ከሰራተኝነት ወደ አምራችነት!
ቀኑን ሙሉ በስራ ሲባክኑ መዋልና ምርታማነት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ቀኑን ሙሉ ወዲህና ወዲያ ስላሉ ብቻ ስኬታማ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ስራ መስራት ማለት ውጤታማና ምርታማ መሆን ማለት አይደለም፡፡
ለምሳሌ፣ በአንዳንድ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሰራተኞች ብዙ ናቸው፣ አምራቾች ግን ጥቂት ናቸው፡፡ በግል ሕይወታችንም ቢሆን ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡ ከጠዋት እስከማታ፣ ሳምንቱን ሙሉ ስነባክንና ስንሯሯጥ ውለንና ከርመን መጨረሻ ላይ ያመረትነው (ያከናወንነው) ነገር ከሌለ ጊዜያችንን በከንቱ አባክነናል፡፡
በጣም እየሰራን ወራትና አመታት አስቆጥረን ብዙም ለውጥ ካላየን ምናልባት ምክንያቱ የምንሰራው ስራ ምርታማ የመሆኑን ጉዳይ ስላላሰብንበት ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በሚገባ ማሰብ ማለት ሁሉን ነገር ከዋናው ዓላማችንና ከግባችን አንጻር መቃኘት ማለት ነው፡፡
ከሰራተኝነት ወደ አምራችነት ለመዘዋወር አንዱ መንገድ በየቀኑ የምንሰራቸውን ስራዎች ቅደም ተከተል ማውጣት ነው፡፡ ይህንን ተግባር ለምንድን ነው የምተገብረው? ሌላ ሊቀድም የሚገባው ስራ ይኖር ይሆን? እዚህ ቦታ ዛሬ የምሄደው ለምንድነው? ሌላ ቀን ብሄድ ምን ችግር አለበት? ይህ የማደርገው ነገር ማከናወን ከምፈልገው ከዋናው አላማዬ ጋር ምን ግንኙነት አለው? . . . እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ሰራተኝነት ማለት የተገኘውንና ፊታችን የመጣውን ነገር ሁሉ ሲሰሩ መዋል ማለት ነው፣ አምራችነት ማለት ከአላማ አንጻር መስራት ማለት ነው፡፡ ሰራተኝነት ቢዚ ያደርገናል፣ አምራችነት ውጤታማ ያደርገናል፡፡ ሰራተኛ ሆነን አምራች ላንሆን እንችላለን፣ አምራች ሆነን ግን ሰራተኛ ላለመሆን አንችልም፡፡
ብዙ አጠናለሁ (ስራ) ውጤቴ (ምርት) ግን ጥሩ አይደለም . . . ብዙ አይነት ተግባሮች አከናውናለሁ (ስራ)፣ ነገር ግን የገቢዬ ምንጭ (ምርት) ግን አይጨምርም . . . ይኸው ብዙ ስደክም (ስራ) አመታት ሆነኝ፣ ሕይወቴ ግን ምንም ለውጥ የለውም (ምርት) . . . ብዙ ጓደኞች አሉኝ (ስራ)፣ ነገር ግን ከማንም ጋር የጠለቀና ውጤታማ ወዳጅነት እንደለኝ አይሰማኝም (ምርት) . . . ፡፡
ከላይ የተጠቀሱት አይነትና መሰል ስሜቶች ካሉብህ በሁኔታው በሚገባ አስብበት፡፡ ከሰራህ አይቀር ለምርታማነት ስራ፡፡ ከሮጥክ አይቀር ለማሸነፍ ሩጥ፡፡ ከለፋህ አይቀር ውጤት ለማግኘጥት ልፋ፡፡
Join us.....
@Ab_book