“ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለምን የአዋልድ መጻሕፍትን ትጠቀማለች” በሚል መሪ ቃል የቦሩ ሜዳ መርሐ ግብር መከናወኑ ተገለጸ።
ጥር ፳፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለምን የአዋልድ መጻሕፍትን ትጠቀማለች” በሚል መሪ ቃል የቦሩ ሜዳ የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር ከልዩ ልዩ ቤተ እምነቶች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ውስጥ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።
በዕለቱ የአዋልድ መጻሕፍት መነሻ እና መድርሻ ከየት ወዴት እንደሆነ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ከታዳሚዎችም ለተነሡ ጥያቄዎች በመምህር ባሕረ ጥበባት ሙጩ እና በመምህር ዮሐንስ ጌታቸው ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች በዕለቱ አጀንዳ ላይ የፈለጉትን ጥያቄ ፊት ለፊት የሚያቀርቡበት እና ምላሽ የሚያገኙበት ቦሩ ሜዳ የተባለ መርሐ ግብር በማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ በየሦስት ወሩ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።