♥️🚕 ባለታክሲው🚕💝
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር የቴሌግራም ቻናል የቀረበ
ክፍል 2
እኔ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንትና ነው ያየሁት እሱ እንዴት ስለኔ ይሄን ያህል ሊያውቅ ቻለ? ይሄን
እያሰብኩኝ ተከፍቶ ወደሚጠብቀኝ በር ገባሁ። መንገድ ጀመርን ስለራሱ እንዲነግረኝ ጠየኩት ተወልዶ ያደገው
ጨርቆስ አከባቢ እንደሆነና የወንድ አያቱ እጅግ ይወዱት ስለነበረ ሲሞቱ መሬት አውርሰውት ሞቱ መሬቱ ተሽጦ
እቺን ላዳ ታክሲ ገዝቶ ስራ መጀመሩን አጫወተኝ ግሩም ደስ የሚል ልጅ ነው ከውበቱም በላይ በዚች 2 ቀን ውስጥ ያሳየኝ መልካምነትና ስነምግባር በጣም የሚገርም ነበር እኔን የት እንደሚያውቀኝ ጠየኩት ሁሌ ታክሲ ስጠብቂ አይሻለሁ ደግሞ ሁሌ ብቻሽን ስለማይሽ
ይገርመኝ ነበር ከዛ አንድ ቀን የተሳፈርሽበትን ታክሲ ተከተልኩት አለምባንክ ስትወርጂ አየሁሽና መኪናዬን
ጥግ ላይ አቁሜ በእግሬ ተከተልኩሽ ከዛ ቤታቹ ስትገቢ አየሁሽ በራቹጋ የሆነ ጩጬ ሰላም ስትይ ስላየሁሽ
ጠራሁትና ያሁኗ ልጅ ስሟ ማነው ስለው ሊዲያ አለኝ ከዛ በቃ ሁሌ አንቺን መከታተል ስራዬ ሆነ አለኝ
አሁን የቅድሙ ጭንቀቴ ለቀቀኝና ዘና ብዬ ማውራት ጀመርኩ እየተጨዋወትን ትምርት ቤት ስለደረስኩ አውርዶኝ ከትምህርት መልስ እንደሚጠብቀኝ ነግሮኝ ሄደ እሱን እያሰብኩ አይደርስ የለ ትምርት አልቆ ስወጣ አገኘሁት ደስ አለኝ ደስታዬ ዉደር አልነበረውም።
በዚህ መልኩ ጠዋት ጊቢያችን በር ላይ ከሰዓት ትምህርትቤት በር ላይ መገናኘት ስራችን ሆነ የፍቅር ጥያቄ ከማናችንም አፍ ሳይወጣ በፍቅር ከነፍን እኔማ
ትምህርቴ ግሩም ስራዬ ግሩም ውሎዬ ግሩም ህልሜ ግሩም በቃ እስትንፋሴ ይመስል የሱን ስም ሳልጠራ
የማወራው ወሬ ጠፋ እሱን ሳላስብ የምታልፍ ደቂቃ ጠፋች እራሴን እስክረሳ ድረስ ወደድኩት።
በዚ መሀል ታላቅ ወንድሜ ሰማ እንዴት ምን ሲደረግ እንኳን አንቺ አንድ ፍሬዋ ልጅ እኔ ታላቅሽም ፍቅር
አልጀመርኩም አሁኑኑ ይሄን ነገር አቁመሽ ትምህርትሽ ላይ ብቻ አተኩሪ ድጋሜ ከዛ ልጅጋር እንዳላይሽ አለኝ
እኔ ግን ማንንም የምሰማበት ሰዓት አልነበረም ከግሩሜጋር እንዳላይሽ ከምትለኝ በህይወት እንዳላይሽ
ብትለኝ ይሻለኛል አልኩት በቃ ሁሌ ቤቱ ውስጥ ጭቅጭቅ ሆነ ሁኔታችን ግራ ያጋባት እናቴ ምንድነው ብላ
ስትጠይቅ ወንድሜ ሁሉንም ነገር ነገራት እናቴ በተራዋ እሪ አለች እኔ ግን ህይወቴ ታልፋታለች አላቆምም አልኩኝ
እንዲ እንዲ እያለ ጊዜውም ሄዶ ማትሪክ ተፈትኜ ት/ት ተዘጋ የትምህርት መዘጋት ለኔና ለግሩሜ ይባስ ምቹ ሆነልን ጠዋት ከሰፈር ይወስደኛል አዲስ አበባን ከሲኒማ ቤት እስከ ሆቴል ስናስሳት እንውልና ማታ ወደ ቤት ይመልሰኛል። የወንድሜና የእናቴ ጭቅጭቅ ከቀን ወደ
ቀን እየባሰ መጣ እኔ ግን ጆሮ አልነበረኝም ግሩሜ እስከዛሬ እንዴት ያለሱ ኖርኩኝ ብዬ እስከማስብ ድረስ
ህይወቴን በደስታ ባህር አጥለቀለቃት።
ታድያ አንድ ቀን እንደተለመደው አብረን ውለን ደስ የሚል ቀን አሳልፈን እቤት በር ላይ አውርዶኝ ተለያየን ሁሌም
ማታ ማታ ከተለያየን በኃላ እቤት ሲደርስ በሰላም መግባቱን ደውሎ ይነግረኛል ያን ቀን ግን ብጠብቀው ብጠብቀው አልደወለም እኔ ስደውል ስልኩ ዝግ ነው
ትንሽ ብጨነቅም ምናልባት ባትሪ ዘግቶበት ይሆናል ብዬ ተኛው ጠዋት ስነሳም አልደወለም ስሞክርም ዝግ ነው
አሁን በጣም አሳሰበኝና አንድ ብሩክ የሚባል ጓደኛውጋ ደወልኩ ከብዙ ጥሪ በኃላ አነሳው ሰላምታ እንኳን
ሳልጠይቀው ቀጥታ ወደጉዳዬ ነው የገባሁት ብሩክ ግሩሜ ምን ሆኖ ነው ስልኩ ማይሰራው?
አልኩት ብሩክ እየፈራ
ሊዱ ግሩሜ ማታ አንቺን ሸኝቶ መኪናውን ማደሪያ ቦታ
አቁሞ ሲመለስ ሌቦች ገንዘብ የያዘ መስሏቸው ደበደቡት አሁን እዚ አለርት ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ተኝቷል እኔም
አጠገቡ ነኝ ከዚህ በኃላ የተናገረውን አልሰማሁትም ከአልጋዬ ተወርውሬ ተነስቼ ጠረቤዛ ላይ ያገኘሁትን ብር
አንስቼ እሮጥኩኝ በምን ፍጥነት ከሆስፒታሉ እንደደረስኩ አላውቀውም ከብዙ ፍለጋ በኃላ ግሩሜ የተኛበትን ክፍል አገኘሁት እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አለቀስኩ አበድኩ እንደምንም ብሎ
አይዞዞሽ ማሬ ደና ነኝ እኮ አለኝ በቃ ውሎዬ እዛ ሆስፒታል ሆነ እቤት የምገባው ለማደር ብቻ ነው እሱንም
አባቴን ፈርቼ እንጂ ከግሩሜ ባልለይ ደስታዬ ነበር።
ከሳምንት በኃላ እቤት ሆኖ ህክምናውን መከታተል እንደሚችል ተነግሮት ከሆስፒታል ወጣ እኔም እቤቱ
እየዋልኩ ማስታመም ጀመርኩ
ታድያ አንድ ቀን ጠዋት እቤት አድሬ ወደሱ ቤት ስመጣ ጓደኞቹ ተሰብስበው እያወሩ ደረስኩ በሩ ክፍት ስለነበረ
መግባቴን ማንም አላየም አንደኛው ጓደኛው ቆይ ለምን እንሷን መደበቅ አስፈለገ ገሎህስ ቢሆን
ኖሮ? ፈጣሪ ነው ያተረፈህ እንጂ እሱማ የሞትክ መስሎት ነው ጥሎህ የሄደው ነገስ ቢጨርስህ ምን ይታወቃል?
ብሩክ ከሱ ተከትሎ እኮ እኔም ያንን ቀን ይነርራት ስል አይ ተው ብለህ አስዋሸኸኝ ቆይ እሱ ወንድሟስ ቢሆን
እንናተ ከተዋደዳቹ ምን አግብቶት ነው የሚያለያያቹ? የሰማሁትን ማመን አልልቻኩም በቆምኩበት መንቀጥቀጥ
ጀመርኩ ብሩክ ምንድነው የምታወሩት ግሩሜን ማን ነው የደበደበው? አልኩኝ ሁሉም ደንግጠው ወደኔ ዞሩ
መልስልኝ ብሩክ ማነው የደበደበው? ብሩክ ፀጉሩን እያሻሸ.....
ሊዱ ያኔ እኔ እውነቱን ልነግርሽ ስልእሱ ነው ተው ከወንድሟ ትጣላለች ብሎ ያስዋሸኝ እንጅ ግሩሜን
ወንድምሽ ነው ልጆች ቀጥሮ ያስደበደበው አለኝ በምን
ቅፅበት ከቤቱ ውስጥ ተወርውሬ እንደወጣሁ አላውቀም ብቻ ወንድሜን ፍለጋ ወደቤት ገሰገስኩ......
ክፍል ሶስት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ‼️
¶🌹የፍቅር ልብ❤️🩹¶™
•───────────────•🌐
#📱ከወደዱት ሼር ማድረግ አይረሳ
ሼር