══•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦
🌹የፍቅር ንቅሣት♥
የመጨረሻው ክፍል 🔚
✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅
ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን፤ግን እኔ ከ5 ደቂቃ በላይ አብሬያቸው ሆኜ ለመጠበቅ ፍቃደኛ አልሆንኩም።ሮቢ አጠገቤ መጥቶ ግን የኔ አለመሆኑን ማሠብ ሞት ስለሆነብኝ ወደ ቤቴ መሄድ ፈለኩኝ፤ጓደኛዬም እያመመኝ ስለነበር ተጨንቃ ወደ ቤት አብራኝ ሄደች።እቤት ካደረሰችኝ በኀላ ተመለሠች፤ልክ እሧ ስትወጣ ጠብቄ ባለቅስ ምመልሠው ይመስል ስንት ዘመድ የሚቀብረውን እንባዬን አፈሠስኩ።ሣላስበው የእናቴ ባል መጥቶ ከተኛሁበት አልጋ አጠገብ ከተቀመጠ በኀላ በጣም ደንግጦ ሮቢ ምን ሆነ ብሎ ጠየቀኝ፤እኔም ግራ እንየተጋባው ሮቢ የሆነ ነገር ሆኖ ነው ብለህ እነሸዴት አሠብክ አልኩት፤ያው ሠሞኑን ሀሳብሽም ጭንቀትሽም እሡ ስለነበር ነው አለኝ።ከመጀመሪያው ይበልጥ በጣም እያለቀስኩ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት፤ምንም ሊያምን አልቻለም ሮቢ አንቺ ላይ ይሄን አያደርግም አለኝ።እናቴ ጉዳይ ለማስፈፀም ሌላ ቦታ ነበረች፤በስልክ ነግሯት ነው መሠለኝ በነጋታው ት/ቤት መጣች።እሧ ስትመጣ የወደ ቤት ሠአት ደዉል ሊደወል የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ነበር፤ከክፍል ካስጠራችኝ በኀላ ት/ቤት ግቢ ውስጥ እንዴት እንደገባ ባላውቅም ሮቢ እኛ ወደቆምንበት ቦታ እየመጣ ነበር፤እየተንተባተብኩ ሮቢ አልኳት ለእናቴ ዞራ አየችውና ጎሽ እንደውም አናግረዋለው አለችኝ።እኔ ግን ልጅቷ የነገረችኝ ጆሮዬ ላይ ሲያቃጭልብኝ በፊት እንደዛ ለማቀፍ ምስገበገበውን ሮቢ ዛሬ ግን አጠገቡ መቆም አልሆንልሽ ቢለኝ አጠገባችን ሣይደርስ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ክፍል ተመለስኩ።ክፍል እንደገባው ወዲያው ስለተደወለ ለጓደኛዬ የሆነውን ነግሬያት ቦርሳችንን ይዘን ወደ ውጪ ወጣን፤ሮቢ እና እናቴ እያወሩ ነበር።ከግቢው ከወጣን በኀላ እናቴ ትንሽ ቆይታ መጥታ ሮቢን ድጋሜ ስለምታዋራው እዚው ከኤልሹ(ጓደኛዬ) ጋ አብረን እንድንሆን ነገረችን።ሮቢም ብዙም ሣይቆየሸ ወጥቶ ከእናቴ ጋ ቆመው ብዙ ሲያወሩ ከቆዩ በኀላ እናቴ ተመልሳ መጣች።ሮቢ ያላትንም እየነገረችኝ ወደ ቤት መሄድ ጀመርን።ሮቢ እኔ ላይ እንደዛ ያደረገበት ምክንያት በጣምምምም ሚገርም ነበር፤አስት ከኔ ጋ ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ ስለነገረችው ነበር፤ይገርማል አይደል እንዴ በጣምምም እንጂ ምክንያቱም ለኛ አብረን እንዳንሆን መከልከል ብርቃችን አልነበረማ፤በጣም ብዙ ችግሮችን አልፈን ፍቅራችንን ማንም እንዳይንደው አጠንክረነው ነበራ፤የኔ እናት ከአንዴም ሶስቴ ስትከለክለን ለፍቅራችን ቦታ ሠጥቼ አብረን እንዳልተጋፈጥን እሡ ይሄ ከብዶት ከኔ ወደ ሌላ ሴት ፊቱን አዞረ።ሮቢ ሊያገኘኝም ሆነ ሊያዋራኝ ምንም አልሞከረም ነበር፤እንዲያውም ይባስ ብሎ ለኔ ስሜት ምንም ሳይጨነቅ ፍቅሬ ምኔ እያለ ከልጅቷ ጋ ሚነሡትን ፎቶ fb ላይ በጣም በብዛት መልቀቅ ጀመረ።ከዛ በኀላ የነበሩት በወራት የሚቆጠሩ ወራቶች ለኔ እጅግ በጣም አስቸጋሪ እና አሳሳቢ ነበሩ።በአባቴ በእናቴ እና በተለያዩ ሠዎች ምክር ወደ ራሴ መመለስ ጀመርኩ። ያ ሀገር ምድሩን ያሰቀናና ምሣሌ የነበረው ፍቅር ዛሬ ሰብሳቢ አጥቶ ተበትኗል፤ሮቢን ከማንም ይበልጥ ማመኔ በብዙ ነገሮች ጎዳኝ።አንተ ለፍቅራችን ምንም መሰዋትነት መክፈል አልቻልክም፤መቼም ቢሆን ግን አንተ ላይ ፈርጄብህ አላውቅም ያዋጣህ መስሎህ ንፁህ ፍቅሬን ረግጠህ ሄደሀል።
ህይወት ሠንሠለት ናት፤አንዱ አንዱን ሲፈልግ ሚፈለገው ደሞ ሌላ ይፈልገል።ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት፤እጅግ ብዙ ነገሮችን አሠባጥራ የያዘች።ህይወት ስሌት ናት፤አንዱን እየቀነስን ሌላውን ምንተካባት።ግን ከምንም በላይ ሀያል የሆነው ፍቅር ህይወት ነው ይሄን ሁሉ ነገር አንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘ፤ሁሉም ሠው ልብ ውስጥ ያለ ግን አውቆ ለተጠቀመበት ብቻ ደስታን ምታጎናፅፍ።።።።።።።።
ተፈፀመ
ምስጋና ፦ ታሪኩን በመከታተል ሀሳባችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረስልኝ
፦ ሁላችንንም በአንድ አደርጎ እውቀቶችን ላስጨበጠን እንቁ ቻናላችንን
፦ ሁላችሁንም ክበሩልኝ በቅርቡ በአዲስ ስራ እመጣለሁ ሀሳባችሁን