♥️ ባለታክሲው🚕
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ
⭐️ክፍል 5️⃣
💝የመጨረሻው ክፍል♥️
........ አይኔ ያየውን ማመን አልቻልኩም በቆምኩበት ሀውልት ሆኜ ቀረሁ.....
አይኖቼን ጨፈንኳቸው ደግሜ ገለጥኳቸው አዎ እውነት ነው ያየሁት እውነት ነው
........ የኔ ግሩሜ የኔ ግሩም እስትንፋሴ የኔ የብቻዬ የሚመስለኝ ግሩሜ ከሷጋር
ተኝቷል ቦርሳዬ ከእጄ አምልጦኝ ሲወድቅ በሰሙት ድምፅ ሁለቱም ከገቡበት
አለም ነቅተው አዩኝ እኔ ግን ከዛ በላይ ቆሜ ለማየት አቅሙ አልነበረኝም
የእምባጭጋግ በጋረደው አይኔ እየተደነቃቀፍኩ እሮጬ ወጣሁ እሮጥኩ ወዴት
እንደምሮጥ አላውቀውም ብቻ ግን ስህተት የሰራሁት እኔ ይመስል ሸሸሁ
እሮጥኩ መንገድ ላይ የሚያየኝ ሰው እብድ መስዬው እስኪሸሸኝ ድረስ ........
ታክሲ ተራ ደረስኩ አለም ባንክ ሲጠራ ሰምቼ ገባሁ ደንዝዣለሁ ምንም
አይሰማኝም ብቻ እምባዬ ያለማቋረጥ ካይኔ ላይ ይዘንባል ታክሲው መንገድ
እንደጀመረ ረዳቱ ሂሳብ እየሰበሰበ እኔጋ ደረሰ ሂሳብ ስጪኝ ነፍሴ አለኝ
ምንም አልያዝኩም ምክንያቱም በድንጋጤ ቦርሳዬ ከእጄ እንደወደቀ ጥዬው ነው
የወጣሁት አጠገቤ የተቀመጡት አዛውንት ምነው ልጄ ደህና አይደለሽም?
አሉኝ ይባስ እንባዬ መርገፍ ጀመረ አሞሽ ነው የኔ ልጅ? አሉኝ በድጋሜ
ወደኔ ተጠግተው
እማማ እቀፉኝ አልኳቸው ደነገጡ ግራ ተጋቡ
እማማ ግሩሜ እኮ አብሯት ተኝቶ አየሁት 0ብሯት አዛውንቷ ይባስ ግራ
ተጋብተው ማነው ግሩሜ እስኪ ተረጋጊ የኔ ልጅ አሉኝ
ግሩሜ ባሌ ነው የልጄ አባት እማማ እቀፉኝ ህመሜን አልቅሼ ማውጣት
እፈልጋለሁ እቀፉኝ ታክሲ ውስጥ ያለው ህዝብ በፀጥታ የሁለታችንን ንግግር
ይሰማል እቅፋቸው ውስጥ አስገብተው በቀስታ ፀጉሬን እያሻሹ አይዞሽ ልጄ
አይዞሽ አይዞሽ አንቺ ንፁህ ነሽ እሱ ነው ማልቀስ ያለበት መገፋት ጥሩ ነው የኔ
ልጅ መበደል ጥሩ ነው ሲገፉ አወዳደቅ ያምራል ደግሞ እኮ ገና ልጅ ነሽ ብዙ
የሚጠብቅሽ ነገር አለ አሉኝ እቅፋቸው ውስጥ ሆኜ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ።
ወዴት እንደምሄድ ጠይቀውኝ ሂሳብ ከፍለውልኝ አየር ጤናጋ ወረዱ ያ
ንግግራቸው ግን ልቤ ውስጥ ቀረ
እናቴ ቤት ደረስኩ ገብቼ ልጄን በእናቴ እቅፍ ውስት በሰላም ተኝታ ሳያት ይባስ
አመመኝ በእምባ እየታጠብኩ የሆነውን ለናቴ ነገርኳት በቃ ታመምኩኝ ጤና
የሚባል ነገር ራቀኝ ሰውነቴ እለት ከእለት እየቀነሰ መጣ ብመከር ብዘከር ምንም
አልፅናና አልኩ ያቺ ቅፅበት ከአይኔ ላይ አልጠፋ አለች እናቴ የልጄንና የኔን ልብስ
ሄዳ እንድታመጣልኝ ነገርኳት ግን ግሩሜ ከዛች ቀን በኃላ እዛ ቤት
እንዳልተመለሰ ጎረቤቶች ለናቴ ነገሯት ስልኩ ላይ ሲደውሉም ዝግ ነው ክህደቱ
ይሄን ያህል ጎድቶኝ ደግሞ መልሼ የት ገብቶ ይሆን ምን አጋጥሞት ይሆን
እያልኩ እጨነቃለሁ አባቴ ግራ ገብቶት ካንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ
ካሁን በኃላ የህይወት መስመርሽን አስተካክይ ያለ ግሩም መኖር አልችልም
የምትይ ከሆነ ሂጂ ፈልጊውና ይቅርታ ጠይቀሽው አብረሽው ኑሪ አይይ አርፌ
ልጄን እያሳደኩ እኖራለሁ ካልሽ ደግሞ እናትሽ ልጅቷን ትይዝልሻለች አንቺ ወደ
ትምህርትሽ ተመልሰሽ ትማርያለሽ አሁኑኑ ውሳኔሽን አሳውቂኝ አለኝ በቃ
ወሰንኩ ከግሩምጋር ተመልሶ መኖር የማይታሰብ ነው ስለዚ ከልጄጋር ሆኜ
ትምህርቴን ለመማር ወሰንኩ ግን ከባድ ነበር ግሩሜ ያን አድርጎኝ እንኳን
ይናፍቀኝ ነበር ሆኖም ቻል አድርጌው አባቴ በመረጠልኝ ፊልድ ኮሌጅ ገብቼ
መማር ጀመርኩ ግሩሜ ግን ከዛን ቀን በኃላ አይኑን አላየሁትም አከራዮቻችን
ቤቱን አሰብረው የኔንና የልጄን ልብሶች ሰጡን
ታድያ ይህ ከሆነ ከአንድ አመት በኃላ ከትምህርት እየወጣሁ ስልኬ ጮኸ
የማላውቀው ቁጥር ነው አነሳሁ
ሄሎ ሄሎ... ምንም መልስ የለም ልክ ልዘጋው ስል
ማማዬ በጣም ናፍቀሽኛል ልጄም ናፍቃኛለች ከስልኩ ውስጥ የግሩሜን
ድምፅ ሰማሁ ልቤ ለ2 ተከፈለ ስልኩን የያዘው እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ ምንም
መናገር አልቻልኩም ዝምምም አልኩት ሊዱ አለኝ
አትጥራኝ ደግሞ ምን ቀረህ? አትጥራኝ እምና ልጃም ደህና ነን ያንተ
ፍርቅም ናፍቆትም አያስልፈገንም ደግሞ በቅርቡ ላገባ ነው ሰርጌ ላይ መገኘት
ከፈለክ ወረቀት ልክልሃሁ ብዬ ጆሮው ላይ ዘጋንበትና ሲምካርዱን አውጥቼ
ሰባበርኩት
አውቄ ነበር ላገባ ነው ያልኩት የኔ ልብ የተፈጠረው ለግሩሜ ብቻ ነው አሁንም
እንኳን በተሰበረ ልቤ እወደዋለሁ አስበልለሁ ግን ያንን ክህትደ ረስቼ አብውሬው
መኖር አልችልም በቃ የትናንት ታሪኬን መርሳት እፈልጋለሁ አዲስ ሲምካርድ
ገዝቼ ያስኩኝ
ህይትወ ቀጥላለች እንሆ እኔና ግሩሜ ከተለያየን 3 አመት አለፈን ልጄም 4
አመት ሊሞላት የተወሰኑ ወራቶች ይቀሯታል እኔም በተማርኩበት ፊልድ በዘንድሮ
አመት በማዕረግ ተመርቄ በኢትዮጵያ አርየ መንገድ የበርራ ክፍል በሆስተስነት
ተቀጥሬ መስራት ከጀመርኩ 2 ወር ሆነኝ
ለካ (ትንሽ ስህተት ትልቅ ፍቅርን ይገድላል) የሚባለው እውነት ኖሯል ያቺ ያንድ
ቀን ስህተት እንደዛ ለሰማይ ለምድር የከበደ ፍቅራችንን ገደለችው።
ዛሬ ልጄ ጓይዬ ናት እህቴ ናት ፍቅሬ ናት የመኖሬ ምክንያት ናት ልጄ ያለፈ ታሪኬን
ሳይሆን የወደፊት ህይወቴን የማይባት ንፁህ መስታወቴ ናት።
♥️ ተፈፀመ 🤗
ልዩ ምስጋና ለባለታሪኮቹና ለእናንተ ለወድ ቤተሰቦቼ🙏
በታሪኩ ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት በግሩፕ ውስጥ መግለፅ ትችላላችሁ