ሰረፈ ሰላም በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሩቃ እና በማሸት ስም የተለያዩ አስነዋሪ ተግባራት ሲፈፅም እንደ ነበረ ዑለሞች በምስክሮች ያረጋገጡበት አቶ ሚስባህ ከማል ከዚህ በኋላ መሰል ተግባራት እንዳይፈፅም ፈፅሞ ከተገኘም በህግ እንደሚከሰስ ፌደራል መጅሊሱ የፃፈው ደብዳቤ ይገልፃል። ይህ ግለሰብ ፈፀማቸው የሚባሉ ተግባራት እጅግ የሚሰቀጥጡ ናቸው። ምንም እንኳ አጀማመሩ የተጎዱ ስፖርተኞችን ወጌሻ በመሆን ማከም የጀመረ ቢሆንም ቀስ እያለ መድሃኒት ወደ መስጠትና ወጣ ባለ መንገድ ሩቃ ወደ መስጠት ተሸጋግሮ በስተመጨረሻ ወደ ጥንቆላው ዓለም እንደተቀላቀለ ዑለማዎቹ ጉዳዩን ለማጣራት በሄዱበት መንገድ ማረጋገጥ ችለዋል።
ሰዎች ኸይር የሰሩ እየመሰላቸው ከጅኖች ጋር መነጋገርና ማድረግ ይጀምሩና የጂን ዓለም ደግሞ ካልገበርክለትና አምልኮ ካልፈፀምክለት ስለማይታዘዝ ቀስ በቀስ ወደ ሽርክ ወደ ጥንቆላ ዓለም ይዘውት ይዘልቃሉ። ለዚህም ነው ከጅን ጋር የሚያቀራርቡ ነገሮች ፈፅሞ እርም ተደርገው የሚታዩት። በቁርአን እንደ ተገለፀው ሸይጧን ጅን ነው። ሸይጧን ደግሞ እንዴት እራሱን ቀያይሮ የሰውን ልጅ ለማጥመም እንደሚሰራ የታወቀ ነው። ሙስሊም ጅን ጋር ነው የማወራው እያለ ሸይጧንን ጓደኛው አድርጎ ከእስልምና ሊያስወጣው ይችላል። ከጅን ጋር ማውራት ትልቅ እውቀት አይደለም። ብዙ ሰዎች ከጅን ጋር ማውራት ብርቅ ስለሚመስላቸው የተለየ ጀብድ የፈፀሙ ይመስላቸውና ሳያስቡት ወደ ሽርክ ዓለም ሰምጠው ይገባሉ።
#ሼር #ሼር #ሼር
#sher #sher #sher
ያድርጉ
https://telegram.me/YASIRAJEL_ALEM