🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 1️⃣4️⃣
እነሱም ጊዜ ሳያጠፉ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወሰዱት 40 እንኳን እስኪያለፍ መጠበቅ አልቻሉም አንድም ቀን የት ወደቀሽ የት አረፍሽ ምን ጎደለሽ ምን እናግዝሽ ሳይሏት የኖሩት ለምን እንደሆነ ፀባያቸው አሁን በደንብ ተገለጠልኝ።
ግን ያላወቁት ነገር እናቴ ድሮ ገና ቤቱን በኔ ስም እንዳደረገችው ነው።
ልክ ይሄንን ሲሰሙ ሁሉም ድራሻቸው ጠፋ ጎረቤት አርባዋን ደገሰላት።
አርባዋ ካለፈ ቡሀላ ለእናቴ ጥቁር ልብስ የለበስኩላት እኔ ብቻ ነበርኩ እና ልእልት።
በእናቴ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ፋኖስ አንዴ እንኳን እግዚአብሔር ያፅናህ ለማለት አለመምጣቷ የጭካኔዋ ጥግ ምን ድረስ እንደሆነ እንዳቀው አደረገችኝ ።
ምንም ቢሆን በእጇ በልታ ጠጥታ ተሳስቃ ስንት ነገር አብረው አሳልፈው እሷ ወዳፈር ስትገባ ጠያቂ ማጣቷ አሳዘነኝ።
ሳሎን ቁጭ ብዬ ፊት ለፊቴ ከተቀመጠው የእናቴ ፎቶጋ እየተያየሁ አይ እማ የሰውን ልጅን ጭካኔ ያረጋገጥኩት አንቺም ጥለሽኝ ስቴጂ ነው።
እራስሽ ከሰው ሸሽገሽ ብቻዬን አሳደግሽኝ እራስሽ ደሞ ብቻዬን ትተሽኝ ሄድሽ እማ ግን አላሳዝንሽም መኝታ ቤትም ስገባ ያለሽ ይመስለኛል ሳሎንም ቁጭ ስል ከጎኔ አረፍ ያልሽ ያክል ነው ሚሰማኝ ብቻ ቤት ውስጥ ሁሉም ቦታ እንዳለሽ አስባለሁ ግን ጠረንሽኝ ላንዴ ማሽተት አንቺን ማቀፍ እነዛ ጉንጮሽን የሳምኩሽ እያስመሰልኩ መንከስ እፈልጋለሁ እማ ስላንቺ ሳስብ ማበድም እፈልጋለሁ መጮህም እፈልጋለሁ ግን የተኛውም ነገር ልቤን አያሳርፍልኝም ደሞኮ እኔም ሞቼ ሰማይ ቤት ቸገናኝቸን እስከዘላለም አብረን እየተያየን መኖር ብንችል ፈጣሪ ምስክሬ ነው እማ ምንም ሳላቅማማ አሁኑኑ ነበር ምሞትልሽ ........
ብቻዬን እየለፈለፍኩ ልእልት ከውጪ ምሳ ይዛ ገባች ።
ቀና ብዬም አላየኋትም እኔ ከእናቴ ፎቶ ላይ አይኔን ማንሳት አልቻልኩም።
ምሳ ብላ ገና ባንድ ወሩኮ የጉንጮችህ አጥንት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል አለች።
አወራሯ ልዝብ ያለ ስለነበር አናደደኝ።
ዞሬ ተመለከትኳትና ቆይ እዚህ ምድር ላይ የተፈጠረች ንፁህ ሴት እማዬ ብቻ ነች እንዴ ሁላችሁም መጀመሪያ ላይ ማስመሰሉንና እንደንፁህ መታየቱን ተክናችሁበታል ምን ይለጥጥሻል ጮክ ብለሽ አታወሪም ደሞ ምናገባሽ ስለኔ ምሳስ እኔ አምጭልኝ ብዬሻለሁ በቃ ንዴቴን በሷ ላይ መወጣት ብቻ ነው የፈለኩት ያመጣችውኝ ምግብ መሬት ላይ ደፋሁት ትቻት ልወጣ ስል ተከተለችኝና እቴቴኮ ወረቀት አስቀምጣልህ ነበር ሲረጋጋ ስጭው ብላኝኮ ነው አለችኝ።
እቴቴ ሚለውን ስም ስሰማ ነዘረኝ የታለ ስጨኛ ልእልት በናትሽ የታለ እሷ ናት የፃፈችልኝ እእ ስጪኝ እስቲ ምን አለችኝ ላንበበው አልኳት ወዲያው በእጇ ጨብጣ የያዘችውን ወረቀት ሰጠችኝ።
እየተጣደፍኩ ሶፋው ላይ ቁጭ ብዬ ወረቀቱን ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ።
እንዲህ ይላል...
የኔ ልጅ የኔ ብቸኛ በጣም ነው ምወድህ ልጄ እንደሰው ታድዬ በሆነና ላንተ ብዙ እህቶችና ወንድሞችን ወልጄልህ ብቻህን ከመሆን ብታደግህ ደስ ይለኝ ነበር እኔም ብቸኛ ሆኜ ብቻህን አስቀረሁህ ..
የኔ ልጅ እኔ አንተ ባትኖርልኝ እንዴት ብዬ እስካሁን እንደምኖር አላቅም ነበር በየትኛውም ሰአት ብርታቴ ነህ ለኔ ዘመዴም ልጄም አባቴም ብቻ ሁሉ ነገሬ ነህ።
በሀኪሞች የተነገረኝ ወሬ አስከፊ ነው ልጄ ታምሜብሀለሁ ብቻህን ትቼህ ልሄድ ነው አደራ አደራ እራስህን እንዳትጥል ልዕልቴ እንደናትም እንደህትም አንተ ከፈቀድክ እንደሚስትም ትሆንልሀለች ደና ሁን የመጀመሪያ ልጅህን በኔ ስም ሰይማት እሺ....
አቃተኝ ከዛ በላይ ማንበብ መታመም አልቻልኩም ልቤ ላይ አፍኖ ያዘኝ ተነስቼ ከቤት ወጣሁ ልእልት እስከውጭ እየሮጠች ተከተለችኝ ድጋሜ ስዞር ከጀርባዬ ካገኘኋት እንደምንጣላ ነገርኳትና እኔ መንገዴን ቀጠልኩ።
እናቴን ሚመስሉ ወፈር ወፈር ያሉ ሴቶችን ለማየት እንዲመቸኝ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩና ከበሩ እራቅ ብዬ ቆምኩ ልክ እንደናቴ ደምቦሽቦሽ ብለው ፀየም ያሉ ሰዎችን ሳይ ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ካይኔ እስኪሰወሩ እመለከታቸዋለሁ።
ይቀጥላል...
🔻ክፍል1️⃣5️⃣ ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔