በኢትዮጵያ በ2017 ዓመት 3 ሚሊዮን ኮንዶም እንደሚሰራጭ ተነገረ
በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም ለመቆጣጠር በተለያዩ አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
ኤ ኤች ኤፍ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት 3 ሚሊዮን የሚሆን ኮንዶም ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት ወደ ኢትዮጽያ እያስገባ መሆኑን እና ጅቡቲ ላይ መድረሱን እንዲሁም በቅርቡ ለደንበኞች ተደራሽ እንደሚሆን በኤኤችኤፍ ኢትዮጵያ የኤችአይቪ መከላከል እና ምርመራ አገልግሎት አድቮኬሲ ፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት ቶሎሳ ኦላና በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ተቋሙ እስካሁን ባለው በአዲስ አበባ ፣ ሲዳማ ፣ ኦሮሚያ ፣ አማራ ክልሎች ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት ትግራይ ክልል የስርጭቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነግረውናል። በመሆኑም በልዩ ሁኔታ ከተጠቀሱ ክልሎች ውጪ ባሉ ከተሞች የኮንዶም እጥረት ሲያጋጥማቸው ከታቀደው መጠን ባለፈ የስርጭት አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ ተቋሙ ማመቻቸቱ ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ ያለው የኮንዶም አቅርቦት ከተጠቃሚዎች ቁጥር ጋር እየተጣጣመ አለመሆኑ ሃላፊው ያነሱ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን እና በመንግስት እንዲሁም በግል ተቋማት በኩል ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን አንስተዋል። ኮንዶም ከቫት ነጻ በመሆኑ የግል ተቋማት በዝቅተኛ ሂሳብ ለደንበኞች የሚያቀርቡበት መንገድ መመቻቸት እንዲሁም ያለውን እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ኤችአይቪን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ከአጠቃቀም አኳያ ያለው የግንዛቤ ማነስ መኖሩን ወጣቶች ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት ዋናኛ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።ኮንዶም ለኤችአይቪ ኤድስ ብቻ ሳይሆን ለአባላዘር እንዲሁም ከሌሎች በሽታዎች ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን እና ከ15 እስከ 29 ዓመት እድሜ ላይ ያሉት ወጣቶች በተቻለ መጠን ራስን መጠበቅ እንዲሁም የኮንዶም አጠቃቀምን በተመለከተ ሁሉም ሰው ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ አቶ ቶሎሳ ኦላና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል