መሳሪያ የሌለው ፍልሚያ
የየትኛውንም ዘመን የአለም ታሪክ መለስ ብለህ አጥና ፍልሚያና ውጊያ ያልነበረበት ወቅት ለማግኘት ያስቸግርሃል፡፡ በተያያዘ ሁኔታ በአለም ላይ የተደረጉ ፍሚያዎችን አጥና ላለበት ፍልሚያ የሚመጥን መሳሪያ ያልነበረው ሕብረተሰብ ፍልሚያው የተሸነፈ ሕብረተሰብ ነው፡፡ ይህ እውነታ አለማችን ከበሽታ ጋር፣ ከድህነት ጋር፣ ከተፈጥሮ አደጋዎች ጋርም ሆነ ጤና-ቢስ ከሆኑ ሰዎች ጋር ባሳለፈችው ፍልሚያ ተግባራዊነት ያለው እውነታ ነው፡፡
በአሁን ሰዓት በሕይወትህ የምትፋለመው ፍልሚያ ከአቅምህ በላይ ሆነ እያሸነፈህ እንደሆነ ከተሰማህ ምናለባት ተገቢውን መሳሪያ በእጅህ አላስገባህም ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ ፍልሚያህ የስሜት ቀውስ ይሁን፣ የአካል ጤንነት መጉደል ይሁን፣ የኢኮኖሚ ትግል ይሁን፣ የሰዎች አጉል ባህሪይ ይሁን . . . ምንም ይሁን! ትክክለኛው መሳሪያ ካለህ ታሸነፈዋለህ፣ ከሌለህ ደግሞ ትሸነፋለህ፡፡
ፍልሚያህን አስመልክቶ ልትሰራቸው ከምትችላቸው ስህተቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- አንደኛው፣ የግልህን ፍልሚያህ ከሰዎች ጋር የማዛመድና ሰዎችን ስላጠቃህ የግል ፍልሚያህን እንደምታሸነፈው የማሰብ ዝንባሌ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ለፍልሚያህ የማይመጥንን (የተሳሳተን) መሳሪያ የመጠቀም ዝንባሌ ናቸው፡፡
መጠየቅ ያለብህ ጥያቄዎች፡-
1) የምፋለመው ፍልሚያ ምንድን ነው?
2) ይህንን ፍልሚያ ለምንድን ነው ማሸነፍ ያቃተኝ?
3) ይህንን ፍልሚያ ለማሸነፍ የሚያስችለኝ ተገቢው የሆነው መሳሪያ ምንድን ነው?
4) ይህንን መሳሪያ እንዴት እጄ ማስገባት እችላለሁ?
አብዛኛዎቹን ፍልሚያዎችህን የምታሸንፈው ራስህን ለመለወጥ በምታደርገው የተሳካ ትግል መሆኑን ግን አትርሳ፡፡
Join us.....
@Ab_book