═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦
🌹የፍቅር ንቅሣት♥
ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል
ክፍል 7⃣
✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅
✍ ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።ብሎ ተቀመጠ።ማስተዋል በተሞላበት ንግግሩ ኮራሁበት።እናቴ ቡና አፍዪ ብላኝ ቡና እያፈላው ብዙ ስነወራ ካመሸን በኀላ ሁሉም ወደ ቤት መሄድና የቀሩት መተኛት ሲጀምሩ እኔና ሮቢ ቁጭ ብለን እያወራን እጄን የሡ እጅ ላይአድርጎ ጣቴን መለካት ጀመረ፤ሮቢ ምን እየሠራህ ነው ስለው ደሞ ሠፊ ቀለበት ገዝቼልሽ የሠው መሣቂያ እንዳልሆን ነዋ አለኝ።ሁለታችንም እየተሣሣቅን እናቴ ድንገት መጥታ እናንተ ከተገናኛቹ በቃ ወሬ አያልቅባችሁም አይደል ነገ እኮ ት/ት አለ ነይ በይ ተኚ አለችኝ እየሣቀች አንተም ደክሞሀል ሮቢ ከትላንት ጀምሮ አልተኛህም በል ተኛ አለችው።አቅፌው ቻው አልኩትና ወደ ቤት ሄድኩኝ።መጋቢት ሰባት ማታ ላይ የኔ ቤተሠቦች አስት የሮቢ ጓደኞች ሌሎች ተከራዮችና እኔና ሮቢ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን ነበር።ሁሉም እራት በልቶ ጨርሶ የየራሡን ወሬ ማውራት ሲጀምር እኔና ሮቢም ከጓደኞቹ ጋ ማውራት ጀመርን።ሁሉም ቀስ በቀስ ወደ ቤት ሲገባ የሮቢ ሁለቱ ጓደኞቹ ደሞ በ pc film ማየት ጀመሩ እኔና ሮቢ ፊልሙ ስላልተመቸን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ከሮቢ ጋ ቁጭ ብለን የባጥ የቆጡን ስነሠወራ ለካ ሠአቱ ሄዶ ነበር፤ከሡ ጋ ስሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ ልክ እንደ ሁል ጊዜው እጄን ይዞኝ እያወራን ጓደኞቹ ተነስተው በቃ እንሂድ ሲሉ አስትም ወጣችና አው መሸባቹ ሂዱ እናንተም ግቡና ተኙ መቼም እናንተን መለያየት ችግር ነው አለችን።ቅር እያለንም ቢሆን ተነስተን ገባን።ፍቅር ለኔም ሆነ ለሮቢ የመጀመሪያችን ነው። ለኔ በጣም ለብዙ ነገር መጀመሪያዬ ሮቢ ነው።ብዙ ነገሮችን በሡ አይቻለው፤ተምሬያለው።ደስ የሚል እና ሁሌም ቢያስቡት የሚያስቀና የማይሠለች የፍቅር ጊዜ አብረን አሣልፈናል።ቅዳሜ ቀን እኔ ግቢ ውስጥ ለማፍላት እቃ አቀራርቤ ቡናውን እየቆላው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና earphone አድርጎልኝ ላንቺ ነው ውዴ ስሚው አለኝ።የናቲ ማን የመጀመሪያዬ ሚለው ዘፈን ነበር።ዘፈኑ ገና መውጣቱ ነው ተነሣሁና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር።እንዴ ቆይ ሌላም አለ ድጋሜ ትስሚኛለሽ ብሎኝ አሁንም የናቲ ማን track 01 ሚለውን ዘፈን ከፈተልኝ።ሀሣባችንን በደንብ ሚገልፅ ግጥም ስለነበረው በጣም ነው የወደድኩት ቅዳሜን በጣም ደስ ብሎን አሣለፍን።ማታ ላይ እናቴ የኔና የሮቢ ቅርበት በጣም በዝቶባት ስላጠራጠራት ያለንን ግንኙነት እንድነግራት ጠየቀችኝ።እኔም ምንም ሣልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት፤ሁሉንም ስለነገርኳት ደስ ብሏት ሮቢንም ስለምታውቀው ምንም አላለችኝም።ሁሉም ነገር ሲመቻች እንዴት ደስ ይላል ከሮቢ ጋ ያለን ፍቅር በጣም እየጨመረ መጣ በቃ ሁሉም እስኪቀናብን ነበር ምንፋቀረው፨ሮቢ ከጋበዘኝ ዘፈኖች ውስጥ የናቲ ማን(የመጀመሪያዬ እና ተነፋፍቆ)፤የያሬድ(ዘለላዬ)፤የታሜ(ሀኪሜ ነሽ)፤የሳንቾ(አታሣዩኝ) ሁሌ ስሰማቸው እስካሁን እሡን ነው የሚያስታውሱኝ ግን ከምንም በላይ የብስራት ሱራፌል(ቃል በቃል)ብሎ ያዜመውን ሙዚቃ ስሰማው ሮቢ አብሮኝ ያለ አጠገቤ የተቀመጠ ነው ሚመስለኝ ሁሌ ከሮቢ ጋ አብረን ስንሆን ስለምንሠማው ነበር።አንድ ቀን እንኳን ሣንኮራረፍ ሁለተኛ ወራችን እየቀረበ መጣ።መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን ነበር
✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like & Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
┄┄┉┉✽✽✽ ┄┄┉┉
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
💗💗------💗💗------