ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_20
....ሰውዬው ነበር እሱ ነገር ግን አልተመለከተኝም ነበር...ወደ ውስጥ ሲገባ ውጪ ላይ አንዳች የረሳው ነገር ያለ ይመስል ወደሗላ እየተመለከተ ነበር እኔም ይሄን ቅፅበት ተጠቅሜ ተደብቄ ወደ ነበረበት ስርቻ ተመለስኩ ግን ወደ ውጪ ሲመለከት የነበረው ሰውዬ ወዲያውኑ ከውስጥ አንዳች ነገር በልቡን የሳበው ይመስል በፍጥነት ዞረ ይመስለኛል ስደበቅ ያሰማሁት ኮሽታ ነው...ለደቂቃዎች በአፍንጫው እያነፈነፈ ቤቱ ውስጥ የገባውን እንግዳ ነገር ማሰስ ጀመረ ቅርቤ ስለነበር ይበልጥ ሰውዬውን መመልከት ቻልኩኝ ሁለቱም አይኖቹ ትክክል አይደሉም አቀማመጣቸውም ይለያል ከአይኖቹ ይልቅ አፍንጫውን አብዝቶ ይጠቀምበታል ነገር የአይኑ ብሌኖች ምስል ይከስቱ አይከስቱ እንጃ...በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰውዬውን እየተመለከትኩት ሳለ በዕድሜ አነስ የምትለዋ ሴት "ለምን እዚጋ ቆም አንድዬ" አለችው በማይገባ ቋንቋ የሆነ ነገር ብሎ መለሰላት "ምንም የለም ሁሉም ሰላም ነው እናትህ እንደ ድሮው ፀጉርህን ልታበጥርልህ ነው ና ወደ ውስጥ እንግባ" አለችው እያባበለችና የሚወደውን ነገር እየነገረችው እሱም በሃሳቧ ተስማምቶ እቅፍ አርጓት ወደ ውስጥ ገቡ...ውስጤ ለሰውዬው እንደ ማዘን አረገው በሆነ አንዳች ክፉ ክስተት እና ገጠመኝ ለዚ እንደተዳረጉ ለማሰብ ሰከንድ አልፈጀብኝም "ብቻ ከዚ በፊት መልካም ቤተሰቦች የነበሩ እሱም መልኩና አስተሳሰቡ ልቡም ጨካኝ ሳይሆን ሩሩህ ሰው ነበር" እያልኩኝ ከራሴ ጋር ስለ ሰውዬው መነጋገር ጀመርኩ ከዛም ከተደበኩበት በጥንቃቄ ተነስቼ ከኔ ቀጥሎ የሚከሰተውን ትዕይንት ወደሚያሳየኝ የመጋረጃ ሽንቁር ተጠጋሁ ወዲያውኑ ትልቋ ሴትዮ ባለመደገፊያ የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጣለች እሱ ደግሞ አነስተኛ ወንበር ላይ ጀርባውን ሰጥቷት እግሯ መሃል ተቀምጧል በያዘችው ማበጠሪያ ሉጫ ፀጉሩን ወደሗላ በማበጠሪያ ታስተኛዋለች አንዳች አትናገርም ቃልም አይወጣትም ነገር ግን ከአይኗ የሚፈሰው እንባ ከእልፍ ድምፅ አልባ ቃላት የበለጠ ይናገራሉ በሚወርደው የእንባዋ ቦይ ላይ ብዙ ብሶቶቿ እና ችግሮቿ በግልፅ ይነበባሉ ፊቷ እንኳን እንደሚያለቅስ ሰው አልተኮማተረም አልተጨማደደም የማትናገረው ውስጧ ሚብሰለሰል እያደር ሚበላት ግን የማታከው አንዳች ነገር እንዳለ አሰብኩኝ..."አንዳንዴ ጥፍር ደርሶ የማያከው ቆዳ ስጋና አጥንትን አልፎ ከውስጥ የሚበላ ክፉ እከክ" አለ አልኩኝ ለራሴ ደሞም ልክ ነበርኩ በሴትየዋ ሁኔታ ከገባሁበት ሰመመን ስነቃ ሳላስበው ጉንጬ በእንባ ርሷል በጣም ደነገጥኩኝ ግራም ተጋባሁኝ እንዴት ሊሆን እንደቻለም ለራሴ ገረመኝ ግን በቃ ሆነ ልቤ እና አይኔ ተስማምተው በአንድነት አዘኑ በእንባዬም ገለፁት..."ግን የእውነትም እጅግ ያሳዝናሉ አንጀትም ይበላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ስጋ ይበላሉ እዚህ ቤተሰብ ላይ የተከሰተው አንዳች ክፉ ገጠመኝ ምን ሊሆን ይችላል እንዴትስ ሊሆን ቻለ" እያልኩኝ ራሴን መጠየቄን ተያያዝኩትን ከራሴ ንግግር ተመልሼ በድጋሜ አይኔን በመጋረጃው ሽንቁር ወደ ውስጥ ሰደድኩት ትልቋ ሴትዮ ፈትል የሚመስለው ነጭ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ተንጋሏል ከፊት ያለው የፀጉሯ ክፍል አልፎ አልፎ ጥቁር ጣል ጣል ብሎበት የተለየ ውበት ሰጥቷታል ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ማበጠሯን ተያይዛዋለች አነስ የምትለዋ ሴትዮ ግን ሰውዬውን ካስገባች በሗላ ደግሜ አልተመለከትኳትም ከነሱጋ አለመሆኗ ቢያስገርመኝም "ለምን" ብዬ ምጠይቀው ሰው የለ ግን ከአይኔ መሰወሯን አልወደድኩትም ውስጤ ተረብሿል... ነገር ግን ቀልቤ አሁንም እናትና ልጁ ላይ ነው...ከዛም እሱ በተራው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ ውሃና የእግር መታጠቢያ አምጥቶ ቀስ እያለ አጠባት ከዛም ቅባት ነገር ይመስለኛል አነስቶ ከእናቱ ትይዩ ባለው የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጦ በእርጋታ ያሻት ጀመር እሷም ፈገግ እያለች አይን አይኑን ትመለከተዋለች ነገር ግን አሁንም አይኗ ከማንባት አልቦዘኑም ነበር ያለመታከት ያነባሉ የእግር ጣቶቿን አንድ በአንድ እያረገ ዘና እንድትል የተቻለውን ይጥራል ደግሞም ከተቀመጠበት ተነስቶ ጉንጯ ላይ ሚንከራተተውን እንባ በመዳፉ ጠርጎ ግንባሯን ይስማታል...ምን አለ አንዳች ነገር ተከስቶ ወደ ቀድሞው በመለስኳቸው ብዬ ተመኘሁ...እዚ ቦታ ላይ ከዚ በላይ መቆየት እንደሌለብኝ ግልፅ ነው ቶሎም ተመልሼ ጓደኞቼን ከዚ አካባቢ ይዤ መሄድም እንዳለብኝ ግልፅ ነው...የውስጡን ትዕይንት ከምከታተልበት የመጋረጃ ሽንቁር አይኔን አንስቼ ወደ በሩ ስዞር አነስ ምትለዋ ሴትዮ................
Part 21....ይቀጥላል.........
ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱