ነዋሪዎች በሰሜን ወሎ ዞን በምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕፃናት በቂ እርዳታ አልቀረበም አሉ!
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በ16 ቀበሌዎች በተከሰተው የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናትንና እናቶች ለመታደግ የተሰራጨው የአልሚ ምግብ ርዳታ በቂ እንዳልኾነ፣ ወላጆች፣ የቡግና ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊና ሐኪሞች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለአንድ ዓመት በዘለቀው ግጭት ምክኒያት ወረዳው ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር እንደኾነ የተናገሩት የቡግና ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል አለሙ፣ ቀድሞውኑ በአልሚ ምግብ ርዳታ ሲደገፍ የቆየውን ማኅበረሰብ ለከፋ ችግር እንደዳረገው ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሦስት እናቶች፣ በጤና ሠራተኞቹና በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት የሕፃናቱ መጎዳት በይፋ ከታወቀ በኋላ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የተሰራጨው የሕፃናት አልሚ ምግብ በቂ አይደለም ብለዋል። በቂ ርዳታ በአስቸኳይ ካልተከፋፈለ በሕፃናትና ነፍሰጡር እናቶች ላይ የታየው ከፍተኛ ጉዳት ወደ አዋቂዎቹም መዛመቱ እንደማይቀር አሳስበዋል።
የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር፣ ከ16 ቀበሌዎች ከተውጣጡ 18 የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የጤና ባለሞያዎች ጋራ በተደረገ ውይይት ርዳታው እንዲገባ ኃላፊነቱን በመውሰዳቸው ርዳታ መላክ ጀምረናል አኹንም እንቀጥላለን ብለዋል።
ከሀገር ሽማግሌዎቹ አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረእግዚአብሔር ዝናቤ፣ ሕፃናቱ ከሞመታቸው በፊት ርዳታ እንዲታደል ባቀረቡት ልመና የአልሚ ምግብ መግባት መጀመሩን ገልጸው፣ ነገር ግን በቂ አይደለም ብለዋል።
Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa