በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና በዓመት ከ5 ሺ በላይ ህጻናት አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የነርቭ እና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና ማዕከል ተመረቀ
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የገነባነውን እና ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የህጻናት የነርቭ እና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና የልህቀት ማዕከል አስመርቀናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉለት ይህ የልህቀት ማዕከል በዓመት ከአምስት ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለህጻናት ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው እንዲሁም አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ የሚደግፍ ነው ብለዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የተገልጋዮች ፍላጎት ለማስተናገድና በጤናው ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለገነባነው ለዚህ የልህቀት ማዕከል የሪች አናዘር ፋውንዴሽን ላደረገልን አስተዋፅዖ በነዋሪዎቻችን እና በራሴ ስም ላመሰግን እወዳለሁ ሲሉ ከንቲባዋ ገልፀዋል።
#ዳጉ_ጆርናል