የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስምንተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስጀመረ
=================================
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ስምንተኛውን ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በይፋ አስጀምረዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት የተጀመረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በዚህ ሀገራዊ ንቅናቄ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት በንቃት ተሳትፏል።
በመርሃ ግብሩ ወቅት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የችግኝ ተከላው ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቀነስ፣ የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ እና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ አካባቢ ለማስረከብ ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በየዓመቱ በንቃት በመተግበር የአካባቢ ጥበቃን፣ የደን ልማትን እና ዘላቂ ልማትን የሚደግፉ ተግባራትን በቀጣይነት እንደሚያከናውን ተጠቁሟል።
|➲| @ASTU_Network