“የገቢዎች ቢሮ ያሳለፈው ውሳኔ የኢንዱስትሪ ሰላምን እንዳያውክ እሰጋለሁ” -የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ፌደሬሽን
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደሞዝ ግብር ማጭበርበርን ለመቅረፍ እንደ ሆቴሎች እና ካፌቴሪያዎች ባሉ የተመረጡ የንግድ ተቋማት ላይ “ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን እና የሰራተኛ ብዛትን” በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ የኢንዱስትሪ ሰላምን እንዳያውክ እሰጋለኹ ሲል የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ፌደሬሽን አስታወቀ።
የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የቢሮው ውሳኔ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጁን መሠረት ያላደረገና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልም እንደሃገር ገና በሂደት ላይ ባለበት ወቅት የተወሰነ መሆኑን መግለጻቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።"ውሳኔውን በተመለከተ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት አልተደረገም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ዝቅተኛ የሠራተኛ ብዛትን በተመለከተ ንግድን በነጻነት ከትንሽ ተነስቶ ለማሳደግ አዳጋች እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ በበኩላቸው ከዚህ በፊት እንደ ምግብ እና መጠጥ ቤቶች ያሉት የንግድ ተቋማት ለሠራተኞቻቸው ስለሚከፍሉት ደመወዝ በአግባቡ እንደማይገልጹ ጠቅሰው የግብር ማጭበርበርን ለማስቀረት አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አመልክተዋል።
በዚህም ቢሮው ለሆቴሎች፣ ለካፊቴሪያዎች፣ ለምግብ እና መጠጥ ቤቶች እንዲሁም ለሥጋ ቤቶች ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት ተመን እና ዝቅተኛ የሰራተኞች ደመወዝ ወለል ማስቀመጡን ተናግረዋል።አክለውም ይህ አዲስ አሰራር አነስተኛ የንግድ ተቋማትን እንደማይመለከት ገልጸው የንግድ ሥርዓቱን የሚያውክ ነገር የለም ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa