ሙስሊሞች ለምን የንፅፅራዊ ሃይማኖቶች ጥናት አስፈለጋቸው?
አሁን አሁን «ሙስሊሞች ለምንድነው የአይሁድና የክርስትና እምነት አስተምህሮዎችን ርዕሰ ጉዳያቸው አድርገው የሚያስተምሩት?»፤ «ለምን የሌላው እምነት ይነካሉ?»፤ «ለምንስ የራሳቸው እምነት ብቻ አያስተምሩም?»፤ «በኢየሱስ ማንነት እና ምንነት ላይ ከመናገርም ሆነ ከመፃፍ ለምን አይታቀቡም…?» የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ ይስተዋላል፡፡
እውን ሙስሊሞች የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናትን እንደ አንድ አጀንዳ መያዛቸው ጠብ አጫሪነት ነው ወይስ በተጨባጭ ምክኒያትና አመክንዬ ላይ የተመሰረተ? ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ሙስሊሞች ለምን የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናት እንደሚያጠኑና ምንም ዓይነት የትንኮሳ ዓላማ (በተለይ ኦርቶዶክስን) እንደሌላቸው በአጭሩ ያስረዳሉ፡፡
1. ሙስሊሞች ምንም እንኳን በዒሳ (ኢየሱስ) ላይ በወረደው ኢንጂል (ወንጌል) እና በሙሳ ላይ በወረደው ተውራት (ኦሪት) የሚያምኑ ቢሆንም ቁርኣን ግን ከእነዚህ መፅሐፎች በኋላ የወረደ እንደመሆኑ በነዚህ መፅሐፍት ላይ የተፈፀሙትን የመበረዝና የመቀየር ስራዎች እንዲሁም የመፅሐፎቹ ተከታይ ነን የሚሉትን ክርስቲያኖች እና አይሁዶችን ሰፊ ትኩረት በመስጠት ይተቻል፡፡ «የመፅሐፉ ባለቤቶች ሆይ!» በሚል የሚጀምሩ በርካታ ክርስቲያንና አይሁድን የሚያናግሩ አናቅፅ በቁርኣን ውስጥ እናገኛለን፡፡ ሥላሴ፣ የኢየሱስ ጌትነት፣ የኢየሱስ መሰቀል አለመሰቀልና ሌሎችም በርካታ ክርስቲያኖች የነእሱ አጀንዳ ብቻ የሚመስሏቸው በርካታ ጉዳዮች ቁርኣን በሰፊው ዳሷቸዋል፡፡ በመሆኑም አንድ ሙስሊም ስለነዚህ ጉዳዮች ሲያወራ ቁርኣን ትኩረት ስለሰጠው አንድ የኢስላም አጀንዳ እንጂ ከቁርኣን ጋር ግንኙነት ስለሌለው የሌላ እምነት አጀንዳ ብቻ ስለሆነ ነገር እያወራ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ክርስቲያን ወንድሞቻችን ይህን ጉዳይ ለመረዳት ወንጌል በወቅቱ የነበሩትን አይሁዶች የተቸበትን ሁኔታ ቢያገናዝቡ ጠቃሚ ይመስለናል፡፡ ፈጣሪ አዲስ ኪዳን ውስጥ ከፊል አይሁዶችን “የአመንዝራ ልጆች” ብሎ በመጥራቱ እንደማይወቀስ ሁሉ በቁርኣንም መፅሐፍ ቅዱስን የበረዙ ወይም ኢየሱስን ፈጣሪ ነው ያሉ ክርስቲያኖችን በመተቸቱ ሊወቀስ አይችልም፡፡
2. ምንም እንኳን ከላይ የጠቀስነው ጉዳይ ለአንድ ሙስሊም ንፅፅራዊ ሃይማኖትን ለማጥናት መሰረታዊው እና በቂ ነጥብ ቢሆንም በአገራችን ለተሰሩት ንፅፅራዊ ስራዎች መንስኤ የሆነው ዋናው ጉዳይ ግን መጠነ ሰፊ የሆነው የሚሽነሪዎች ሃይማኖትን በስንዴና በዘይት የማስቀየር ስራ ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት የኢኮኖሚ ችግር አንፃር በርካታ በምዕራቡ ዓለም የሚረዱ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶችን ለማስተናገድ የተገደደች ሲሆን እነዚሁ ድርጅቶች የሚሰጡት ዕርዳታ ብዙ ጊዜ በስብአዊነት ላይ ብቻ የተመረኮዘ ከመሆን ይልቅ አብሮ የፕሮቴስታንት እምነትን ከማስፋፋት ጋር የተያያዘ መሆኑን ከሙስሊሞች በላይ ብዙ አማኞቿን የተነጠቀችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትረዳዋለች፡፡ ሚሽነሪዎች ለአንድ ችግረኛ ሙስሊም ስንዴና ዘይት ሰጥተው “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ሲሉት እኛ ደግሞ እንደነሱ ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለሌለን መርዳት ባንችል የቀረበለትን ኢየሱስን የመቀበል ጥያቄ መመለስ የሚያስችለው “እውን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው?!” የሚል ሲዲ ወይም መጽሐፍ ብናቀርብለት ትንኮሳ ነውን?
3. ከላይ እንደጠቀስነው ዋነኛው ንፅፅራዊ ስራዎች የተሰሩበት ዐላማ የፕሮቴስታንቱን የማክፈር እንቅስቃሴ ለመቀነስ የታለሙ እንጂ በምንም መልክ የኦርቶዶክስ አማኞችን ያነጣጠሩ አልነበሩም፡፡ በነዚህ ስራዎች የተፈለገው ኦርቶዶክስን መተቸት ቢሆን ኖሮ ኦርቶዶክስ ከሌሎች የክርስቲያን አንጃዎች የሚለይባቸውን እንደ ታቦት፣ ቅዱሳን፣ ቅርፃቅርፆች የመሳሰሉ ጉዳዮችን በሰፊው መተቸት ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን የስራዎቹ ዓላማ ይህ አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው በአገራችን የተሰሩት አብዛኞቹ የንፅፅር ስራዎች የዶ/ር ዛኪር እና የሸኽ አህመድ ዲዳትን ስራዎች ከመተርጐም ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ትምህርት የሰጡባቸው አገሮች ያሉት ክርስቲያኖች ፕሮቴስታንት አልያም ካቶሊክ እንጂ በፍፁም ኦርቶዶክስ አይደሉም፡፡
4. በሌሎች የክርስቲያን አንጃዎች የኦርቶዶክስን መሰረታዊ እምነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚተቹ በርካታ መፅሐፍት የተሰሩ መሆኑ እየታወቀ ሙስሊሙ በሰራቸው ኦርቶዶክስን ለይቶ በማይመለከቱ መፅሐፎችና ሲዲዎች ምክንያት ረብሻ ለማስነሳት መሞከሩ ከበስተጀርባው ፖለቲካዊ ዓላማ ሊኖረው እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባል፡፡
5. ሙስሊሙ የሚሰራቸው ስራዎች አሁን በክርስቲያኖች እየተፃፈ እንዳለው በስድብና በማንቋሸሽ ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን ምክንያታዊና ትህትና የተሞላበት አቀራረብ ነው፡፡ በመሰረቱ አንድ ሙስሊም እንደ ዒሳ (ኢየሱስ) እና መርየም የተከበሩ ሰዎችን ቢሰድብ ከእምነቱ እንደሚወጣ (እንደካደ እንደሚቆጠር) መታወቅ አለበት፡፡
6. በቁጥር 3 እንደተጠቀሰው በአገራችን የተሰሩት አብዛኞቹ ንፅፅራዊ ስራዎች የዶ/ር ዛኪርና የሸኽ አህመድ ዲዳት ስራዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች የሰጧቸው ትምህርቶች ወይም ያደረጓቸው ክርክሮች በአብዛኛው የተደረጉት እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ኖርዌይ፣ አሜሪካና ህንድ … የመሳሰሉ ሙስሊሞች በጣም አናሳ ወይም የሉም የሚባልበት አገሮች ሲሆን የትኛውም አገር ግን አንዳችም ችግር አልፈጠሩም፡፡ ተቃውሞ ካላቸው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አለመስማማታቸውን ከመግለፅ ባለፈ ሃይማኖታችንን አንቋሸሽክ ብሎ ጠብ የፈጠረ ሰው አለመኖሩን ሲዲዎቹ ይመሰክራሉ፡፡
7. የተሰሩት ሰራዎች ሚሽነሪዎችን የመከላከል ዓላማ እንጂ ኦርቶዶክስ ላይ ያነጣጠሩ አለመሆናቸውን የሚያረጋግጥልን ሌላው ነጥብ አገራችን ላይ የንፅፅራዊ ሃይማኖት ትምህርት በመስጠት ላይ ያሉ ሙስሊም ግለሰቦች ለትምህርት የተንቀሳቀሱባቸውን ክልሎች ብናጤን በአጠቃላይ የሚሽነሪ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው የደቡብና ከፊል የኦሮሚያ ክልሎች ብቻ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ኦርቶዶክስ ወደሚበዛባቸው የትግራይ ወይም የአማራ ክልል ሄዶ ንፅፅራዊ ትምህር ሰጥቶ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡
8. አንዳንድ ግለሰቦችና ሚዲያዎች የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናት ፅሁፎችን አገራችን ላይ መጀመሪያ የሰሩት ሙስሊሞች እንደሆኑ በመጥቀስ በክርስቲያኑ ወገን አሁን እየተፃፉ ላሉት ፈር የለቀቁ ተሳዳቢ ፅሁፎች ሙስሊሙን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ከብዙ አስርት ዐመታት በፊት ጀምሮ የሙስሊሙን እምነት የሚያንቋሽሹና የትችትን ሥርዓት ያልጠበቁ እንደ “ተዐምረ ማርያም”፣ “አፍሪቃና እስልምና” እና “ሙሐጀባ”… የመሳሰሉ መፅሐፍት መኖራቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
9. በሙስሊሙ በኩል ከክርስትና ጋር ግንኙነት ያላቸው መፅሐፍት ወይም ሲዲ ሲሰሩ የማስታወቂያ ፖስተሮች የሚለጠፉት መስጅዶች አካባቢ ብቻ እንጂ እንደሌሎቹ እምነቶች በየአደባባዩና መንገደ ላይ አለመሆኑ አሁንም በነዚህ ስራዎች ዓላማ የተደረገው ሙስሊሙ ራሱን ከሰባኪዎች ሊከላክልበት የሚችል ነገር ማስጨበጥ እንጂ ክርስቲያኑን መተንኮስ እንዳልሆነ በግልፅ ያሳያል፡፡
© ከ 9 አመት በፊት የተዘጋጀ ፅሁፍ