#ትምህርቶች᎗ለባለ᎗ትዳሮች
⓵ ልክ እንዳገባሀት የሚስትህ የፊት በኩል ራስ ላይ እጅህን አድርገህ ይህንን ዱአ አድርግ
"بسم الله اللهم إني أسألك من خيرها وخير ما جبلتها عليه وأعوذ بك من شرها وشر ما جبلتها عليه"
⓶ አዲስ ተጋቢዎች አብረው ሁለት ረከአ ሰላት ሊሰግዱ ይወደድላቸዋል
➠ይህ ተግባር ከሰለፎች የተረጋገጠ መሆኑን ሸይኽ አልባኒ አዳበ ዚፋፍ ኪታባቸው ላይ ይጠቅሳሉ
⓷ ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ የሚባል ዱአ
"بسم الله اللهم جنبنا الشيطان وجنب الشيطان ما رزقتنا"
⓸ በአንድ ለሊት ከባለቤቱ ጋር ተገናኝቶ ድጋሚ አሁንም ሊገናኛት ከፈለገ በመሀል ውዱእ ማድረግ ይወደድለታል።
➠ኡዱ ማድረጉ ለግንኙነቱ ነሻጣ እንደሚሰጣቸው ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ ተጠቁሟል።
⓹ ቢታጠብ ደግሞ የበለጠ የተወደደለት ይሆናል ምክንያቱም ከመልእክተኛው በየግንኙነታቸው መሀከል መታጠባቸው ስለተገኘ
⓺ ባል እና ሚስት አብረው በአንድ ቦታ እየተያዩ መታጠብ ይፈቀድላቸዋል
➠አኢሻ እና መልእክተኛው በዚህ መልኩ ይታጠቡ ነበረ
⓻ ከባለቤቱ ጋር ተገናኝቶ በዛው መተኛት የፈለገ ሰው ውዱእ አድርጎ ቢተኛ ይወደድለታል
➠ግን ይሄ ውዱ ግዴታ አደለም ሳያደርግ ቢተኛም ወንጀል አይኖርበትም
➠ታጥቦ ቢተኛ ግን ከሁሉም በላጭ ይሆንለታል
⓼ አንዳንድ ግዜ በውዱ ፋንታ ተየሙም አድርጎ ቢተኛም ይችላል
⓽ ሚስቱ የወር አበባ ላይ ሆና ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም ከባድ ወንጀል ነው
➠ነገር ግን በብልቷ ከመገናኘት ውጪ ባለ ሁኔታ ከሷ ጋር እንደፈለገ መጠቃቀም ይፈቀድለታል
⓾ የማታ ሚስጥራቸ ለሰው ማውራት ከባድ ወንጀል ነው
➠ባልም ይሁን ሚስት በግኑኝነት ግዜ ያለ ሚስጥራቸውን ለማንም መናገር የለባቸውም
✍ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን)
✍
https://t.me/ye_Sunnyi_Setochi_Medrek 🌹كوني سلفية على الجادة🌹