🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ኢላሪ (እውነተኛ ታሪክ) ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ህሊና
ክፍል 1️⃣4️⃣
ምን እንደሚለኝ እያሰብኩ ያለኝ ቦታ ደረስኩ። ልዑል ብቻውን ቁጭ ብሏል ወደ እርሱ ሄጄ ሰላም ተባብለን ቁጭ አልን።አንዳንድ ነገሮች ካወራን በኃላ ለምን እንደፈለገኝ ጠየኩት።ተስተካክሎ ተቀመጠ እና ...ይኸውልሽ ኢላራ ላወራሽ ካሰብኩ ትንሽ ቆየው ግን ነገሮች ተደራረቡ እና ደግሞ አንዳንድ ነገሮችኝ በደንብ ልይ ብዬ ነው።...ምንድ ነው እሱ ልዑል..ኢላሪ ያው ታውቂያለሽ ጓደኝነታችን እንደድሮ እንዳልሆነ መሀላችን ያልሆነ ነገር ተፈጥሯል አላውቅም ፈጣሪ በጓደኝነታችን ሊፈትነን ይሁን ትግስታችንን ሊያይ ፈልጎ ይሁን አላውቅም ለምን ይሄ እንደሆነ።
ኢላሪ ሁለት የምወዳቸው ወንድሞቼን እያጣው ነው።አንቺም አንዷ ጉአደኛሽን እያጣሽ ነው...ማለት ማንን ነው ማጣው..ሀኒን ነዋ...ሀኒ ስትል ..ኢላሪ ሀኒ ዳንን እንደምታፈቅረው አውቃለው..ማለት እንዴት...ኢላሪ እኔ ለሀና የብዙ ጊዜ ጉአደኛዋ ነኝ እና ስሜቱዋን እረዳለው እና አሁን ሀኒ ደህና ልትመስል ትችላለች ግን ደህና አይደለችም።
ቆይ ታዲያ ብዬ ላወራ ስል አቋረጠኝ...ኢላሪ ቆይ እኔን አዳምጭኝ አሁን የምጠይቅሽን ነገር ሳትደብቂ ንገሪኝ..እሺ ምንድ ነው...ከዳን ወይም ከእዮባ ፍቅር ይዞሻል ደንግጬ ዝም አልኩት።... እባክሽ ኢላሪ መልሽልኝ ከሁለት አንዳቸውን በተለየ አስተያየት የምታይው አለ።...ቆይ ልዑሌ ከአንዳቸው ፍቅር ከያዘኝ ችግር አለው።
ኢላሪ ይቅርታ ግን አለው አንዴ ከያዘሽ ተይ ማለት አልችልም ግን ባይሆን ደስ ይለኛል።ካልሆነ ግን ጉአደኞቻችንን ሲል አስቆምኩት..ከማናቸውም ፍቅር አልያዘኝም አትስጋ እሺ አልኩት...ኢላሪ የምርሽ ነው...አዎ ግን እዮባና ዳን አያወሩም እንዴ...ያወራሉ ግን እንደድሮ አደለም ፈልገውት አይደለም ታውቂያለሽ ሁለቱም ራሳቸውን ጥፋተኛ እያደረጉ ስለሆነ ነው።...እሺ ልዑሌ ወደ ድሮ እንዲመለሱ ምን ላድርግ።
ኢላሪ ዋና እሱን ላማክርሽ ነው የጠራሁሽ።ሁለቱንም በየተራ ታወሪያቸዋለሽ ምን ብለሽ እንደምታወሪ መናገር አይጠበቅብኝም አይደል...አዎ አውቃለው ግን መቼ እና የት...እሱ ለኔ ተይው ብቻ ስደውልልሽ መምጣት ነው አለኝ።
እሺ ብዬ ተሰናብቼው ወደ ዶርም ሄድኩኝ።ምንም ሳልል ገብቼ ነጠላ አውጥቼ ይዤ ልወጣ ስል ማኪ ..ወዴት ነው አለችኝ...ቤተክርስቲያን አልኳት ...አብረን እንሂድ እሺ ብዬ እኛ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ሌሎቹ ካፌ ሄዱ።ልክ ቤተክርስቲያን ስደርስ ከማኪ ራቅ ብዬ እንባዬን እንደጉድ አዘራውት።
ደጃፉን ተምበርክኬ ብሶቴን አወጣሁት።ሳለቅስ የእዮባ ፍቅር በውስጤ እንዳለ ታወቀኝ።አምላኬ እባክህ እዮብን አትንሳኝ ከዚህ ፈተና አውጣኝ ፈጣሪዬ በፍቅር አትፈትነኝ እያልኩ አነባውት።የአያቴም ሀዘን አልወጣልኝም መሰል እሱዋንም እየጠራው እሲኪበቃኝ አለቀስኩ።
ካጎነበስኩበት ቀና ስል የሆነ ልጅ በትኩረት እያየኝ ነው።ምንም ሳልል አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ።ማኪ ጋር ልቀመጥ ብዬ ያለቀስኩበት አይኔ ትንሽ ይልቀቅ ብዬ ለብቻዬ ቁጭ አልኩ።ትንሽ ቆይቼ ብድግ ብዬ ልሄድ ስል ልጁ እጄን ነካ አድርጎ እናት አለኝ።ዞር ብዬ አቤት አልኩት።...ይህውልሽ ምንም ሆንሽ ምንም በፈጣራ እና በፍቅር ተስፋ እንዳትቆርጪ እሺ...ማለት ፍቅር ስትል...ያው ባለሽበት እድሜ ዋናው መከራ ፍቅር ነው ብዬ ነው...እሺ አመሰግናለው ብዬ ማኪኝ ጠርቻት ወደ ጊቢ ተመለስኩ።
ቀጥታ ወደ ካፌ ሄድን።ምግብ አልበላ አለኝ ምግቡን ትቼ ማኪያቶ መጠጣት ጀመርኩ።ውስጤ ደህና አይደለም ህመም እየተሰማኝ ነው ግን ሄጄ ልተኛ ብል ይደብራቸዋል ብዬ ዝም አልኩ። የሆነ ሰዓት ግን ብዥ እያለብኝ መጣ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ እጄ መኝቀጥቀጥ ጀመረ።ድምፅ ይሰማኛል ግን ምን እንደሆነ መለየት አቃተኝ።አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ይታየኛል ዞር ብዬ ስመለከት ክሊንክ መሆኑን ተረዳው።
አንድ ነርስጨ..ደህና ነሽ አለችኝ...ምንድ ነው ብዬ ጠየኳት...ራስ ስተሽ ወድቀሽ አምጥተውሽ ነው አይዞሽ ትንሽ እረፊበት ብላኝ ወጣች።ልክ እንደወጣች ጉአደኞቼ ተከታትለው ገቡ።እዮባ ዳኒና ልዑልም ነበሩ።ስትታመሙ ሚጨነቅላቹ ወይም አጠገባቹ ሰውን እንደማየት ደስ የሚል ነገር የለም።
ሁሉንም ደህና ነኝ ካልኩ በኃላ ልዑል አጠገቤ መቶ ..ደህና ነሽ አለኝ።...አዎ ልዑሌ ደህና ነኝ ግን ይበልጥ ደህና እንድሆን ግን ከእዮባ እና ከዳን ውጪ ውጡ ሁላችሁም አልኳቸው እሺ ብለው ወጡ።ልክ እንደወጡ ዳን ...ደህና ነሽ አለኝ እኔም ከተኛውበት ብድግ ብዬ...አይ አይደለውም አልኩት።እዮባም ቀበል አድርጎ...እና ዶክተር እንጥራ አለ...ይሄ ህክምና አያስፈልገውም እባካችሁ ደህንነቴን የምትፈልጉ ከሆነ ዝም ብላቹ አድምጡኝ።
እዮባ ዳን ላንተ ምንህ ነው አልኩት እዮባም...ዳን ለእኔ ወንድሜ ነው አለኝ።...እሺ እዮባ አንተስ ዳን...ለእኔም እዮብ ወንድሜ ነው።...እና አሁን ወንድምነታችሁ የት ሄደ ንገሩኝ ማናችሁም ምን አይነት ጥፋት አላጠፋችሁም እናም ለማንም መስዋት መሆን አይጠበቅባችሁም እሺ ምክንያቱም ሁለታችሁም ከተሳሳተ ሰዎ ነው ፍቅር የያዛችሁ።ስለዚህ ይሄን አውቃችው ወደ ድሮ ወንድምነቻችሁ ትመለሳላችሁ ከኔጋርም እስከዛሬ ባላችሁ የጉአደኛ ቅርበት እንቀጥላለን ከዛ በጣም ደህና እሆናለው።
ይሄን እንዳልኩ ዳን ክፍሉን ለቆ ወጣ።እዮባም ወደ እኔ ጠጋ ብሎ...መቼም መቼም ኢላሪ አንቺኝ እንደጉአደኛ ተቀብዬሽ አላውቅም መቀበልም አልችልም ብሎኝ እሱም ጥሎኝ ወጣ።
ዛሬ ክላስ ጠዋት ነበረኝ ግን መግባት ስላስጠላኝ ለጓደኞቼ እንደማልገባ ነግሪያቸው ለሚኪ ደውዬ መቶ ከዚ ጊቢ እንዲወስደኝ ነገርኩት።ልክ እንደመጣ ሲነግረኝ ተነስቼ ወጣሁ።ከጊቢ እየወጣው ከቤዛ ጋር ማለት ከአቤል አፍቃሪ ተገጣጠምን።ፈገግ ብዬ ሰላም ልላት ስል ግልምጥ አድርጋኝ ሄደች።ምን ሆና ይሁን ብዬ ዝም ብዬ ሄድኩኝ።በር ላይ ማይኮ መኪናውን ተደግፎ ቆሙአል።አቅፌ ሰላም አልኩት።ማይኮ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው እሱን ሳገኘው ሰላም ይሰማኛል ወንድሜም አይደል😘 ሰላም ካለኝ በኃላ ምን ሆነሽ ነው ብሎ ጠየቀኝ....ምንም ብቻ ከዚህ ቦታ ውሰደኝ...እሺ በይ ግቢ አለኝ ወደ መኪናው ገብተን መንገድ ጀመርን። ..የት ልውሰድሽ ልዕልቴ አለኝ ማይኮ እና እናቴ ከድሮ ጀምሮ ልዕልቴ ነው ሚሉኝ እኔም የእውነት ልዕልት የሆንኩ ነው ሚመስለኝ።
የፈለክበት ውሰደኝ ደስ ያለክ ቦታ ...እሺ የእኔ አኩራፊ ብሎ ፈገግ አለ።ከትንሽ ጉዞ በኃላ የሆነ ቦታ ጋር ደረስን።አንድ የማያምር ጭር ያለ ቦታ ሆኖ ካፌ አለው።ብዙ ሰው እንዳየሁት ከሆነ ቁጭ ብሎ ለማንበብ ይጠቀምበታል።እኔና ሚኪም ገብተን ቁጭ አልን።ሁለታችንም ማኪያቶ አዘን ማውራት ጀመርን።
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል 1️⃣5️⃣ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔