ሆኗ ለች!

ከተማ አስተዳደሩ ሽልማቱን ያገኘነው በከተማችን እየተስራ ባለው የኮሪደር ልማት እና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ለመኖሪያ ምቹ በማድረግ እና ተያይዞም በተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ፤ ቴክኖሎጂ ተኮር የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና አቅርቦት ለነዋሪዎች ያለውን አስተዋፅዖ ጭምር በመለየት የተሰጠ ነው ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባስመዘገባቸው አመርቂ ውጤቶች በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለዉ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተሸላሚ መሆን ችላለች።

የአዲስ አበባ ከተማ ከሌሎች ስማርት የአፍሪካ ከተሞች ጋር ተወዳድራ ሽልማቱን ከሚወስዱ ሶስት ከተሞች መካካል አንዷ መሆን የቻለች ሲሆን ፤ ክብርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባን በመዋክል የተላከው የልኡኳን ቡድን ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ይህ አዋርድ ለአዲስ አበባ ከተማ ሊሰጥ የቻለበት ዋነኛ ምክንያት በኮሪደር ልማት ከተማይቱን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተስማሚ ለማድረግ የተገኘውን አመርቂና ውጤታማ ተግባር መሰረት በማድረግ መሆኑን እና በአርንጓዴ አሻራ የአየር ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለውን ተምሳሌታዊ ተግባር በማስመልከት እንደሆነ ተገልጿል ። በተጨማሪም ሰው ተኮር ስማርት ከተሞች ለትውልድ መገንባት የሚለውን የከተማነት ሀሳብ በከተማይቱ ተግባራዊ በመደረጉ ነው። እንዲሁም ዘመናዊ እና ምቹ ከተማን ለመፍጠር ለአብንትም የእግረኞች መሄጃ እና የሞተር አልባ ተሸከርካሪዎች መንገድ ደረጃውን በጠበቃ ቴክኖሎጂ መገንባታቸውን መሰረት በማድረግ መሆኑን በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
















ለ20 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የሚያገለግሉ ግብአቶች ድጋፍ ተደረገ።

(ህዳር 11/2017 ዓ.ም) የግብአት ድጋፉ በ2017ዓ.ም በ20 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተቋቋሙ የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ለአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ከተመደበ በጀት በተፈጸመ ግዢ መሰራጨታቸውን ከቢሮው የልዩ ፍላጎት/ አካቶ ትምህርት ስራ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ድጋፉ የተለያዩ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ የሞንቶሶሪ ዕቃዎች በተለይም ለአይነስውራን እና መስማት ለተሳናቸው እንዲሁም የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ ዊልቸሮችና ክራንቾችን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት የቢሮው የልዩፍላጎት አካቶ ትምህርት ባለሙያው አቶ ፀጋዬ ሁንዴ ጠቁመው ግብአቶቹ 1,456,565 ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል።

ግብአቶቹ ለልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ተደርጎባቸው እንደመሰራጨታቸው ቢሮው በቀጣይ በየትምህርት ቤቱ በመገኘት ግብአቶቹ ለተገቢው አገልግሎት መዋላቸውን በድጋፍና ክትትል የሚያረጋግጥ መሆኑን የልዩ ፍላጎት የጎልማሶች እና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትግስት ድንቁ አመላክተዋል።


ከአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመጡ የሕፃናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ ቀኑን አስመልክቶ በህፃናት መብትና ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ ለህፃናት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ቀኑ የሚከበርበት ምክንያት ሕፃናትትን የማዳመጥ አስፈላጊነትና ሕፃናትን በማዳመጥ የምናገኛቸው ጥቅሞች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ነጥቦች የያዙ ሃሳቦች ተነስተው በህፃናቱ ውይይት ተደርጎበታል ::

በወቅቱ የህፃናትን መብት በምን መልኩ ማስከበር እንደሚገባ የሚያስተምር ጭውውትና የስነፅሁፋዊ ሥራዎች በተማሪዎች ቀርበዋል ::


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com














ህዳር 11 ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ::

(ህዳር 11/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን የስርዓተ ፆታ ዘርፍ "ሕፃናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው!" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ 19ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ሕፃናት ቀን በአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት አክብሯል ::

ቀኑን ስናከብር ለህፃናት መብት መከበር በጋራ መስራትና ለህፃናት እንክብካቤና ድጋፍ ማድረግ አለብን ያሉት የቢሮው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ ኢትዮጵያ የህፃናትን መብት ለማስከበር ዓለም አቀፍ ስምምነት የፈረመች ሀገር እንደመሆኗ የሕፃናትን መብት በማስከበር አድሎአዊ አሰራርን ለማስቀረትና በምቹ ቦታ የመኖርና የማደግ መብታቸውን ለማስከበር የትምህርት ተቋማት ድርሻ ትልቅ መሆኑን አብራርተዋል ::

አያይዘውም ለህፃናት መብታቸውን እንዲያውቁ ማስተማርና መሻታቸውን ማሟላት እንዲሁም ህፃናትን ለማዳመጥ ራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ይገባል ብለዋል ::

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ፋሲካ ወርቁ በበኩላቸው የሕፃናትን ቀን ከማክበር ባለፈ የህፃናቱን ሀሳብ በማዳመጥ የተሻለ ትውልድ ማፍራት የትምህርት ማህበረሰቡ ኃላፊነት በመሆኑ ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንወጣለን በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ::

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.