ስህተትን የማረም ጥበብ
ስህተትህን እመን
ለራስህ አንድን ቁምነገር እንድትሰራ ልሞግትህ፡፡ ምናልባት ከአንተ ጋር የከረመው የሕይወት ዘይቤ ከዚህ ተቃራኒው ቢሆንም እንኳን፣ ከዚህ በኋላ ግን ስህተት ስትሰራ በቀላሉ ስህተትን አምኖ የመቀበልን “ቀላልነት” ለማዳበር ተጣጣር፡፡
ይህ ቁምነገር የሚጠቅመው ለራስህው ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ስህተታቸውን አምኖ መቀበል ለሌላው ሰው የሚጠቅም ነው የሚመስላቸው - ሌላ ትልቅ ስህተት! ስህተትህን በቀላሉ አምኖ የመቀበል ዝንባሌ፣ ከሁሉ በፊት ትክክለኛ እንደሆንክ ለማሳየት ከሚመጣ ትግልና ሸክም ነጻ ያወጣሃል፡፡
ሲቀጥልም፣ የእርማት እርምጃ የምትወስድበት ደረጃ ላይ ያስቀምጥሃል፡፡ በመጨረሻም፣ ሰዎች እንዲቀበሉህና እንዲገነዘቡህ መንገድን ይጠርግልሃል፡፡
የመሻሻያ እቅድን አውጣ
ማንኛውም ለውጥ በገጠመኝ አይመጣም፡፡ በተለይም ለውጥ ያስፈለገበት ሁኔታ ከአመለካከት ጋር የተገናኘ ሲሆን ሁኔታው እየከበደና የበለጠ ትኩረት እየፈለገ ይመጣል፡፡ በመነጋገር ላይ ያለነውን ስህተትን የመደጋገም ችግር ለመቅረፍ ልናስብባቸው የሚገቡን ነጥቦች አሉ፡፡
“ይህ ችግር እንዳለብኝ አምኜ ተቀብያለሁ?” “የችግሬ ምንጩ ምንድን ነው?” “ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እችላለሁ?” “ከየትኛው መጀመር አለብኝ?” “ለውጥ እያመጣሁ መሆኑን ለማወቅ መመዘኛዎቼ ምንድን ናቸው?” እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን በመመለስ እቅድ የተሞላበት እርምጃ ውስጥ መግባት ይቻላል፡፡
ዲሲፕሊንና ተጠያቂነትን አዳብር
አንድን ልማድ ለማዳበር የምንጀምረው ከዲሲፕሊን ነው፡፡ ፈጽሞ ማድረግ የማንችለውንና የማንፈልገውን ነገር ራሳችንን “በመቆንጠጥ” እና በማስገደድ ስናስጀምረው የዲሲፕሊንን መንገድ ጀምረናል ማለት ነው፡፡ በመቀጠልም ሁኔታው ብዙ ከመደጋገሙ የተነሳ ልማድ ሆኖ መሰረታዊ የባህሪይ ለውጥ ሲያመጣ ዲሲፕሊን ስራውን ሰርቷል ማለት ነው፡፡ በመጨረሻም አሮጌውን ዘይቤ ትተን አዲሱን በመተካት ማቆም እስከማንችል ድረስ ልማድ ሲሆን ዲሲፕሊን ስራውን ጨርሷል ማለት ነው፡፡
ምናልባት ይህንን ጉዞ ሙሉና ስኬታማ የሚያደርግልን አዲሱን ልማድ እስክናዳብር ድረስ በሃላፊነት የሚጠይቀንን ሰው ማግኘትና ለዚያ ሰው ፈቃዱን መስጠት ነው፡፡
መልካም ቀን፣ ያገሬ ሰዎች! እወዳችኋለሁ!
Join us.....
@Ab_book