በተጨማሪም የአሰልጣኞች ስልጠናውን የሚወስዱ መምህራን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመመራት ስልጠናውን እንዲከታተሉና በሚፈለገው ልክ በመረዳትና የወሰዱትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች ለማስተላለፍ የሚያስችል አቅም እንዲያዳብሩ አሳስበዋል ::
በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴን በብቃት ለመምራትና ለመተግበር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዋናው መሳሪያ መሆኑን የተናገሩት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር በቅድመ አንደኛ ትምህርቱ ላይ በትኩረት መስራትና በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴን በብቃት ለመተግበር ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የመምህሩን ክህሎት ማሳደግና ማብቃት እንደሚገባ አብራርተዋል::
በከንቲባ ጽ/ቤት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ማስፋፊያ አማካሪ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን የቀዳማይ ልጅነት ትግበራ በአዲስ አበባ ይጀመር እንጂ ወደሌሎች ክልሎች ብሎም በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት እየተስፋፋ ያለ መሆኑን በመረዳት ሰልጣኞች በዚህ ደረጃ ለስልጠናው ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል ::
የአሰልጣኞች ስልጠናው በዋናነት የቀዳማይ ልጅነት ምንነትና አስፈላጊነት ፣ በጫወታ የማስተማር ስነዘዴ አተገባበርና ምቹ የመማሪያ አካባቢ መፍጠር ፣ እንዲሁም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ምንነትና የትምህርት አመራር ክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡ መምህራን አማካኝነት ለሁለት ቀናት የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል::
በአሰልጣኝ ስልጠናው የቢሮ ባለሙያዎችን ጨምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ አስተባባሪዎች የዘርፉ ቡድን መሪዎችና የቅድመ 1ኛ ደረጃ መምህራን እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc