የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት አቅም የሌላቸውን
ለመደገፍ ካሰባሰበው ድጋፍ ለአካል ጉዳተኞች አበረከተ።
ድጋፉ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ህብረት ፌደሬሽን የተበረከተ ሲሆን በማህበሩ በኩል
ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች የሚተላለፍ ይሆናል።
የከተማ አስተዳደሩ ያበረከተው ድጋፍ የንፅህና መጠበቅያ ቁሳቁሶችና ምግብን ያካተተ
ነው።
በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞች ማህበሩ የሚገኝበት ቅጥር ጊቢ ለአካል ጉዳተኞች
የማይመች በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ወጪ በአዲስ መልክ እንዲገነባ መወሰኑን ከከንቲባው ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@zena24now