💞የፍቅር ቃል💞


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩
@daily_promoterr

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የዚህ ቻናል ዓላማ ሰዎች በመልካም አስተሳሰባቸው የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣የስኬት ተፈጥሯዊ ህግን በመረዳት ስኬታማ እንዲሆኑ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን''
Join Now
https://t.me/+kE5qcdRQO6tmNTE0




​​​​💞...

⇘እናት የመጀመሪያ የፍቅር ትርጉምና
ተምሳሌት ናት።

⇘ገና ሳታውቅህ በፊት ታፈቅርሃለች
መወለድህን በጉጉትና በናፍቆት
ትጠብቃለች።

⇘ከተወለድክ ቡኃላ ደግሞ በፍቅርና
በእንክብካቤ ታሳድግሃለች።

⇘እናት ስህተትህን እያየች ጉድለትህን
እያወቀች ምንም ሳትሳሳ ታፈቅርሃለች።

⇘እናት ማለት ፍቅር ናት አንተን ለማፍቀር
ምክንያት አትፈልግም።

❤️@yefker_kalee❤️


༻༺༺  ግ  ጥ  ም   ༻༻༻


       ❧❧ ልወዳት ነው መሰል ❧❧

ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ፤
ቀልቤ እኔን ጥሎ እሷ ጋር በረረ ።
አያት እንዳልነበር እንደ ንፁህ እህቴ፤
ታዲያ ምነው ዛሬ እንቅልፍ ማጣቴ።
አይኗን ካላየው ድብርት ውስጥ መግባቴ።
ልወዳት ነው መሰል ትናፍቀኛለች ፤
በደቂቃ ሲኮንድ ትዝ ትለኛለች ።
ከሌላ ጋር ሳያት በቅናት ማበዴ ፤
አፈቀርኳት መሰል ወቸው! በል ዘመዴ።
ልነግራት ስፈልግ የልቤን አውጥቼ፤
ፍቅሬ እንድትሆን በፅኑ ጓጉቼ ።
ግን ደግሞ እንደገና እጠራጠራለሁ፤
እህትነትሽን እንዳላጣ ሰጋሁ።
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ፤
በቃ................!
እነግራታለሁ በኔ አልተጀመረ።

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄
‌‌‌‌‌‌‌‌🌹🍃✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌✨🍃🌹 

❥............🍃🌹🍃.............
@yefker_kalee
@yefker_kalee

   🌹🌹 #LOVE 🦋🦋

7k 0 83 5 84

​​​​​​​  ​​         ┈┈••◉❖◉●••┈
         ዝም ብለሽ ስሚኝ🌺
      ❣ :¨·....................:¨·.❣


......... ✍ፃፍኩልሽ💌 ........

አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል
አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
ዛሬ ግን
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄
‌‌‌‌‌‌‌‌🌹🍃✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌✨🍃🌹   @yefker_kalee
       @yefker_kalee

7.3k 0 63 14 83



ውሎህን ቃኝ"!

አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ?
ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።

የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::
አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው
ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች

በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
"ውሎሽ የት ነው?"
Have a nice weekend


የኔ...

ተከፍቼ ሳዝን እንደ ወንድም፣
በደስታዬ አብሮነት የማትደክም፣
ስትቆጣኝ እንደ አባት ፣
ስትመክረኝ እንደ እህት ፣
የኔ መልካም የፍቅሬ እናት፣
ለኔ ስትል የማቶነው ምንም የላት።

ምን ልበላት...የኔ ፍቅር ማር ጣፋጬ?
ስም ከንቱ... ይጨነቅበት ስም አውጭው፡
እኔግን የእኔ ብያት፣
በአንዲት ውብ ቃል ልቋጭላት።

Ermi
✍


🌹🥀 @yefker_kalee 🌹🥀


ሰላም ውድ የፍቅር ቃል ቤተሰቦች
ከ 200 ሺ በላይ በተሰብሳቢዎቹ የካርድ ሽልማት ልንጀምር ነው ምን ይመስላችኋል በጥያቄ ነው ሽልማቶቹ


" ለጦጣ 1 ሚሊዮን ብር እና ሙዝ ብታስቀምጥላት ምታነሳው ሙዙን ነው።"
                    ጃክማ
👉ልክ እንደዚሁ በተመሳሳይ ሁኔታ የጦጣ ጭንቅላት ያላቸው ሰዎችም አሉ በህይወታቸው ምን እና እንዴት መምረጥ እንዳለባቸው እማያውቁ።


         ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ

ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ

ከዚያን ቀን ጀምሮ

ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ

ዘገየሁ

መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው

እኔኮ ሆዴ

አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ፨

🌹🥀         ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ

ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ

ከዚያን ቀን ጀምሮ

ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ

ዘገየሁ

መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው

እኔኮ ሆዴ

አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ፨

🌹🥀
@yefker_kalee 🌹🥀

14.6k 0 123 3 115



━━━━━━━✦✦━━━━━━━

የናፍቆት መዶሻ ®

ባካል ተራርቀን የናፈቅሽኝ ለታ
ልቤ ይሰቃያል ያጣና እርጋታ
ሆዴም የሚራበው አይደለም ገበታ
ናፍቆቱ ነው እንጂ ልቤ ኣንቺን አጥታ
ቀልቤ ትረካለች ኣንቺን በማየቷ
ውሃ እንኳ ባትጠጣ ይጠፋል ጥማቷ
ልቤ ያጣጥማል በቀንም በማታ
በክፉም በደጉም ሄዶ በትውስታ
አብረን እየኖርን ያለፍነው ትዝታ
እማ የኔ አለም የልቤ መንገሻ
የሂይወቴ ማማር መነሻም መድረሻ
ሌላሰው አይደለም ኡሚ ኣንቺ ነሻ
የእንጀራ ነገር ማራራቁን ሲሻ
እኔን ካንቺ ኣርቆ አርጎኝ ሆደ ባሻ
ይቀጠቅጠኛል የናፍቆት መዶሻ

❤️
@yefkr_kalee❤️

16.7k 0 128 6 123

✅ኢትዮጵያ ለምትኖሩ ሁሉ  ትልቅ የስራ እድል ጠንክሮ በመስራት የምትለወጡበት ስራ

1 ምንም የትምህርት ደረጃ አይጠይቅም

2 በማንኛው እድሜም ሆነም ፆታ መስራት ይቻላል

3 100% ህጋዊ ከመግስት ፍቃድ ያለው  ድርጅት ነው በተለያዩ ከተሞች ቅርጫፍ አለው

ስራውን መጀመር ሆነም ስለስራው ማንኛውንም መረጃ ለማግኘት  በውስጥ ያናግሩኝ
📥 @ERMIYAS_27


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን!🙏❤🙏


‍ 💞ፍቅር ያሸንፋል💕

                  ክፍል አስራ ሶስት(13)

                    📌የመጨረሻ ክፍል📌

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

ልጁ ሊደፍረኝ ይጣደፍ ጀመር ብጮሂ እገልሻለው ቢልም እኔ ግን ሞትን መርጬ ሆቴሉን በጩኸት አደባለኩት ይሄኔ ደንግጦ በፍጥነት ክፍሉን ለቆ ወጣ ወድያው የሆቴሉ ሰራተኞችና ጥበቃው እየተንጋጉ መጡና ምን ሆንሽ አሉኝ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል ጭንቀት ነው ይቅርታ ከረበሽኳቹ አልኳቸው በድንጋጤ ግምባሬ ላይ ችፍ ያለውን ላብ እየጠረኩ አንዳንዶቹ እየተነጫነጩ አንዳንዶቹ ደግሞ በሁኔታዬ አዝነው ትተውኝ ወተው ሄዱ፡፡ ልክ ሲነጋ ለዮናስ ደወልኩለት አማራጭም አልነበረኝም ሰላምና ጓደኞቿ ጋር ብሄድ ተመልሼ ወደ ሱስ እንደምገባ አውቅ ነበር ለዛ ነው ዮናስን የመረጥኩት ደውዬ ከሆቴል መውጣቴን ስነግረው ያለሁበት ድረስ መጥቶ እቤቱ ወሰደኝ ብቻውን ነው የሚኖረው ግን ቤቱ በጣም ያምራል ቤተሰቦቹ አሜሪካ መሆናቸውን ነገረኝ ለምን እሱ እዚ እንደሚኖር ስጠይቀው መልሱ አንድ ነበር ከሀገር መውጣት አይፈልግም፡፡ ዮናስ ጋር መኖር ከጀመርኩ 1 ወር ሞላኝ ዮናስ ግርም የሚል ሰው ነው እጅግ በጣም ቆንጆና ሀብታም በዛ ላይ እድሜው ከ27 አይበልጥም ግን ለሴት ልጅ ያለው ክብር በዛ ላይ አንድ ቀን እንኳ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮም ሆነ በመልክና ገንዘቡ ሴት ማማለል ሲፈልግ አይቼው አላውቅም አብረን መኖራችንን ቀጠልን እኔም ስራ ፈልጌ ስላጣሁ ስደት ለመሄድ ማሰብ ጀመርኩ ይሄንንም ለዮናስ ሳማክረው ደስ እንዳላለው ነገረኝ፡፡ ይልቁንም አሁን ቤተሰቦቼን መጠየቅ እንዳለብኝ መከረኝ እኔ ግን ቢያንስ እንኳ ገንዘብ ይኑረኝ ለፍቅር ብዬ የከዳሁትን አባቴን ባዶዬን አይኑን ማየት አልችልም ያሳፍረኛል ነበር መልሴ ፓስፖርት አውጥቼ ደላላ ጋር ሄድኩኝ ከዛም ወደዱባይ ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመርኩ ይሄን ሳደርግ ዮናስ በጣም ተናዶብኛል ግን እድሜ ልክ የሚያኖረኝ የለም እሱም ቢሆን ሰው ነው አንድ ቀን ይሰለቸዋል ስለዚህ የሱን መናደድ ቦታ ሳልሰጠው መሯሯጤን ቀጠልኩ ታድያ አንድ ቀን ሙሉ ምርመራ ተመርምሬ ውጤት ለመላክ ስመረመር ውጪ መሄድ እንደማልችልና የልብ ድካም እንዳለብኝ ተነገረኝ፡፡ አሁን የምርም ፈጣሪ እንደረሳኝ አመንኩ ከዛም በጣም በንዴት ወደ መጠጥ ቤት ሄድኩኝ ልክ ገብቼ መጠጥ እንዳዘዝኩኝ ዮናስ ደወለ ገና ከማንሳቴ ጫጫታውን ሰምቶ እንዴ ደሞ ምን ሆነሽ ነው ወደተውሽው ማንነትሽ የተመለሽው አለኝ በቁጣ እኔም ከንግግሬ እምባዬ እየቀደመ ተስፋ ቆርጬ ነው ዮኒዬ ለማያውቀኝና ለረሳኝ ፈጣሪ ከዚ ቡሃላ አልጨነቅም አልኩት አሁኑኑ መጣው ብሎኝ ስልኩን ዘጋው ህይወት እንደዛ ቀን ተስፋ አስቆርጣኝ አታውቅም ከሀዘኔ ብዛት ማልቀስ በራሱ ተሳነኝ፡፡
ከተቀመጥኩ ከደቂቃዎች ቡሃላ አጋጣሚ ስዞር ሰላምና አንድ የማላውቃት ሴት ከካሌብ ጋር ክብ ሰርተው የመጠጥ አይነት ከፊታቸው ተደርድሯል እያየኋቸው መናደዴን ቀጠልኩ ከቆይታ ቡሃላ ሽንት ቤት ስሄድ ሰላም ተከትላኝ መጣች ባላያት ደስ ይለኛል እንኳን ቆሜ ላወራት ይሄኔ ከት ብላ እየሳቀች ዮኒ እቅዶቹ ሰርተውለታል አይደል አለችኝ ሁኔታዋ መስከሯን ያሳብቃሉ ምን ማለት ነው አልኳት ንዴት መላ አካላቴን እየወረረው ማለትማ አንቺን በእጁ ለማስገባት እንደለፋ አልቀረም መልአክ መስሎ...አለችና ከት ብላ ሳቀች በጣም ተናድጄ በጥፊ አልኳትና ልደግማት ስል ሰው ያዘኝ ግን ምን ለማለት ይሆን ደግሞ ከዮናስ ልታጣላኝ ነው ወይስ እውነት ያለችው ልክ ነው??? እኔና ሠላም መታጠብያ ቤት በር ላይ ግብ ግብ እንደገጠምን ወድያው ካሌብና ጓደኛዋ መጡ ልክ ሲያየኝ ፊቱ ተቀያየረ ምንድነው የመረጥሽውን መርጠሽ ሄደሻል ምን ቀርቶሽ ነው የምትከታተይኝ አለኝ በጣም ተናድጄ ቆይ አንተ ምንድነህ ካላሳበድከኝ አተወኝም ማለት ነው አልኩት ሁለታችንም በስሜት ከማውራታችን የተነሳ ሰው ፀጥ ብሎ ይሰማን ጀመር አስመሳይ ነሽ ለስሙ ስንት ፈተና አይተሻል ለስሙ ቤተሰብሽን ትተሻል ግን ያሁሉ መስዋዕት መክፈልሽ ዛሬ ሌላ ወንድ ያስመለክትሻል ብዬ አስቤም አላውቅም አንድ ቃል እንኳ ልሰሚኝ አትፈቅጂም ሁሉም ግን በግዜው ይገባሻል ሪታንም ቢሆን ሰበብ ያረግሽው አውቀሽ ነው ጭራሽ አስረገዝካት አልሽኝ ትንሽ እንዲመሳሰልልሽ ከሌላም ቢሆን ያረገዘች ሴት መፈለግ ነበረብሽ ያላረገዘን ሰው ግን ብሎ ንግግሩን ገታውና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰና ባንቺ ምክንያት ቤተሰቦቼ ተስፋ ያረጉትን ትምህርቴን አቆምኩ ደስ ይበልሽ ገና ልክ እንደዚ ጨርቄን ጥዬ አብዳለው...አለና የለበሰውን ቲሸርት እላዩ ላይቀደደው የእውነት ደነገጥኩ ግራ ገባኝ ይሄ ሁሉ ሲሆን የነበረው እኔና ካሌብን ለማለያየት ነው? እሺ ዮናስ ማነው እንዴትስ አገኘኝ ሰላም ቅድም እንዳቀደው በጁ አስገባሽ ያለችኝ እውነቷን ከሆነ አንድ ነገር አለ .... ይሄን እያሰብኩ እዛው ዞረብኝ የማስበው ነገር ካቅም በላይ ሆነብኝ ይሄኔ ጥያቸው ለመውጣት ስጣደፍ ዮናስ መጣና ያስሚንዬ ምንድነው አለኝ ምን እንደሆነማ አንተን ልጠይቅህ እስቲ ንገረኝ ካቅም በላይ ጥሩ የሆንክልኝ ለምንድን ነው አልኩት ንግግሬን ለቅሶዬ እያቆራረጠብኝ... ይሄኔ ሰላም ያለወትሮዋ እምባዋ እየወረደ ከዚ በላይ ካሌብ ሲሰቃይ ማየት አልፈልግም ሁሉም ነገር ድራማ ነበር ሪታን መሀል ያስገባትና እኔም ይበልጥ እንድትራራቁ ሳደርግ የነበረው ዮናስ አፈቅራታለው እናም በጄ አስገቡልኝ ብሎ ገንዘብ ይሰጠን ስለነበር ነው አሁን ግን በቃኝ ለካሌብ ሌላ ለያስሚን ሌላ እያወራውና እያሳየው ማራራቄ በቃኝ ፈጣሪስ ምን ይለኛል ብላ እያለቀሰች ወታ ሄደች ህልም ይሁን እውን መለየት አቃተኝ ሁሉም ሰው ግራ እንደገባው መገመት ቀላል ነበር፡፡ ወዴት እንደምሄድ ባላውቅም ልወጣ መንገድ ስጀምር ዮናስ ከፊቴ ቀድሞኝ መንገድ እየዘጋብኝ ሰክራ ነው አትስሚያት አለኝ ምንም ሳልለው እጁን አስለቅቄው መንገድ ስጀምር ሪታና ሰላም ተከታትለው ገቡ ከዛ ሪታ እግሬ ላይ ወድቃ እያለቀሰች ይቅርታ ጠየቀችኝ ፊልም የምተውን ይመስል ግራ ተጋባሁ ምንም ሳልላት ቆሜ ሁሉንም ማየት ጀመርኩ ይሄኔ ካሌብ እንደ እብድ እያረገው ሪታን ከግሬ ላይ አንስቶ ሁለቴ በጥፊ መታት ይሄኔ ካሌብዬ እረፍብዬ እጁን ያዝኩት፡፡ የኔና የካሌብ እንቅፋት ለካ መልአክ መስሎ የቀረበኝ ዮናስ ኖርዋል እምነትን መጠበቅ ግድ ቢሆንም ፍቅር ያሸንፋል ና እኔና ካሌብ ወደቀድሞ ፍቅራችን ተመልሰን መኖር ቀጥለናል እኔም ተጠምቄ የተዋህዶ እምነት ተከታይ ሁኛለሁ ትምህርታችንንም ቀን እየሰራን ማታ መማራችንን ቀጥለናል መሀላችን ከፈጣሪ በቀር ማንንም አናስገባም ቤተሰቦቼንም ጋር እራሱ በስልክ ተጣርቀን ለበአል ደግሞ ከካሌብ ጋር ሄጄ ይቅርታ ልጠይቅ ተስማምተና.......

                               ♾ተፈፀመ♾
                
  ምስጋና ፦ ታሪኩን በመከታተል ሀሳባችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረስልኝ 
          ፦  ሁላችሁንም ክበሩልኝ በቅርቡ በአዲስ ስራ እመጣለሁ ሀሳባችሁን Comment ላይ አሳውቁኝ 🙏
💛
@yefkr_kalee ❤️
💛
@yefkr_kalee ❤️
አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉

12.2k 0 29 21 154

‍ 💞ፍቅር ያሸንፋል💕

                  ክፍል አስራ ሁለት (12)

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


ሪታ እርጉዝ ነኝ ብላ ስትመጣ ራሴን ሳትኩ እሱን ብዬ የተንከራተትኩለት ፍቅረኛዬ ሌላ ሴት አስረግዞ ሳይ ዳግም በህይወት መኖር በራሱ ሞት ነው የመሰለኝ ከደቂቃዎች ቡሃላ ስነቃ ካሌብ እጆቹን አንተርሶኝ ምንጣፍ ላይ በጀርባዬ ተንጋልያለሁ ሪታ የለችም ነቅቼ ጠባብ ቤታችንን ስቃኛት ካሌብ ነቃሽ አለና እምባው ወረደ ያዞ እምባ አልኩ በውስጤ ዛሬ እንዲያውም የተፈጠረውን ለማስታወስ ማንንም መጠየቅ አልፈለኩም እናም በፍቅር ከምወዳቸው እጆቹ ላይ ተነሳሁ እንባዬ ሀዘኔን ያቀለው ይመስል ያለማቋረጥ እየወረደ በውሃ የራሰው ልብሴ ላይ ያርፋል እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ ልብሴን ሰብስቤ ሻንጣዬ ውስጥ ከተትኩት ይህን ሳደርግ ካሌብ በጥሞና ይከታተለኝ ነበር ከዛም ምንም ቃል ሳልተነፍስ ወደበሩ አመራሁ፡፡
ልክ በሩጋ ስደርስ ግራ የተጋባ እያስመሰለ ምን ተፈጠረ ውዴ ድጋሚ ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው አለኝ ቀጣፊ እምባውን እያዘነበ እስከዛሬ ቢሆን ሲያስነጥስ እንኳ እንባው ብትረግፍ ውስጤ በሀዘን ይጥለቀለቅ ነበር ዛሬ ግን እንዲ እያለቀሰና እየተማፀነኝ ፍፁም ሊያሳዝነኝ አልቻለም! ሪታስ አልኩት ይሄኔ አይኖቼን ላለማየት
እያቀረቀረ ሲጀመር ለምን እንደመጣች አላውቅላትም ሄዳለች አለኝ ይሄኔ ይበልጥ እየተናደድኩ ካሌብ ከዚ ቡሃላ ልትዋሸኝ አትችልም ይልቅ ፈጣሪ የሰጠህን ፀጋ አትግፋ ልጅህን እመንና አሳድግ እኔም ፈጣሪ ይገባሻል ያለኝን እያደረገ ነውና አርፌ እቺ አፀያፊ ህይወቴን ልኑራት ብዬ ገፍቼው ወጣሁ እንደዛ ሲሆን አይቼው አላውቅም መሬት ላይ ተደፍቶ ተንሰቀሰቀ ግን ሊያስቆመኝ አልቻለም ፡፡
ወጥቼ ሆቴል ልሄድ በየመንገዱ ብቻዬን እያወራው አለቅስ ነበር ከዛ ሆቴል ደርሼ የሰራተኞች ክፍል ገብቼ ተቀመጥኩ የሙሃሙድ ዘፈን ተከፍቶ ያቀነቅን ነበር
ተው ልመድ ገላዬ ገላዬ
ተው ልመድ ገላዬ
ትቶህ የሄደን ሰው ገላዬ
አትበል ከላላዬ...
ይላል ይሄን ሙዚቃ ስሰማ ቁስሌ የተነካ ያህል ተሰምቶኝ ተንሰቀሰኩ እእእእእ ከዛ እዛው የተቀመጥኩበት ጋር ጋደም አልኩና እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ልክ ስነቃ ሰአቱ ወደ መምሸት ተቃርቧል ከዛም እራሴን
መጠጣትና አጉል ሱሶችን መተው እንዳለብኝ አሳመንኩት ግን ስራ እስከማገኝ እዛው ሆቴል እያደርኩ መስተንግዶ መስራቴን ቀጠልኩ ሴት ልጅ ፈተናዋ ብዙ ቢሆንም የኔ ግን ልክ አጣ የሆቴሉ ባለቤት ልጅ እዛው ማደሬን ሲያይ ይፈታተነኝ ጀመር አንድ ቀን ዮናስ አጋጣሚ መጣ ከካሌብ ጋር እንደታረቅን ካወቀ ቡሃላ መጥቶ የማያውቀው ዮናስ ዛሬ ሳየው ልክ አባቷን እንዳየች ህፃን እምባዬ ባይኔ ሞላ የሚገርመው ፊቴን አይቶ ውስጤን ማንበብ ይችላል እናም ውጪ እፈልግሻለው ብሎኝ ወጣሁ እያለቀስኩ ካሌብ ያረገኝን ሁሉ ነገርኩት አባብሎኝ ሄደ ፡፡
ከዛ እንደቀድሞው እንገናኝ ጀመር ሁሌም እንደሚያረገው ያስቀኝና ሀዘኔን ያስረሳኛል አልፎም ስለ ወደፊት ይመክረኛል ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ማታ ተረኛ ሆኜ ቀን ላይ ከዮናስ ጋር ስንዞር ዋልን ፊልም አየን ብቻ ደስተኛ ነበርኩ የሚገርመው ምንም ያህል አብረን ብናሳልፍ ሴትነቴን ወይም ገላዬን አይመኝም ታድያ አብረን ውለን ልክ የስራ ሰአቴ ሲደርስ ወደ ሆቴል ሸኝቶኝ ተመለሰ ያን ቀን የሆቴሉ ባለቤት ልጅ ነበር እሱ ሲኖር ሁሉም ነገር ይቀፈኛል ዛሬም ልክ እንደዛው እየደበረኝ ሳስተናግድ ቆይቼ ሰአት ሲደርስ ልተኛ ክፍሌ ገባሁ ይሄኔ ተከትሎኝ ገባና ከውስጥ ቆለፈው ብጮሂ እገልሻለሁ አለኝና ልብሱን ለማውለቅ ቁልፉን ይፈታ ጀመር.....የመጨረሻው ይቀጥላል

✎ ክፍል አስራ ሶስት ✅የመጨረሻ ክፍል(13) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛 @yefkr_kalee 💜
💛 @yefkr_kalee 💜

9.2k 0 25 13 99

‍ 💞ፍቅር ያሸንፋል💕

                  ክፍል አስራ አንድ(11)

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 💛

በርግጥ ካሌብዬን አሁንም ቢሆን አልጠላሁትም ያም ማለት ግን በሱ ተስፋ አልቆረጥኩም ማለት አይደለም እናም ካጠገቤ መጥቶ ሲቆም ብደነግጥም በንግግሩ ግን በጣም ተናደድኩ የከዳኝ ሳያንሰው ከዮናስ ጋር ጠረጠረኝ መጠርጠሩም ሳያንሰው ይሄን ያክል ቀን የት እንደሆንኩ እንኳ የማያውቅና ያላሳሰበው ሰው ዛሬ ደርሶ እሱው ተበዳይ ሆነ ሁኔታዬ ሲቀያየርበት ዮናስ ያስሚን ችግር አለ እነሱ ማናቸው አለኝ ይሄኔ ሰላም ቀበል አድርጋ እሱ ፍቅረኛዋ ነው እኔ ደግሞ ጓደኛዋ ስትል ንዴቴን መቆጣጠር ይሳነኝ ጀመር ግን ከመናገር ይልቅ ጥያቸው መሄድን መረጥኩ ዮናስ አላስቻለውም ጠብቂኝ ቢያንስ ልሸኝሽ አለኝ ፀጥ ብዬው እርምጃዬን ቀጠልኩ ፡፡
ዮናስም ከጎን ከጎኔ እየሄደ ባለትዳር ነበርሽ እንዴ አለኝ ዝም አልኩት እሺ ተይው አትንገሪኝ ቅድም ስታቅፊኝኮ ሀንግ ልትሰሪኝ ነው የሚመስለው የማቀፍ ልምድ እንደሌለሽ ያስታውቃል ሆ አንቀሽ ልገዪኝ ... አለና ከት ብሎ ሳቀ እውነትም ዮናስ ይለያል ከካሌብ ጋር ያሳለፍኩትን እያሰብኩ ስረበሽ እሱ ግን አስረሳኝ ጭራሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን እረስቼ መሳቅ ጀመርኩ ከዛ ወደስራዬ ገባሁ ማታ ልምጣ ሲለኝ እና ላትመጣ ነው አልኩት እውነትም ቢቀር ይደብረኛል እሱም አንድ ቀን እንደካሌብ ቢከዳኝም እስከዛው ግን አብሬው በንፁ ጓደኝነት እቀጥላለው፡፡ እየሰራው የማስበው ጠዋት ካሌብዬ እንዴት ሰላምን አግኝቷት ነው አሷ ደሞ ማን ካፌ እንዳለው አውቃ ነው ይዛው የመጣችው እንዴት ወደኛ መጡ የሚለውን ነው ሲቀጥል ሰላም እንደዛ እንደተጎዳሁ እያወቀች ከካሌብ ጎን እንዴት ትቆማለች ጭራሽ ዮናስ እንዲርቀኝ ብቻ ሰላም ሁሉም ጠባሳዎቼ ላይ አሻራዋ ይታየኝ ጀመር እቺ ልጅ ከኛ ስር ለምን አልጠፋ አለች?? ብቻ ጭንቅላቴ እነዚን ጥያቄዎች እየፈጠረ ያስጨንቀኛል ግን ምንም መልስ ስላልነበረኝ በቃ አጋጣሚዎች ናቸው ብዬ አልፈዋለው. እንደምንም መሸ ይሄኔ ተጣጥቤ ልብሴን ቀይሬ ልወጣ ስል በር ላይ ካሌብን አገኘሁት አናግሪኝ አለኝ ግን ላናግረው አልቻልኩም ምክንያቱም በሱ ምክንያት እየሆንኩ ያለሁት በጣም ይጎዳል ዝምብዬው ስሄድ ለዚ ነበር ብዙ ፈተና አልፈሽ እኔን መርጠሽ የመጣሽው ለዚ ነበር አባትሽን አልሰማ ብለሽ እኔን የመረጥሽው? አለኝ ይሄኔ እርምጃዬን ገታ አድርጌ ማሰብ ጀመርኩ ከዛም ዞር ብዬ ምን ቀረህ ወይስ ሪታ ጥላክ ሄደች አልኩት እንደምታስቢው አይደለም ሲል ሊያሳምነኝ ሞከረ እኔም ከስካሁኑ ልፋቴ አይበልጥም ይቅርታ ላርግለት ብዬ ይቅርታ አረኩለት፡፡ ከካሌብ ጋር እንደገና አብረን መኖር ጀመርን በርግጥ በሙሉ ልቤ አላመንኩትም ግን ግዜ ሁሉን ያሳየኛል በሚል ፍቅር መስጠቴን ቀጠልኩ ሪታ ከቤታችን ወታለች ግን የት እንዳለች መጠየቅ አልፈለኩም ዮናስንም ሳገኘው ስለካሌብ ሁሉንም አጫወትኩት ግን ዮኒ ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም አላለኝም ወንድም ሊሆነኝ ቃል ገባልኝ ካሌብዬ ደግሞ ዮናስ ከሚባል ልጅ ራቂ ሲል አስጠንቅቆኛል እኔም ካሌብዬን ቅር ከሚለው እያልኩ ዮናስን ማግኘት ተውኩ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቁርስ እየሰራው ቤት አፀዳለው ይሄኔ የፍቅሬ እንቅፋት ሪታ በር አንኳኳች ስከፍት እሷ ናት በሩን ብጠረቅምባት ደስ ባለኝ ግን እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ ምን ፈለግሽ አልኳት ካሌብን አለችኝ ካሌብዬ ተኝቷል አልኳት ፊቷ ልክ አይደለም እናም ችግር አለ አልኳት ይሄን ስል እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ እርጉዝ ነኝ አለች ይህን ስትል ከካሌብ ነው እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ ብዥ አለብኝ ... እኔና ካሌብ ታርቀን በፍቅር 3 ወር እንኳ ሳንቆይ ሪታ እንደገና ህይወቴ ውስጥ ጣልቃ ገባች መቋቋም አቅቶኝ እራሴን ሳትኩ......ይቀጥላል


✎ ክፍል አስራ ሁለት (12) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefkr_kalee 💜
💛
@yefkr_kalee 💜


‍ 💞ፍቅር ያሸንፋል💕

                  ክፍል አስር(10)

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

እንዴት በቶሎ ሰከርኩ ወይስ እራሴን እንዳላውቅ መጠጤ ውስጥ መዳኒት አረጉብኝ? ምንም አላውቅም ብቻ ከንቅልፌ ባልነቃ ይሻለኝ ነበር እንደዛ እያለቀስኩና ደፍሮኛል ብዬ ያሰብኩትን ሰውዬ ምን እንደማደርገው እየዛትኩ እያለ ስልኬ ጠራ በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ማውራት አይደለም ደዋዩን ማየት አልፈለኩም ዘጋ ከዛ ድጋሚ ተደወለ አሁንም ዘጋ በመጨረሻ አነሳሁት ይሄኔ የኔሰካራም አስቸኳይ ጉዳይ ስለነበረኝ ነው ሳትነቂ ትቼሽ የሄድኩት አለኝ ይሄ በትክክልም የዮናስ ድምፅ ነው ግን ጆሮዬን ማመን አቃተኝና ማን ልበል አልኩ ወይ ጣጣ ሰካራም ጓደኛ መያዝኮ ችግሩ ይሄ ነው ዮናስ ነኝ ስመጣ የተፈጠረውን እነግርሻለሁ አለኝ የማወራው ስለጠፋብኝ ምንም ሳልለው ተሰናብቶኝ ስልኩን ዘጋው፡፡ በህይወቴ እንደዚ ጓጉቼ የማውቅበት ቀን ትዝ አይለኝም ዮናስን አግኝቼው ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓው አንድ ልቤ ደግሞ ከኔ ጋር ነው ያደርሽው ቢለኝ ሀፍረቱን መቋቋም የምችል አልመስልሽ አለኝ ብቻ ግን ሰአቱ መገስገሱን ቀጥሎ ፀሃይዋ ለመጥለቅ ትሰናዳ ጀመር እኔም ስራ የማታ ተረኛ ስለነበርኩ የመስተንግዶ ዩኒፎርሜን ለበስኩ ምሽት 12፡00 ሰአት ላይ ዮናስ ደወለ ስራ መሆኔን ስነግረው መጣ ግን ለማውራት እድል አጣሁ እሱም ይህን ተረድቶ ጠዋት እንደሚመጣ ቃል ገብቶልኝ ወደ ቤቱ ሄደ:: ልክ ሲነጋ ከእንቅልፌ ስነቃ ቶሎ ብዬ ስልኬን አየሁ መልክት ገብቶልኝ ነበር ዮኒ ነው እዛው አካባቢ የሚገኝ ካፌ ቀጠረኝ ተጣጥቤ ወደዛው አመራሁ ልክ ስደርስ ተነስቶ ሰላም አለኝና እንድቀመጥ ወምበር ስቦ ጋበዘኝ ለሴት ልጅ ክብር እንዳለው ያሳያል እኔ ግን ጉዳዬ የትላንት አዳሬን ማወቅ ነበር እናም ትኩስ ነገር አዘን ማውራት ቀጠልን፡፡ እእእእእእ አልኩ ጥያቄዬን ከምን መጀመር እንዳለብኝ ለማሰብ እየሞከርኩ የኔ ቆንጆ የምሬን
ልንገርሽ በጣም ታምሪያለሽ አለኝ ይሄኔ እንዲ ሊከዳኝ እንደንግስት ሲክበኝ የኖረው ካሌብ ትዝ አለኝና አይደል አልኩት እውነቴን ነው ትላንት ያ ሰውዬ ቀጥሮሽም ቢሆን ፈልገሽም ብትሄጂም የእንቅልፍ ኪኒን ብርጭቆሽ ውስጥ መጨመሩ አናዶኛል ሲቀጥል ገና ልጅ ነሽ እድሜሽን ከሚመጥን ሰው ጋር አትዝናኚም?አለኝ፡፡ ንግግሩ ይበልጥ ሳበኝ ኪኒን? ብዬ ቃሉን ደገምኩትና አስከትዬ ከዛስ ቆይ አንተ እንዴት... ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ እኔ ገና በግዜ ስደውልልሽ ያለሽበትን ነግረሽኝ ነበር በርግጥ ና አላልሽኝም ግን መጣሁ ስመጣ ከሰውጋ ሳይሽ ልክ ባልሆንም ከፋኝ ከዛ ሰውዬውን እህቴ ናት ስለው አንቺም ምንም ብሰክሪም እንኳን አላሳፈርሽኝም ወንድሜ ነው ብለሽ ሙጭጭ አልሽብኝ እናም ይዤሽ ያደርሽበት ሆቴል ወሰድኩሽ አለና ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ደሞ ያሳቅሽኝ አብረከኝ ሁን እፈራለው እያልሽ ስታለቅሺ አንጀቴን ነበር የበላሽኝ አለ ይሄኔ እኔም ምን እንዳረኩ እንኳ ባለማስታወሴ በሀፍረት አቀርቅሬ ፈገግ አልኩ ሳላስበው ደግሞ ምንም ሳያረገኝ ከዛ ሰውዬ ስላስጣለኝ በጣም ተደስቼና ወንድም ያገኘው ያህል ተሰምቶኝ ተነስቼ ጥምጥም አልኩበት ይሄኔ ከየት መጣ ሳልለው ካሌብዬ ከሰላም ጋር ካጠገቤ መቶ ቆመ ድንግጥ ብዬ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ይሄኔ ካሌብ አሀ ለካ አንቺም ወንድ አጊንተሽ ነው ትተሺኝ የሄድሽው አለኝ..........ይቀጥላል


✎ ክፍል አስራ አንድ (11) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefkr_kalee 💜
💛
@yefkr_kalee 💜

13.4k 0 35 48 163

‍ 💞ፍቅር ያሸንፋል💕

                  ክፍል ዘጠኝ (9)

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛


ሰውየው ካጠገቤ መቶ ለመቀመጥ ወንበር እያመቻቸ ሁላቹም ጠጡ ሂሳብ እንዳትጨናነቁ አላቸው አብረውኝ ወደተቀመጡት ፊቱን አዙሮ እነሱም በደስታ ሰውየውን በየተራ አቀፉት እኔ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አይኔን ብርጭቆዬ ላይ ተክዬ ብቻዬን ማውራቴን ቀጠልኩ በንግግሩ መልስ ያጣው በቀላል አማርኛ ሹገር ዳዲ የሚባለው ሰውዬ ቆንጆ የተከፋሽ ትመስያለሽ አለኝ አሁንም የአይኖቼን አቅጣጫ ሳልቀይር ዝም አልኩት ይሄኔ ማነህ ና ሌላ መጠጥ ታዘዛት አለና ለአንዱ አስተናጋጅ ትዛዝ ሰጠ እኔም ገልመጥ እያረኩት አመሰግናለው መቸገር አይጠበቅብህም አልኩት፡፡ እሱም በመልሴ የምፀት ቃል ፈገግ እያለ ምን መሰለሽ ቆንጆ ብሎ እጁን ወደ ትከሻዬ ላከው ይሄኔ መጠጥ ባደፋፈረው ልቤ ተማምኜ ከወንበሬ ተፈናጥሬ እየተነሳሁ እንዳትነካኝ ሰውዬ ወንዶች ስትባሉ ከሴት ጭን ውጪ የሚያስብ አእምሮ አልታደላቹም አልኩትና ጥያቸው መታጠብያ ክፍል ገባሁ፡፡
መታጠብያ ቤት ገብቼ ትንሽ እራሴን ካረጋጋው ቡሃላ ልወጣ ስል ሰላም ተከትላኝ ኖሮ መጣች እኔም አልፌአት ልሄድ ስል ያስሚን አለች እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆም አልኩ ተረጋጊ ውዴ ሰውዬው ላይ እንደዛ መሆን አልነበረብሽም አለችኝ ምንም ሳልመልስላት ትቻት ወደ ቦታዬ ሄድኩ ልክ ስቀመጥ ሰውየው ጠጪ አለኝ ባትለኝም እጠጣለው ብዬ ብርጭቆዬን አንስቼ ጨለጥኩትና ተነስቼ ወጣሁ ከዛም ወደ ሆቴል መንገድ ጀመርኩ፡፡ ሞቅ ስላለኝ ምንም አላውቅም ነበር ብቻዬን ስሄድ አንዴ ስስቅ አንዴ ሳለቅስ እብድ እመስል ነበር በዚ መሀል አንድ መልኩን በደምብ ያላየሁት ወጣት ሰላም አለኝ ቀናም ብዬ ሳላየው ዝም ብዬው መንገዴን ቀጠልኩ ኧረ አናግሪኝ ብቻሽን ከምትሄጂ ስለሀገር ጉዳይም ቢሆን እናውራ ሲል ንግግሩ ፈገግ አስብሎኝ ቀና ብዬ አየሁት ከዛም አመሰግናለው አብረሽኝ ለመሄድ ስለተስማማሽ አለ ፈገግ እንዳልኩ እብድ አልኩት ልጁ ዮናስ ይባላል አቋሙ በጣም ያምራል በዛ ላይ ለዛ ያለው ቀልዱ ሀዘን ያስረሳል ያን ቀን ሆቴል ድረስ እያሳቀኝ ሸኝቶኝ ስልኬን ተቀብሎኝ ተለያየን፡፡ በርግጥ ከዚ ቡሃላ ምንም አይነት ወንድ መቅረብ አልፈልግም በነጋታው እራሴን አሞኝ ስለነበር ተኝቼ ዋልኩ ከዛ ወደማታ ስልኬ ጠራ አንስቼ ሀሎ ስል ሪታ ነኝ ያስሚን የካሌብ ብላ...
ንግግሯን ሳትጨርስ ስልኩን ዘጋሁባት ንዴት መላ አካሌን አንቀጠቀጠኝ ከዛ ተነስቼ ትላንት ስጠጣ ያመሸሁበት ክለብ ሄድኩ ልክ ስደርስ የማላውቀው ስልክ ተደወለ ላለማንሳት ፈልጌ ዝም አልኩት ደግሞ ሲጠራ ግን አንስቼ ማን ልበል አልኩ ቁጣ በሚመስል ድምፅ ይሄኔ ኧረ ቀስ ሆ ስልኬን በቁጣ አታሳቂያት አለኝ ዮናስ ነበር ባያየኝም ፈገግ አልኩ የት ነሽ አለኝ ከዛ ያለሁበትን ነግሬው አየጠጣሁ ነው እንዳትመጣ ብዬ ዘጋሁበት፡፡
ከደቂቃዎች ቡሃላ የትላንትናው ሰውዬ መጣ ከዛም ከጎኔ ተቀመጠ ዝም ብዬ መጠጣቴን ቀጠልኩ ከዛ ግን እንዴትና በምን እንደሰከርኩ ባላቅም ስነቃ የሚያምር አልጋ ላይ እርቃኔን ተኝቻለሁ ደንግጬ ተፈናጥሬ ስወርድ ማንም የለም የማታው ሰውዬ አስክሮ እንደደፈረኝ ገባኝ መጨረሻዬ ይህ መሆኑ ይበልጥኑ አስለቀሰኝ......ይቀጥላል

✎ ክፍል አስር(10) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefkr_kalee 💜
💛
@yefkr_kalee 💜

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

210 484

obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur

ውሎህን ቃኝ"! አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ...
ሰላም ውድ የፍቅር ቃል ቤተሰቦች ከ 200 ሺ በላይ በተሰብሳቢዎቹ የካርድ ሽልማት ልንጀምር ነው ምን ይመስላችኋል በጥያቄ ነው ሽልማቶቹ
የኔ... ተከፍቼ ሳዝን እንደ ወንድም፣ በደስታዬ አብሮነት የማትደክም፣ ስትቆጣኝ እንደ አባት ፣ ስትመክረኝ እንደ እህት ፣ የኔ መልካም የፍቅሬ እናት፣ ...
​​​​​​​  ​​         ┈┈••◉❖◉●••┈          ዝም ብለሽ ስሚኝ🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ........
https://t.me/+kE5qcdRQO6tmNTE0