አብርሃም እሸቴ እና አብዲ ሰለሞን የነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የንግድ ሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ሆኑ
*****
አብርሃም እሸቴ እና አብዲ ሰለሞን የነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የንግድ ሥራ ፈጠራ ውድድር የሦስተኛው ምዕራፍ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ከሠላሌ የመጡት አብሮ አደጎቹ በኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የፈጠራ ሥራቸው ነው ውድድሩን ለማሸነፍ የበቁት፡፡
አብሮ አደጎቹ ውድድሩን በአንደኛነት በማጠናቀቃቸው የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት እና የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
አሸናፊዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአሸናፊዎቹ ያዘጋጀውን ከወለድ ነፃ 10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ፡፡
በተጨማሪም ሙሉዓለም እና ምስጋናው 2ኛ፣ አበባው እና አማረ 3ኛ፣ ዶ/ር ደሳለው ታደሰ 4ኛ እንዲሁም አምሳሉ መኮንን 5ኛ ወጥተዋል፡፡
ተወዳዳሪዎቹም በቅደም ተከተላቸው የ500 ሺህ፣ የ300 ሺህ፣ የ200 ሺህ እና የ150 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
@AAU_INFO_CENTER