ሰለፍያ❗️❗️
በተውሂድ ጎዳና ጉዞ የጀመረ፣
ሽርክ ቢድዕውን በግልፅ ያነወረ፣
የኢብራሂም የኑህ የሹዕይብ ፋና፣
የሁድ የሙሀመድ የዛ የገናና፣
የሷሊህ የሙሳ የዒሳ ግሳፄ፣
ከሽርክ ራቁ ነው በሚያምር ቅላፄ፣
እኛም እንላለን ቅድሚያ ለተውሂድ፣
በዚህ ጎዳና ላይ በቀደምቶች መንገድ፣
አይናቸው ቢቀላ ፊታቸው ቢጠቁር፣
ሙሪዳቸው ቢጮህ ጅማቱ እስኪገተር፣
ሽርክን የተረዳ ቢድዕን ያወቀ፣
ከሱና ባህር ውስጥ ትንሽ የጠለቀ፣
በሱፍዮች ደሊል አይወናበድም፣
ጨርቁን ከጣለጋ በፍፁም አያብድም፣
ቁርዕንና ሀዲስ ምርኩዝ እያለለት፣
አይንቀዋለልም በጫት ስካር ተረት፣
አሏህ ያፅናን ሁሌም በሀቅ ጎዳና፣
በሰለፍያ ላይ በኢብራሂም ፋና፣
በተሸቆጠቆጠው ዉበት በደፋበት፣
በተውሂድ በሱና ይውሰደን ወደ ሞት፣
የሽርክ ማእበል እንዳይወዘውዘኝ፣
የቢድዕው ንፋስ እንዳያንሳፍፈኝ፣
ጌታየዋ እባክህ ብርታቱን ለግሰኝ፣
ከጎኔ ቁምልኝ ያ-አሏህ አግዘኝ፣
ምላሴ እንዳይቦዝን አንተኑ ከማውሳት፣
ላንተው ክፍት ዝግት ከንፈሬን አድርጋት፣
እግሮቼም ይዛሉ ይድከሙ ወደሱ፣
ከአረንጓዴው ጨፌ ጀነት እስኪደርሱ፣
ይህ ነው ሰለፍያ የኔ መታወቂያ፣
የምመዘንበት የክብደት መለኪያ፣
ሰሜና ስራየ ባይመጣጠንም፣
የእውነት ሰለፍይ ለመሆን ብጥርም፣
የአቅሜን እየፈፀምኩ ለድክመቴ እስቲግፋር፣
እመለሳለሁኝ ሁሌም ወደ ገፋር። https://t.me/AbuSarahh
በተውሂድ ጎዳና ጉዞ የጀመረ፣
ሽርክ ቢድዕውን በግልፅ ያነወረ፣
የኢብራሂም የኑህ የሹዕይብ ፋና፣
የሁድ የሙሀመድ የዛ የገናና፣
የሷሊህ የሙሳ የዒሳ ግሳፄ፣
ከሽርክ ራቁ ነው በሚያምር ቅላፄ፣
እኛም እንላለን ቅድሚያ ለተውሂድ፣
በዚህ ጎዳና ላይ በቀደምቶች መንገድ፣
አይናቸው ቢቀላ ፊታቸው ቢጠቁር፣
ሙሪዳቸው ቢጮህ ጅማቱ እስኪገተር፣
ሽርክን የተረዳ ቢድዕን ያወቀ፣
ከሱና ባህር ውስጥ ትንሽ የጠለቀ፣
በሱፍዮች ደሊል አይወናበድም፣
ጨርቁን ከጣለጋ በፍፁም አያብድም፣
ቁርዕንና ሀዲስ ምርኩዝ እያለለት፣
አይንቀዋለልም በጫት ስካር ተረት፣
አሏህ ያፅናን ሁሌም በሀቅ ጎዳና፣
በሰለፍያ ላይ በኢብራሂም ፋና፣
በተሸቆጠቆጠው ዉበት በደፋበት፣
በተውሂድ በሱና ይውሰደን ወደ ሞት፣
የሽርክ ማእበል እንዳይወዘውዘኝ፣
የቢድዕው ንፋስ እንዳያንሳፍፈኝ፣
ጌታየዋ እባክህ ብርታቱን ለግሰኝ፣
ከጎኔ ቁምልኝ ያ-አሏህ አግዘኝ፣
ምላሴ እንዳይቦዝን አንተኑ ከማውሳት፣
ላንተው ክፍት ዝግት ከንፈሬን አድርጋት፣
እግሮቼም ይዛሉ ይድከሙ ወደሱ፣
ከአረንጓዴው ጨፌ ጀነት እስኪደርሱ፣
ይህ ነው ሰለፍያ የኔ መታወቂያ፣
የምመዘንበት የክብደት መለኪያ፣
ሰሜና ስራየ ባይመጣጠንም፣
የእውነት ሰለፍይ ለመሆን ብጥርም፣
የአቅሜን እየፈፀምኩ ለድክመቴ እስቲግፋር፣
እመለሳለሁኝ ሁሌም ወደ ገፋር። https://t.me/AbuSarahh