"ታመሀል ይለኛል ሀኪም"
_____
ህመሜ እንደሌሎቹ መስሎት እራስ ምታት
መስሎት ሙቀት መጨ
መር ትኩሳት ነ
ገር መስሎት፤
.....
ስንቱን መድሀኒት ሲያዝ ስገዛ የታዘዝኩትን
ምንም ለውጥ ላላይበት ስወስድ የተባልኩትን፤
......
እንኳን ሊሻለኝ ይቅርና ደህን ልሆን እንደ በፊት
እየባሰብኝ መጣ ለምን እንደሆን እንጃለት፤
.....
ታመህ ነው ይለኛል ሀኪም ጤናህ አልተመለሰም
እየጨመረ ነው እንጂ ምንም ሊቀንስ አልቻለም
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም፤
.....
መች ምልክቱን ነግሬው እንዴት እንደሚያደርገኝ
የውስጤን መች አየውና ሁሌ ታመሀል የሚለኝ፤
.....
አያተኩስም ግንባሬ ሙቀቴም ገና አልጨመረም
እራስ ምታትም የለብኝ ደም ብዛት ግፊት ስኳርም፤
.....
የራሴን ህመም የማውቀው እኔው ሆኜ ከሱ በላይ
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም ላይረዳው የኔን ስቃይ፤
.....
ላያውቅ ፍቅር ማጣቴን ከደስታ ሀሴት መራቄን
ላያውቅልኝ ሰው ማጣቴን አንድነትን መናፈቄን፤
.....
ችግሬ ሌላ ሆነና ለየት ያለ ከሌሎቹ
ሁልጊዜ መጠየቄ በዝቶባቸው ቢሰለቹ፤
.....
አሉኝ ጭራሽ ይህ እብደት ነው ጨመር አርገው ከትኩሳት
አብሰውት ከደም ብዛት ከደም ግፊት ከራስ ምታት፤
......
ጤንነትህ ልክ አይደለም አይምሮህ ትንሽ ተነክቷል
ህመምህ ድንበር ተሻግሯል በቃ አንተ ልጅ አብደሀል
#ይለኛል ሀኪሙ ታመሀል፤
.....
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም ጤንነትህ ልክ አይደለም
ለህመሞችህ መድሀኒት በጭራሽ እኔጋር የለም፤
.....
ይለኛል እብድ መስዬው ተለይቶበት ህመሜ
ሳይገባው የኔ በሽታ ፍቅር እንደሆን ጥሜ ፤
.....
ጥላቻ ነው የኔ ጠላት ጥላቻ ነው የኔ ህመም
ትኩሳት ሙቀት መጨመር እራስ ምታትም አይደለም፤
....
እብደትም ከቶ አይደለም የአይምሮ መሳት ችግር
በሽታዬ ጥላቻ ነው የኔ ህመም ማጣታት ፍቅር፤
....
መለያየት ነው ህመሜ መራቅ ከምወዳቸው
እስክገናኝ ከውዶቼ ወዳጅ የኔ ካልኳቸው፤
....
አይቀንስም በሽታዬ ህመሜም አይድንም ከቶ
እንዲህ አድር ባይነት በልባችን ተንሰራፍቶ፤
...
ጥላቻችን ተባብሶ አንድነታችን ደፍርሶ
መተማመን ተመናምኖ መከባበራችን ቀንሶ ፤
...
እንዴት ይሻለኛ ከቶ
ጥላቻችን ወደር አጥቶ፤
...
ልይገርህማ ሀኪሙ የኔን ህመም መድሀኒት
ፍቅር ደስታ መተሳሰብ እኩልነት አንድነት
መከባበር አብሮ መኖር ማጠናከር ወዳጅነት
የጥላቻችን ማርከሻ እኚህ ናቸው መድሀኒት፤
...
ያኔ ይሽራል በሽታው እብድ መባሌም ያበቃል
ጨለማው ፊቴ ይፈካል ዝም ያለው ጥርሴም ይስቃል፤
...
ይሽራል ያኔ በሽታው ይሄ የልቤ ህመም
እስከዛው ግን ቀን እስኪያልፍ
#ታመሀል አትበለኝ ሀኪም፤
__
@yene_gtm
@yene_gtm
✍✍fethi 🧔