"እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ! በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮታዊ ባሕርይ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እርሱ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር አይ ዘንድ የቸርነቱ ፀዳለ ብርሃን ዐይነ ልቡናየን ያብራልኝ፤ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ! ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የሁሉ እመቤት ነሽ እኮን።"
"እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ! የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዐርብ የተገኘውን የደኅንነታችንን ተስፋ ያስገኘሽ እውነተኛ መዝገብ ነሽ እኮን፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኀዘን ከገነት ወጥቶ በተሰደደ ጊዜ ከልቡናው ኀዘን ተረጋግቶብሻል፡፡" (መልክዐ ኪዳነ ምሕረት)
የብርሃን እናት ድንግል ወላዲተ አምላክ ከቃል ኪዳኗ ታሳትፈን! ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እና የዐሥራት ሀገሯን ቅድስት ኢትዮጵያን ትጠብቅልን! ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁ እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን!!!