┈┈••◉❖◉●••┈
👨🌾 ተወዳጁ🌺
❣ :¨·....................:¨·.❣
♥️ ክፍል አንድ
✍በአሁኑ ደግሞ እጅግ አጓጊ ና አሳዛኝ ታሪክ ይዤ መጥቻለሁ በአስተያየታችሁ መሰረት ባሁኑ የወንድ ልጅን ታሪክ ነው የማቀርብላቹ !!!!🌺🌺🌺🌺
ሄኖክ ዳኜ ይባላል የተወለደው በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ ላይ ሲሆን የአ.አበባን ውሃ የቀመሰው ገና በልጅነቱ የ5 አመት ህፃን ሆኖ ነበር ወላጅ እናቱ ታናሽ እህቱን ስትወልድ በፈሰሳት ደም ምክንያት ስትሞት የእናቱ ወንድም አበበ ሄኖክን ለማሳደግ ከባለቤቱ ወ/ሮ ሀና ጋር በመነጋገር ወደ አዲስ አበባ ይዞት
ይመጣል ... ይሄኔ የአጎቱ ሚስትም ሆነች አጎቱ በሄኖክ ደስተኛ ሆኑ ምክንያቱም ልጅ ለመውለድ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም ፈጣሪ ደግሞ ይህን በማሰብ ሄኖክን ሰጣቸው...
ሄኖህ እንደማንኛውም ህፃን የአፀደ ህፃናት ትምህርት አልተማረም
ገና በ6 አመቱ ቀጥታ 1ኛ ክፍል ነበር የገባው ታድያ ሄኖክ ምንምኳ ኬጂ(kg) የመማር እድል ባይገጥመውም በክፍሉ
ውስጥ ካሉ ጎበዝ ተማሪዎች ተርታ ይሰለፍ ነበር... አጎቱ አበበም ሆነ የአጎቱ ሚስት ሀና ሄኖክን እንደ ልጃቸው ይወዱታል አፀደ ህፃናት ያልተማረውም ከክፍለ ሀገር ሲመጣ 6ኛ አመቱን ይዞ
ስለነበር እድሜው እንዳያልፈው በማሰብ ነበር... ሁሌም ከስራ ሲመጡ ባልና ሚስት ጣፋጭ የሆነውን ልጃቸውን በናፍቆት ነው የሚያገኙት እሱም ወላጆቹን እረስቶ ወላጅ ካደረጋቸው
ሰንብቷል...ማደግ አይቀርምና ሄኖክ የ19 አመትና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሆነ
ይሄኔ ነበር ህይወት ፈተናዋን ሀ ብላ የጀመረችው እጎቱ በድንገተኛ ህመም አረፈ ሆኖም ሀና የቀድሞ ፍቅሯን ሳትቀንስ ኑሮ ቀጠለ ...ሄናክ ገና በ19 አመቱ የ25 አመት ወጣት ይመስላል ከግቢው ተማሪዎች በጠቅላላ ውብ አማላይና በትምህርቱ ጎበዝ ባጠቃላይ
ሁሉን አሟልቶ የሰጠው ብቸኛ ሰው እሱ ነበር ፈጣሪ እጁን ታጥቦና ተጨንቆ የሰራው ይመስላል ይሄኔ በብዙ ሴቶች እይታ ውስጥ ገባ... የሄኖክ የልብ ጓደኛ መስፍን ይባላል እሱ ከሄኖክ በተቃራኒው ወፍራምና ድቡልቡል በመሆኑ በቅፅል ስሙ ዶጮ እየተባለ ይጠራል... ታድያ ይሄ ጓደኛው መልካም ከመሆን ባለፈ
ለሄኖክ የልብ ጓደኛው በመሆኑ ሴቶች ሁሌም ደብዳቤ ለሄኖክ እንዲሰጥላቸው ይልኩት ነበር.... የ12ኛ ክፍል ትምህርት ተጀምሮ በመማር ላይ ሳሉ አንድ ቀን
እረፍት ሲወጡ አንዲት ጠይም ፀጉሯ እንደሚያምር ቢያስታውቅም በቅጡ ያልተያዘ ቀጠን ብላ አይኖቿ በብዙሃን አስተያየት የፍቅር አይን የሚባልላት ከዛን ቀን በፊት አስተውሏት የማያውቅ የ9ነኛ
ክፍል ተማሪ ወደ ሄኖክ በመቅረብ አንድ ወረቀት ሰጠችው ያኔ ገና ሲያያት ልቡ ስንጥቅ ብሎ የገባች መሰለው ሀሳቡ በሙሉ ስለሷ ብቻ ሆነ በሚያማምሩ ጥርሶቿ ፈገግታን ለግሳው "ጓደኛዬ
ናት የላከችልህ መልስህን እዚው ጋር መጥቼ እቀበልሃለው" ብላው ተመልሳ ሄደች በአይኖቹ ተከተላት ከሩቅ ሌላ ቀይ እረዘም ብላ ከልብስ እስከፀጉሯ በጥንቃቄ የተዋበች ሴት ትጠብቃት
ነበር... በርግጥ ለሄኖክ ደብዳቤ ብርቁ አልነበረም ይሄ ቀን ግን ልዩ ነበር
ነግቶ እዛ ቦታ እስኪሄድ ቸኮለ... ይሄን እያሰበ ደብተሩን ገልጦ ያየዋል የአጎቱ ሚስት ሀና ይሄን ሰአት በር አንኳኳች ሰራተኛዋ ከፍታላት ስትገባ ሁኔታዋ እንኳን ለሚያውቃት ለማያውቃት
ያስደነግጣል ... "አንድ ልጅ እንኳ ሳይሰጠኝ ጥሎኝ ሄደ..." ትላለች በሰከረ አንደበቷ ቃላቱን እየጎተተች... ባሏን ነበር... ሁኔታዋ የረበሸው ሄኖክ አይዞሽ እናቴ ብሎ ጫማዋን አውልቆ አስተኛት ይሄ ሁኔታ ግን በዛን ቀን ብቻ አልተቋጨም... ደጋግማ ትሰክራለች ከዛም አልፋ ከሄኖክ ከፍ የሚሉ ጎረምሶችን ይዛ መምጣት ጀመረች.........
ከተመቻችሁ ላይክ👍
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
@zenafetabegna ዘና ፈታ በኛ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄