ተደፍራ የወለደችዉን ልጅ በማዳበሪያ ጠቅልላ ጫካ ዉስጥ የጣለችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በምስራቅ ቦረና ዞን ምዕራብ ወላቡ ወረዳ ዉስጥ የወለደችዉን ልጅ በማዳበሪያ ጠቅልላ የጣለችዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቷ ተገለፀ ። እንደ ምዕራብ ወላቡ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፃ ተከሳሽ ጀሚላ ጡና የተባለችዉ ግለሰብ ከጋብቻ ዉጪ በደረሰባት የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የወለደችዉን ልጅ ማዳበሪያ ዉስጥ በመጠቅለል ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ላይ ማንም ሳያያት ጫካ ዉስጥ የጣለች መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል ።
ተከሳሻ ከጋብቻ ዉጪ ተገዳ በመደፈር በመዉለዳ እና ቤተሰቦቿን በመፍራቷ የተነሳ ድርጊቱን መፈፀማ ተገልጿል ። በወቅቱ በስፍራዉ በነበሩ ግለሰቦች ጥቆማ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ልትዉልም ችላለች ።
ፖሊስም የተጣለዉ ህፃን በህይወቱ አለመኖሩን በማረጋገጡ የቀብር ስነስርዓት እንዲፈፀም ካደረገ በኋላ የተከሳሻ የምርመራ መዝገብ ለአቃቤ ህግ ልኳል ። አቃቤ ህግም በወንጀል መቅጫ ህግ ቁጥር 574 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ልጅን ወልዶ በመጣል ወንጀል ህግ ክስ መስርቶባቷል ።
የአቃቤ ህግን ክስ ሲከታተል የቆየዉ የምዕራብ ወላቡ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሻ ያለፍቃዳ ተደፍራ መዉለዷን እንደ ክስ ማቅለያ በመዉሰድ በ1 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምዕራብ ወላቡ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘዉ መረጃ አመላክቷል።
#ዳጉ_ጆርናል