ብስክሌት ጠጋኝ የነበረው የአሁኑ
ኮንትራክተር ጓደኛዬ እንዴት ሰለመ ??
===============
T.me//yeyasine_wedaje
ከጓደኝነታችን በፊት ክርስቲያን የነበረው ጓደኛዬ በጣም የሚገርም አስደናቂ ባህሪ እንደ ነበረው ከበፊት ጓደኞቹና ጎረቤቶቹ ሰምቻለሁ ። በፊት የነበረው መልካም ባህሪውና ቆራጥነቱ ዛሬ ላይ በእስልምና ውስጥ የበለጠ ውበት አጎናፅፎታል ።
_
ይህ ሰው ከጎረቤቶቹ መካከል አንድ እግረ ሽባ የሆኑ ሙስሊም ሰው ነበሩ ። እኚህ ሰው ሁሌም ባይሆን ለጁምዓ ሰላት ከመስጅድ አይቀሩም ነበር ።
ይህ ጎረቤቱ አርብ አርብ ሁሌም እየተንፏቀቁ ወደ መስጅድ ሲሄዱና ሲመጡ ሲመለከት በውስጡ ያስጨንቀው ጀመረ ።
_
አንድ ቀን በውስጡ ይህን ሰው በብስክሌቱ ወደ መስጅድ ማድረስና ከሰላት ቡሃላ ጠብቆ መመለስ እንዳለበት ወሰነ ። ይህን ሀሳብ ለሰውዬው ሲያማክራቸው እሳቸውም በጣም በመደሰት ዱዓ አድርገውለት በሀሳቡ ተስማሙ ።
_
የመጀመሪያውን ጁምአ ለሰላት አድርሷቸው ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ ሆኖ ከኹጥባ በፊት በሼኽ ኢብኑ ዩሱፍ የሚደረገውን የኹጥባ ተፈሲርና በኢማሙ እርጋታ የሚነበበውን የአርብኛ ኹጥባ በድምፅ በማጉያ ሲያዳምጥ የማያውቀው ስሜት ልቡን ተቆጣጠረው።
_
የሁለተኛው ጁምዓ እስኪደርስ ጨነቀው ቀኑም ደረሶ የመስማት እድል አግኝቶ አዳመጠ እንዳባለፈው ጁምዓም የሰማው ነገር ሁሉ ልቡን አሸብሮታል ። ጉዳዩ ወደ ሌላ ምእራፍ ተሻገረ ። ደገመ ደጋገመ ። ደካማን በመርዳት እዝነት የጀመረችው ልቡ የአላህንና የሩሱለላህን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ለመስማት በፍቅር ተጠለፈች ።
_
የተወሰነ ሳምንታት ከተመላለሰ ቡሃላ እሱን ወደ መስጅድ እንዲመላለስ ሰበብ የሆኑት ሰውዬ በሁለት ጁምዓ መሃል ወደ አኺራ ሄዱ ።
_
ይህ ሰው ውስጡ ሀዘን ቢኖርም በየጁምዓው ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ በመሆን ውስጡን የማረከውን ኹጥባ ለማዳመጥ መመላለሱን አላቋረጠም ።
_
አንድ ቀን ለይለተል ጁምዓ በመናም በህይወቴ አይቼ ማላውቀው በጣም የሚያምር ሰው እጄን ይዞ መስጅድ አብረን ገባን ኹጥባም ሰማሁ ሰላትም ስግጄ ከመስጅድ እየወጣን ሳለ ከእንቅልፍ ነቃሁኝ የመጀመሪያው የሱብሂ አዛን ወአሽሃዱ አነ ሙሀመደን ረሱለላህ እያለ ነበር የነቃሁት ።
_
ታዲያ ይህንን መናም ለማስፈታት ማንም ጋር መሄድ አልፈለገም የጁምዓ ሰላት ወቅትን ጠብቆ እንደበፊቱ ሰው ሊያደርስና ኹጥባ ሊሰማ ሳይሆን ከሙስሊሞች ጋር
የሚቀላቅለውን ሰው ለመፈለግ ነበር የወጣው ።
_
በመጨረሻም ከሰፈራቸው አንድ ሻይ ቤት የነበረው መሀመድ የሚባል ሰው ጋር በመሄድ ወደ መስጅድ ይዞት እንዲሄድ ሲጠይቀው ሙሀመድም በመጀመሪያ ሸሃዳ
መያዝ እንዳለበት ይነግረዋል ።
_
እሱም ሸሃዳ ምንድነው ቢለው > ብለህ ትመሰክራለህ ሲለው ይህንንማ ማታ ያ ሚያምር ሰው አስብሎኛል ብሎ ማታ ያየውንና የሰማውን ነገረው ።
_
ሙሀመድም እየተገረመ ወደ መስጅድ በመውሰድ ከኡለሞች ጋር በማገናኘት የነገረውን ሲነግራቸው ኡለሞቹም እኛ ረሱለላህ ያሰለሙትን ሰው ደግመን አናሰልምም ባይሆን ደስ እንዲለን እስቲ ያሉህን ንገረን አሉት ።
_
ጓደኛዬም የመጨረሻውን ምእራፍ እነዚያ ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ ሆኖ በፍቅር ምክራቻውን ሲሰማ ልቡን በፍቅር ያሸበሩትን ኡለሞችን ፊት ፊታቸውን እያየ የሰማውን ሸሃዳ ለኡለሞች አስደምጦ …………… ገቢ ሆነ ።
_
በሰአቱ ቦታው ላይ የነበሩት ኮሚቴዎች ህዝብ ፊት ቆሞ መስለሙን እንዲገልፅና ህዝቡም የደስታ መገለጫ ስጦት እንደሚሰጡት ሲነግሩት እሱ ግን መስለሜን መናገር እችላለሁ ። ግን ስጦታ ያላቹትን ግን ማርያምን አለፈልግም ሲል የኮሚቴዎች ሳቅ መልሶ እሱንም አስቆት እስላምን መኖር ከጀመረ ይኸው ሁለት አስር አመታቶች አለፉት ።
==============
_
ረሱለላህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰዎችን ወደ ኢስላም ያስገቡት በዳእዋ ፣ በዱዓ ፣ በኢክራም ፣ በኢኽላስና በአኽላቅ ሲሆን አብዛኛው ሶሀባ ኢስላምን የተቀበሉት በአኽላቃቸው ነበር ።
_
ኢማናችን፣ተቅዋችን ፣ኢኽላሳችን፣እንዲሁም ኢባዳዎቻችንን ለሌሎች አይታያቸውም ነገር ግን አኽላቃችንን ነው የሚመለከቱት ።
አላህ ያግራልን !!
Jan 31 2020
@yasin_nuru @yasin_nuru