የጥምቀት በዓል በተከበረባቸው የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሥርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
👉ከእነዚህ መካከል በተወሰኑት ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የበዓሉን ሠላማዊነት በቅርበት ለመከታተልና ለህብረተሰቡ ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ላይ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማቋቋም የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማዋቀር ከፍትህ እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ተግባር ወንጀልን እና የወንጀል ስጋቶችን መቆጣጠር ችሏል፡፡
በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በእነዚሁ በጊዜያዊነት በተቋቋሙት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ምርመራ ተጣርቶባቸዋል፡፡ ከተያዙት መካከል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መኖራቸውም ታውቋል፡፡
ብርሀኑ አበበ የተባለው ተከሳሽ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲዮም በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በርካታ ሰው መሰባሰቡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ የስርቆት ወንጀል ፈፅሟል፡፡
ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተከሳሹ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በግምት 3:00 ሰዓት ገደማ ከሁለት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ 2 ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡
ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ካጠናቀቀና አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በበዓሉ ስፍራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በዚያው ዕለት ተከሳሽ ብርሃኑ አበበ በ2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት የፖሊስ መምሪያው መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ በነበረው የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል፡፡
ታዘበው ሞላ የተባለው ይኸው ተከሳሽ በበዓሉ ከታደሙ አንዲት ግለሰብ ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቆ በድጋሚ ከሌላ ሰው ላይ ሊሰርቅ ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በስፍራው በተቋቋመው ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ከተጣራበት በኋላ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
ዛሬ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም የተከሳሽ ታዘበው ሞላን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በተፋጠነ ችሎት በማየት ጥፋተኝነቱን በማስረጃ በማረጋገጥ በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በጃን ሜዳ በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የታዳሚውን ብዛት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተመሳስለው ገብተው ወንጀል የፈፀሙ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል፡፡
ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት፣ የቅሚያ እና የራስ ያልሆነን ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል የፈፀሙ ናቸው ተብሏል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ የወንጀል ፍሬ የሆኑ እና የተለያየ አይነት ሞዴል ያላቸው ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል