ከሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ የስራ እድል ያገኘው የ7 ዓመቱ ህጻን
የሰባት አመቱ ኮዲንግ ባለሙያ ሰርጌይ ከሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ ፕሮ32 አስተዳደር ቡድንን እንዲቀላቀል የስራ ግብዣ ቀርቦለታል፡፡
ታዳጊው ‘የኮዲንግ ሞዛርት” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ሲሆን በዩቲዩብ ላይ በሚያቀርባቸው የፕሮግራሚንግ የማስተማሪያ ቪዲዮዎች ታዋቂነትን ያተረፈው ሰርጌይ በኮዲንግ ብቃቱ እና በማስተማር ችሎታው አድናቆትን አትርፏል።
ይህንን ተከትሎ የሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ ፕሮ32 ማሰልጠኛ ኃላፊ ሆኖ ድርጅቱን እንዲቀላቀል የስራ ቅጥር ደብዳቤ ልኮለታል።
ነገር ግን በሩሲያ ህግ መሰረት አንድ ሰው ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ ለመስራት እድሜው 14 አመት መድረስ አለበት፡፡
ስለዚህም ሰርጌይ እድሜው ለቅጥር እስከሚደርስ ድረስ ድርጅቱን ማገዝ በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ከወላጆቹ ጋር መወያየቱን የፕሮ32 ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢጎር ማንዲክ ለቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ተናግሯል፡፡
ቤተሰቦቹ ልጃቸው ባገኘው እድል በጣም ደስተኛ እንደሆኑ እና ሰርጌይ ኩባንያውን እስኪቀላቀል በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልጸውልኛል ብሏል፡፡
ታዳጊው ሰርጌይ 3ሺህ 500 ተከታዮች ባሉት የዩትዩብ ቻናሉ ላይ በሩሲያኛ እንዳንዴም በተሰባበረ በእንግሊዘኛ በሚለቃቸው ስለኮዲንግ፣ ፓይቶን፣ ፕሮግራሚንግ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ስለ ተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በማስተማር ‘የኮዲንግ ሞዛርት’ ለመባል ችሏል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa