በኢትዮጵያ በየዓመቱ 30 ሺህ ህፃናት ከነርቭ ዘንግ ክፍተትና ከጭንቅላት ውሃ ክምችት ጋር አብረው ይወለዳሉ ተባለ
በኢትዮጵያ በየአመቱ ከሚፀነሱ ህጻናት መካከል 30 ሺህ የሚሆኑት ከነርቭ ዘንግ ክፍተትና ከጭንቅላት ውሀ ክምችት ጋር አብረው እንደሚወለዱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሚኒስቴሩ የስርአተ ምግብ ባለሙያ ወ/ሮ ቤዛዊት ወርቁ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከጉዳዮ ጋር በተገናኘ እንደ ሀገር ወጥ ጥናት ባይኖርም በተለያዮ ክልሎች ላይ የተጠኑት ጥናቶች በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ህፃናት በችግሩ እንደተጠቁ ያሳያሉ ብለዋል።
የሰሜንና የደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በይበልጥ ለችግሩ ተጋላጭ መሆናቸዉን ጠቅሰው በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ህፃናት የችግሩ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።የችግሩ መንስኤዎች በርካታ ቢሆኑም የፎሊክ አሲድ እጥረት በዋነኛነት ይጠቀሳል በማለት የስርአተ ምግብ ባለሙያዋ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።
አንዲት ሴት እድሜዋ ከ15 እስከ 49 በሚሆንበት ጊዜ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ምግቦችን በመውሰድ ይኖርባታል ተብሎ ቢመከርም ከእርግዝና በፊት ይህን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ክፎተቶች መኖራቸዉ ተገልጻል።ችግሩ በተለይም ከአመጋገብ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር እንደመሆኑ እስከ 70 በመቶ የፎሊክ አሲድ እጥረት ለችግሩ እንደሚያጋልጥ መረጃዎች ያሳያሉ።
አያይዘውም በዚህ ምክንያት ህጻናቱ ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳት ብሎም ለሞት ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል።በመዉለድ የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ሴቶች በቤታቸዉ በሚገኙ ምግቦች በቀላሉ ፎሊክ አሲድን ማግኘት የሚችሉ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል እንደ ምስር፣ሰላጣ፣አቮካዶ፣አተር እና የዶሮ ስጋ ያሉ ምግቦችን መመገብ ይኖርባቸዋል ተብሏል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል