መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦
ዘፋኝ የራሱን ነፍስ አጥፍቶ የሰውን ነፍስ ጨምሮ እንደ ሚያጠፋ መጻሕፍት በብዛት ያስረዳሉ። የእስክንድርያ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አትናቴዎስ አባ ባውሚንን ወደ እርሱ እንዲመጣለት መልእክተኛ ልኮበት በመንገድ ሲሄድ አንዲት ዘፋኝ እየተጫወተች አይቶ ዕንባው እስኪ ፈስስ ድረስ አለቀሰ። አብረውት ያሉት አኃው መነኮሳት አባታችን ሆይ! ዕንባህ እንደ ውኃ እስኪወርድ ድረስ ለምን ታለቅሳለህ? አሉት። አባ ባውሚንም ስለሁለት ነገር አለቅሳለሁ። አንደኛ ዘፋኝ በመሆኗ ነፍሷን ያጣች የዚችን ሴት ጥፋት እያሰብኩ። ሁለተኛም ይች ሴት አምላካችን በማይወደው ዘፈን ሰዎችን ለማስደሰት ይኸን ያህል ስትተጋ እኔ እግዚአብሔርን የማስደስትበት ትጋት የለኝምና፥ ይኸን እያሰብኩ አለቅሳለሁ ብሎ መልሶላቸዋል (ዜና አበው)።
(መምህር ዲበኲሉ ሰንደቄ - "ነገረ መላእክት" ያልታተመ መጽሐፍ)
https://t.me/zikirekdusn