ምን ነካሽ ?!
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?
ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።
እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።
እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፫ ዓ.ም
@yene_gtm
@yene_gtm
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?
ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።
እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።
እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፫ ዓ.ም
@yene_gtm
@yene_gtm